2012 (እ.አ.አ)
የገናን መንፈስ እንደገና ማግኘት
ዲሴምበር 2012


የቀዳሚ አመራ መልእክት፣ ታህሳስ 2012 (እ.ኤ.አ)

የገናን መንፈስ እንደገና ማግኘት

ፕሬዘደንት ቶማስ ኤስ ሞንሰን።

ከብዙ አመቶች በፊት እንደ ወጣት የቤተክርስቲያን ሽማግሌ፣ የታመሙ ልጆችን ለመባረክ ከሌሎች ጋር ወደ ሶልት ሌክ ስቲ ሆስፒታል ተጠርቼ ነበር። ወደ እዚያ እንደገባሁም፣ ደማቅ እና ሰላማዊ የሆኑ ብርሀኖች ያለውን የገና ዛፍ ተመለከትን፣ እናም ከተዘረጉት ቅርንጫፉቹ ስርም በጥንቃቄ የተሸፈኑ ስጦታዎችን አየን። ከእዚያም አንዳንዶቹ በእጃቸውና በእግራቸው ላይ ጀሶ ያላቸው፣ ሌሎቹ በቀላሉ ለመዳን የማይችል በሽታ ያለባቸው፣ ትንንሽ ወንዶች እና ሴቶች ልጆችን በሚገኙበት መተላለፊያው አልፈን ሄድን።

በጣም የታመመ ትንሽ ልጅ ጠራኝ እና፣ “ስምህ ማነው?” አለኝ።

ስሜን ነገርኩት፣ እና እንዲህም ጠየቀኝ፣ “በረከት ልትሰጠኝ ትችላለህ?”

በረከት ተሰጠው፣ እናም ከመኝታው ዞር ብለን ለመሄድ ስንጀምር፣ እንዲህ አለ፣ “በጣም አመሰግናለሁ።”

የተወሰነ እርምጃ ከወሰድን በኋላ፣ እንዲህ ብሎ ሲጣራ ሰማሁት፣ “ወንድም ሞንሰን፣ መልካም ገና።” ከእዚያም ታላቅ ፈገግታ ገፅታውን ሸፈነው።

ያም ልጅ የገና መንፈስ ነበረው። የገና መንፈስ በዚህ ወቅት ብቻ ሳይሆን አመቱን በሙሉ በልባችን እና በህይወታችን ሁላችንም እንዲኖረን ተስፋ የማደርገው ነው።

የገና መንፈስ ሲኖረን፣ በዚህ ወቅት የተወለደበትን የምናከብረውን እርሱን እናስታውሳለን፥ “ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና” (ሉቃስ 2:11)።

በእኛ ጊዜ የገና ወቅትን ለማክበር ስጦታ መስጠት ታላቅ ሚና ያለው ነው። ጌታ ለእርሱ ወይም ለሌሎች በዚህ በአመቱ ውድ ወቅት እኔ ምን ስጦታ እንድሰጥ ይፈልገኛል በማለት እራሳችንን መጠየቁ ጥቅም ካለው ብዬ አስባለሁ።

የሰማይ አባታችን ለእርሱ እና ለልጁ የታዛዥነት ስጦታ እንድንሰጥ እንደሚፈልግም ሀሳብ አቀርባለሁ። እርሱም ውድ ልጁ በመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ ሀሳብ እንደሚያቀርበው፣ ከራሳችን እንድንሰጥና ራስ ወዳጅ ወይም ስግብግብ ወይም ጠበኛ እንዳንሆን እንደሚጠይቀን ይሰማኛል፥

“እውነት እውነት እላችኋለሁ፣ የፀብ መንፈስ ያለበት ከእኔ አይደለም፣ ከዲያብሎስ እንጂ፤ እርሱም የፀብ አባት የሆነ እናም የሰዎችን ልብ እርስ በርስ እንዲጣሉ በቁጣ የሚያነሳሳ ነው።

“እነሆ፣ ሰዎችን አንዳቸውን ከሌላኛው ልባቸውን ለቁጣ የሚያነሳሳ ይህ የእኔ ትምህርት አይደለም፤ ነገር ግን እንደነዚህ ያሉ ነገሮች እንዲወገዱ ማድረግ ይህ የእኔ ትምህርት ነው።” (3 ኔፊ 11፥29–30)።

በእዚህ በአስደናቂ የዘመን ፍጻሜ፣ የማፍቀር እና ከራሳችን ለመስጠት ያለን እድሎች መጠን የላቸውም፣ ነገር ግን እነዚህም የሚጠፉ ናቸው። ዛሬ የምናስደስታቸው ልቦች፣ የሚባሉ ደግ ቃላት፣ የሚከናወኑ ስራዎች፣ እና የሚድኑ ነፍሳት አሉ።

ስለ ገና መንፈስ ብልህ አስተያየት ያለው አንድ ሰው እንደጻፈው፥

እኔ የገና መንፈስ ነኝ—

ወደ ድህነት ቤት ገብቼ፣ የደበዘዘ ፊት ያለውን ልጅ በሚያስደስት ድንቀት አይኖቹን እንዲከፍት አደርጋለሁ።

የስግብግብ ሰውን የተጨመጠ እጅ እንዲላላ፣ እና በዚህም በነፍሱ ላይ የሚያበራ ቦታ እንዲሳል አደርጋለሁ።

ያረጁት ወጣትነታቸውን እንዲያድሱ እና በድሮው ደስተኛ መንገድ እንዲስቁ አደርጋለሁ።

በልጆች ልብ ውስጥም ፍቅር ህይወት እንዲኖረው፣ እና እንቅልፍንም በምትሀት በታገዘ ሕልም የደመቀ እንዲሆን አደርጋለሁ።

የግዋጉ እግሮች የጨለመ ደረጃን በተሞላ ቅርንጫት በመውጣት፣ በአለም መልካምነት የተገረሙ ልቦችን ትተው እንዲሄዱ አደርጋለሁ።

አባካኙ የሚያጠፋበት መንገዱን እንዲቆያም እና ለሚወዱት ሰው የሚያስደስት እምባ፣የጠነከረ የሀዘንን መስምር የሚያጥብ እምባ፣ እንዲለቀቅ የሚያደርግ ምልክት እንዲልክ አደርገዋለሁ።

የጨለመ የእስር ቤት ክፍልን በመግባት፣ የቆሰለውን ሰው ምን ሊሆን ይችል እንደነበር እንዲያስታውስ እና ወደፊት ለሚመጣው ቀን እንዲመለከት እጠቁማለሁ።

ህመም ባለበት በጸጥተኛው፣ እና ለመናገር ደክሞ ጸጥ ያለ የሚያረካ ምስጋና በማሳየት በሚንቀጠቀጥበት ከንፈር ባለበት ቤት ውስጥ ቀስ ብዬ እገባለሁ።

በሺህ መንገዶችም፣ የደከመው አለም ወደ እግዚአብሔር ፊት እንዲመለከቱ፣ እናም ለትንሽ ጊዜም ትንሽ እና ጎስቋላ የሆኑትን ነገሮች እንዲረሳ አደርጋለሁ።

እኔ የገና መንፈስ ነኝ።1

እኛም የገና መንፈስን፣ እንዲሁም የክርስቶስ መንፈስን፣ በአዲስ እናግኝ።

ማስታወሻ

  1. E. C. Baird, “Christmas Spirit,” in James S. Hewitt, ed., Illustrations Unlimited (1988), 81.

ከዚህ መልእክት ማስተማር።

የፕሬዘደንት ሞንሰንን መልእክት ከቤተሰብ ጋር ስትካፈሉ፣ ጌታ ለእርሱ እና ለሌሎች ምን ስጦታ እንድንሰጥ እንደሚፈልገን የጠየቁትን ጥያቄ ላይ ትኩረት ለማድረግ አስቡበት። የቤተሰብ አባላት “የገና መንፈስን፣ እንዲሁም የክርስቶስ መንፈስን፣ በአዲስ” እንደሚያገኙ ሀሳባቸውን እንዲጽፉ (ወይም ለትትንሽ ልጆች ስዕል እንዲስሉ) አበረታቷቸው።