የሴቶች የቤት ለቤት ማስተማሪያ መልእክት፣ ታህሳስ 2012 (እ.ኤ.አ)
የሴቶች የቤት ለቤት ጉብኝት፣ የደህንነት ስራ
ይህን መዝገብ አጥኑ እና ተገቢ ከሆነ ከምትጎበኟቸው እህቶች ጋር ተወያዩት። እህቶቻችሁን ለማጠናከር እና የሴቶች መረዳጃ ማህበርን የህይወታችሁ ተሳታፊ ክፍል እንዲሆን እንዲረዳችሁ ጥያቄዎቹን ተጠቀሙባቸው።
የሴቶች የቤት ለቤት ጉብኝት ለሴቶች የመጠበቅ፣ የማጠናከር፣ እና እርስ በራስ የማስተማር እድል ይሰጣል —ይህ በእውነትም የደህንነት ስራ ነው። በሴቶች የቤት ለቤት ጉብኝት፣ እህቶች በአዳኝ ምትክ ያገለግላሉ እናም ሴቶችን ለዘለአለማዊ ህይወት በረከቶች ለማዘጋጀት ይረዳሉ።
ፕሬዘደንት ስፔንሰር ደብሊው. ኪምባል (1895–1985) እንዳሉት “ጌታ በራዕዮቹ እንዳለው፣ ‘እነርሱ ማስጠንቀቅ፣ ማብራራት፣ እናም ማስተማር፣ እናም [ሌሎችን] ወደ ክርስቶስ እንዲመጡ መጋበዝ አለብን’” (ት. እና ቃ. 20፥59)። ቀጥለውም እንዲህ አሉ፣ “ምስክራችሁ አስደናቂ ማከናወኛ ነው።”1
እንደ ሴቶች የቤት ለቤት አስተማሪዎች ስለወንጌል እውነት ያለንን እውቀት ስንጨምርበት፣ ምስክርነቶቻችን ፣ለመጠመቅ እና የቤተክርስቲያን የአባልነት ማረጋገጫን ለመቀበል እየተዘጋጁ ያሉትን እህቶቻችንን ያጠናክራሉ እናም ይደግፋሉ። አዲስ አባላትን በወንጌል ውስጥ እንዲተከሉ ይረዳቸዋል። ጉብኝታችን እና ፍቅራችን “የተበተኑትን ለመመለስ [እና] ልባቸው በወንጌል ላይ ቀዝቀዝ ያሉትን ለማሞቅ” ይረዳል።2 እናም እህቶች በቤተመቅደስ በመሳተፍ ወደ ክርስቶስ እንዲመጡ እናበረታታለን።
“ነፍሳትን ታድናላችሁ፣ እናም አሁን በቤተክርስቲያኗ ንቁ ተሳታፊ የሆኑ ሰዎች፣ ንቁ ተሳታፊ ምናልባት የሆኑትበት ምክንያት እናንተ በቤቶቻቸው ውስጥ ስለምትገቡ እና አዲስ አስተያየት ስለሰጣችኋቸው ይሆናል። መጋረጃውን ከፍታችኋል። አድማሳቸውን ዘርግታችኋል። …
“እነዚህን እህቶች ብቻ ሳይሆን፣ ምናልባት ባሎቻቸውን እና ቤቶቻቸውን እያዳናችሁ እንደሆናችሁ ትመለከታላችሁ።”3
ከቅዱሳት መጻህፍት
ከታሪካችን
ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ የሴቶች መረዳጃ ማህበርን ሲያደራጅ፣ ሴቶች ደሆችን መንከባከብ ብቻ ሳይሆን ነፍሳትን ማዳን እንዳለባቸው ተናግሯል። የቤተክርስቲያኗ ሴቶች በሰማይ አባት የደህንነት አላማ ውስጥ አስፈላጊ ሀላፊነት እንዳላቸውም አስተምሯል።4 ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ ባስተማራቸው መሰረታዊ መርሆች በመመራት፣ እኛ እንደ ሴቶች መረዳጃ ማህበር እህቶች ሴቶችን እና ቤተሰቦቻቸውን ለእግዚአብሔር ታላቅ በረከቶች ለማዘጋጀት አብረን ለመስራት እንችላለን።
ፕሬዘደንት ብሪገም ያንግ (1801–77) እንዳሉት “እርስ በራስ ርህራሄ ይኑረን፣ እናም ጠንካራ የሆኑት ደካማዎችን ወደ ጥንካሬ በጥንቃቄ ይንከባከቡ ፣ እናም ለመመልክት የሚችሉትም አይነ ስውር የሆኑት ለእራሳቸው መንገዱን ለማየት እስኪችሉ ድረስ ለመምራት ይችላሉ።”5
© 2012 በIntellectual Reserve, Inc መብቶቹ በህግ የተጠበቁ። በዩ.ኤስ.ኤ የታተመ። እንግሊዘኛ የተፈቀደበት፧ 6/11 (እ.ኤ.አ) ትርጉም የተፈቀደበት፧ 6/11 (እ.ኤ.አ) Visiting Teaching Message, December 2012 ትርጉም። Amharic። 10372 506