2013 (እ.አ.አ)
ከጓዳኛ ጋር መካፈል
ፌብሩወሪ 2013


ወጣቶች

ከጓደኛ ጋር መካፈል

አንድ ቀን ለሰምነሪ ክፍል ሳጠና፣ የሚያምር ልዩ የሆነ ስሜት ተሰማኝ። በሚቀጥለው ቀን የምንማረውን ሳነብ፣ የትምህርት ቤት ጓደኛዬ ፊት ታየኝ እናም ከእርሷ ጋር ምስክሬን መካፈል እንደሚገባኝ ጠንካራ ስሜት ተሰማኝ።

ይህ ስሜት ግልጽ ቢሆንም፣ ፈርቼ ነበር። እርሷም የቤተክርስቲያን አባል ለመሆን የምትፈልግ ሴት ስለማትመስል፣ ጐደኛዬ ትቃወመኛለች ብዬ ፈራሁ።

የወጣት ሴቶች አጠቃላይ ፕሬዘደንት የነበሩት እህት ሜሪ ኤን. ኩክ በሀይል እንድንሰራና ጀግኖች እንድንሆን ያበረታቱንን ንግግር አሰብጉበት።1 እንደዚህ ለመሆን ፈለግኩኝ፣ ስለዚህ ለዚያች ሴት ደብዳቤ ጻፍኩኝ እናም ስለቤተክርስቲያኗ እውነተኛነትና ለመፅሐፈ ሞርሞን ስላለኝ ፍቅር መሰከርኩኝ። በሚቀጥለው ቀን መፅሐፈ ሞርሞንን እና ደብዳቤዬን በቦርሳዋ ውስጥ አስገባሁ።

በሚያስደንቀኝ ሁኔታ፣ ጓደኛዬ ለወንጌሉ ተቀባይ ነበረች። ከዚያ ቀን ጀምሮ፣ ከመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ በምታጠናበት ምን እንደተማረች ትነግረኝ ጀመረች። ከጥቂት ሳምንቶች በኋላ፣ ከወንጌል ሰባኪዎች ጋር አስተዋወቅኳት። ወዲያውም፣ የምትማረው እውነት እንደሆነ የመንፈስ ቅዱስ ማረጋገጫን አገኘች። የወንጌል ሰባኪዎች እና እኔ ስለስሜቷ ስትነግረን አለቀስን። ጓደኛዬም ተጠመቀች፣ እናም ወላጆቿም እንዴት እንደተለወጠች በመመልከት ተደንቀው ነበር።

ፍርሀቴን ለማሸነፍና ወንጌልን ወደ ህይወቷ ለማምጣት ለመርዳት በመቻሌ ደስተኛ ነኝ።

ማስታወሻ

  1. የሜሪ ኤን. ኩክን፣ “Never, Never, Never Give Up!” ተመልከቱ Liahona፣ ግንቦት 2010፣ 117-19።

አትም