2013 (እ.አ.አ)
ወደ ጌታ መቀየር
ፌብሩወሪ 2013


የሴቶች የቤት ለቤት ጉብኝት መልእክት፣ የካቲት 2013 (እ.ኤ.አ)

ወደ ጌታ መቀየር

ይህንን መልእክት አጥኑ እና ተገቢ ከሆነ ከምትጎበኟቸው እህቶች ጋር ተወያዩት። እህቶቻችሁን ለማጠናከር እና የሴቶች መረዳጃ ማህበርን የህይወታችሁ ተሳታፊ ክፍል እንዲሆን እንዲረዳችሁ ጥያቄዎቹን ተጠቀሙባቸው። ለተጨማሪ መረጃ ወደ www.reliefsociety.lds.org ሂዱ

ምስል
የሴቶች መረዳጃ ማህበር ማህተም

እምነት • ቤተሰብ • እርዳታ

የቤተክርስቲያኗ አዲስ እህቶች፣ እንዲሁም ወደ ሴቶች መረዳጃ ማህበር የሚገቡ ወጣት ሴቶች፣ እንደገና መሳተፍ የጀመሩ እህቶች፣ እና አዲስ ተቀያሪዎች፣ የሴቶች የቤት ለቤት አስተማሪዎች ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል። የአስራ ሁለት ሐዋሪያት ቡድን አባል ሽማግሌ ኤም. ራስል ባለርድ እንዳሉት፣ “የተቀየሩትን ለመጠበቅ እናም ተሳታፊ ያልሆኑትን አባላት ወደ ሙሉ ተሳታፊነት ለመመለስ የአባላት እርዳታ በጣም አስፈላጊ ነው። “የሴቶ መረዳጃ ማህበር… ከቤተክርስቲያኗ ውስጥ ካሉት የጓደኝነት መንገዶች መካከል ሀይለኛ የሆነው እንደሆነ አስተያየት ይኑራችሁ። ወደሚማሩት እና ወደተሳታፊነት ወደሚጀምሩት ቀድማችሁ ተገኙ፣ እናም በክፍሎቻችሁ በሙሉ ወደ ቤተክርስቲያኗ በፍቅር አቅርቧቸው።”1

እንደ ሴቶች መረዳጃ ማህበር አባላት፣ አዲስ አባላት የቤተክርስቲያኗን መሰረታዊ ተግባሮችን እንዲማሩ መርዳት እንችላለን፥

  • ንግግር ማቅረብ።

  • ምስክርነትን መስጠት።

  • የጾም ህግን መኖር።

  • አስራት እና በኩራትን መክፈል።

  • በቤተሰብ ታሪክ ስራ መሳተፍ።

  • ለሞቱ ትውልዶች ጥምቀትንና የቤተ ክርስቲያን አባልነት ማረጋገጫን ማከናወን።

ሽማግሌ ባለርድ እንዳሉት፣ “አዲስ አባላት ምቾት እንዲያገኙና በቤተክርስቲያኑ ተቀባይነት እንዳላቸው እንዲሰማቸው ጥሩ ጓደኛ ያስፈልጋቸዋል።”2 ሁላችንም፣ ግን በተለይም የሴቶች የቤት ለቤት አስተማሪዎች፣ “ወደ ጌታእንዲቀየሩ” (አልማ 23፥6) ለመርዳት ከአዲስ አባላት ጋር ጓደኝነትን የመመስረት አስፈላጊ ሀላፊነት አለን።

ከቅዱሳት መጻህፍት

2 ኔፊ 31፥19–20ሞሮኒ 6፥4

ከታሪካችን

ፕሬዘደንት ጎርደን ቢ. ሂንክሊ (1910–2008) እንዳሉት፣ “ሁልጊዜም በቁጥር በሚያድጉ ተቀያሪዎች፣ መንገዳቸውን እንዲያገኙ ለመርዳት ታላቅ ተጨማሪ ጥረቶች ማድረግ አለብን። እያንዳንዱም ሶስት ነገሮች ያስፈልጓቸዋ፥ ጓደኛ፣ ሀላፊነት፣ እና ‘በእግዚአብሔር በመልካም ቃላት’ (Moroni 6:4) እንክብካቤ።”3

የሴቶች የቤት ለቤት አስተማሪዎች የሚጠብቋቸውን ለመርዳት ችሎታ አላቸው። ጓደኝነትአብዛኛውን ጊዜ መጀመሪያ ይመጣል ፣ልክ ለአንድ በእድሜ ለገፋች እህት የጉብኝት አስተማሪ ለሆነችው ወጣት እህት የሴቶች መረዳጃ ማህበር እንደሆነው። የማጽዳት ስራንጎን ለጎን በመሆን እስኪሰሩ ድ ረስ እነርሱ ጓደኝነትን ለመመስረት ረጅም ጊዜ ወስዶባቸው ነበር። ጓደኞች ሆኑ፣ እናም ስለሴቶች የቤት ለቤት ትምህርት ሲነጋገሩ፣ ሁለቱም “በእግዚአብሔር መልካም ቃል” ተመገቡ።

ፕሬዘደንት ጆሴፍ ፊልዲንግ ስሚዝ (1876–1972) እንዳሉት፣ የሴቶች መረዳጃ ማህበር “በምድር ላይ ባለው የእግዚአብሔር መንግስት አስፈላጊ ክፍል ነች እናም … ታማኝ አባላቷ በሰማይ አባት መንግስት ውስጥ የዘለአለም ህይወት እንዲያገኙ ትረዳቸዋለች።”4

ማስታወሻዎች

  1. ኤም. ራስል ባለርድ፣ “Members Are the Key፣” Liahona፣ መስከረም 2000፣ 18።

  2. ኤም. ራስል ባለርድ፣ Liahona፣ መስከረም 2000፣ 17።

  3. ጎርደን ቢ. ሒንክሊ፣ “Every Convert Is Precious፣” Liahona፣ የካቲት፣ 1999፣ 9።

  4. ጆሴፍ ፊልዲንግ ስሚዝ፣ በ Daughters in My Kingdom: The History and Work of Relief Society ውስጥ (2011)፣ 97።

ምን ማድረግ እችላለሁ?

  1. ለጓደኛዬ በመጸለይ እህቶቻችንን ስናገለግል መንፈስ እንዲመራን እጠይቃለሁን?

  2. የምንጠብቃቸው እያንዳንዷ እህት በእውነት ስለእርሷ እንደምናስብ እንድታውቅ ዘንድ እንዴት ልናገለግላት እንችላለን?

አትም