2013 (እ.አ.አ)
የቤተመቅደስ ቃል ኪዳኖች
ኤፕረል 2013


የሴቶች የቤት ለቤት ማስተማሪያ መልእክት፣ ሚያዝያ 2013 (እ.አ.አ)

የቤተመቅደስ ቃል ኪዳኖች

ይህን መልእክት አጥኑ እና እንደተገቢነቱ ከምትጎበኟቸው እህቶች ጋር ተወያዩት። እህቶቻችሁን ለማጠናከር እና የሴቶች መረዳጃ ማህበርን የህይወታችሁ ተሳታፊ ክፍል እንዲሆን እንዲረዳችሁ ጥያቄዎቹን ተጠቀሙባቸው። ለተጨማሪ መረጃ ወደwww.reliefsociety.lds.org ሂዱ

ምስል
የሴቶች መረዳጃ ማህበር ማህተም

እምነት • ቤተሰብ • እርዳታ

ፕሬዘደንት ቶማስ ኤስ. ሞንሰን “ወደ ሰማይ አባታችን በዘለአለማዊ የቤተሰብ ግንኙነት አንድ ቀን እንድንመለስ እና ከበላይ በበረከቶች እና በሀይል እንድንባረክ የሚፈቅዱልን በቤተመቅደስ ውስጥ የምንቀበላቸው ስርዓቶች ለሁሉም መስዋዕቶችና ለሁሉም ጥረቶች ብቁነት ያላቸው ናቸው”1 ብለዋል። ወደ ቤተመቅደስ ገና ያልገባችሁ ከሆናችሁ፣ ቅዱስ የቤተመቅደስ ስርዓቶችን ለመቀበል በእነዚህ ለመዘጋጀት ትችላላችሁ፥

  • በሰማይ አባት፣ በኢየሱስ ክርስቶስ፣ እና በመንፈስ ቅዱስ እመኑ።

  • ስለኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያና በዳግም ስለተመለሰው ወንጌል ያላችሁን ምስክርነት አሳድጉ።

  • ህያው ነቢያትን ደግፉ እናም ተከተሉ።

  • ወደ ቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃድ ወረቀት ለማግኘት ብቁ ለመሆን አስራትን ክፈሉ፣ በስነምግባር ንጹህ ሁኑ፣ ታማኝ ሁኑ፣ የጥበብ ቃላትን አክብሩ፣ እና ቤተክርስቲያኗ በምታስተምረውም በስምምነት ኑሩ።

  • ጊዜን፣ ችሎታን፣ እና ያላችሁን የጌታን መንግስት ለመገንባት ስጡ።

  • በቤተሰብ ታሪክ ስራ ተሳተፉ።2

ፕሬዘደንት ሞንሰን በተጨማሪ እንዳስተማሩት፣ “[በቤተመቅደስ] ውስጥ የገባናቸውን ቃል ኪዳኖች ስናስታውስ፣ እያንዳንዱን ችግሮችን ለመቋቋም እና ፈተናዎችን ለማሸነፍ ተጨማሪ ችሎታ ይኖረናል።”3

ከቅዱሳት መጻህፍት

ትምህርት እና 1.ቃል ኪዳኖች 14፥7; 25፥13109፥22

ከታሪካችን

“ከናቩ ቤተመቅደስ ቅደሳ በኋላ ከ5 ሺህ በላይ ቅዱሳን ሞልተውት ነበር። …

“የቤተመቅደስ ቃል ኪድኖች ጥንካሬ፣ ሀይል እና በረከቶች የኋለኛ ቀን ቅዱሳን ወደ [ምዕራብ] በሚጓዙበት፣ በብርድ፣ በሙቀት፣ በርሀብ፣ በድሀነት፣ በበሽታ፣ በአደጋ፣ እና በሞት [በሚሰቃዩበት] [ደገፏቸው]።”4

እንደ ብዙዎቹ የሴቶች መረዳጃ ማህበር እህቶች፣ ሳራ ሪች እንደ ቤተመቅደስ ሰራተኛ አገለገለች። ስለአጋጣሚዋም እንዲህ አለች፥ “በዚያ ቤተመቅደስ ውስጥ በጌታ መንፈስ በእኛ ላይ የፈሰሰው እምነትና እውቀት ባይኖር ኖሮ፣ ጉዞአችን በጭለማ እንደሚዘል አይነት ይሆን ነበር። … ነገር ግን፣ …የእርሱ የተመረጥን ሰዎች እንደሆንን እየተሰማን፣ በሰማይ አባታችን እምነት ነበረን፣ … እናም በሀዘን ምትክ፣ የዳንንበት ቀን በመምጣቱ ደስታ ተሰማን።”5

ለታማኝ የኋለኛ ቀን ሴቶች ስደቱ “በጭለማ የሚዘለልበት” አልነበረም። በቤተመቅደስ ቃል ኪዳኖቻቸው ተደግፈው ነበር።

ማስታወሻዎች

  1. ቶማስ ኤስ. ሞንሰን፣ “ቅዱስ ቤተመቅደስ—የአለም ምልክት፣” Liahona, ግንቦት 2011፣ 92።

  2. Daughters in My Kingdom: The History and Work of Relief Society (2011)፣ 21 ተመልከቱ።

  3. ቶማስ ኤስ. ሞንሰን, Liahona, ግንቦት 2011፣ 93።

  4. Daughters in My Kingdom፣ 29–30።

  5. ሳራ ሪች፣ Daughters in My Kingdom፣ ውስጥ 30።

ምን ማድረግ እችላለሁ?

  1. በቤተመቅደስ በየጊዜው እያመለክሁኝ ነኝን?

  2. እህቶቼ የቤተመቅደስ በረከቶችን እንዲቀበሉ እያነበታታኋቸው ነኝን?

አትም