2013 (እ.አ.አ)
ተነስቷል
ኤፕረል 2013


የቀዳሚ አመራር መልእክት፣ ሚያዝያ 2013 (እ.አ.አ)

ተነስቷል

ምስል
ፕሬዘደንት ሔንሪ ቢ አይሪንግ

የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ እውነተኝነት ምስክር የተስፋና የልብ ውሳኔ መንጭ ነው። ይህም ለማንም የእግዚአብሔል ልጅ እንዲህ ሊሆን ይችላል። እናቴ በሰኔ 1969 (እ.አ.አ) በበጋ ቀን በሞተችበትም ቀን ይህም ለእኔ እንደዚህ ነበር፣ ከዚያም በኋላ ለነበሩት አመታትም እንደዚህ ነበር፣ እናም እንደገና እስከማያት ጊዜም ድረስ እንደዚህ ይሆናል።

ለጊዜ ለመለያየት ያለ ሀዘን ወዲያው በደስታ ተተክቷል። ለደስተኛ ግንኙነት ከነበረው ተስፋ በላይ ነበር። ጌታ በነቢያቱ በኩል በጣም ብዙ ገልጾ ስለነበርና መንፈስ ቅዱስ የትንሳኤን እውነተኛነት ለእኔ ገልጾልኝ ስለነበር፣ ከተቀደሱትና ከሞት ከተነሱት ውዶቻችን ጋር እንደገና መገናኘት ምን እንደሚመስል በአዕምሮዬ ለመመልከት እችላለሁ።

“እነዚህም በጻድቃን ትንሳኤ የሚመጡት ናቸው። …

“እነዚህም እግዚአብሔር እና ክርስቶስ ሁሉንም በሚፈርዱበት በሰማይ ስሞቻቸው የተጻፉላቸውም ናቸው።

“እነዚህ የአዲስ ኪዳን አማላጅ በሆነው፣ ይህን ፍጹም የኃጢአት ክፍያን በመፈጸም የራሱን ደም በማፍሰስ ባከናወነው በኢየሱስ ፍጹም የሆኑት ጻድቃን ሰዎች ናቸው” (ት. እና ቃ. 76፥65፣ 68–69)።

ኢየሱስ ክርስቶስ የሞትን እስር ስለበጠሰ፣ ወደ አለም የተወለዱ የሰማይ አባት ልጆች በሙሉ እንደገና በማይሞት ሰውነት ከሞት ይነሳሉ። ስለዚህ፣ ስለዚያ አስገራሚ እውነት ያለን የእኔና የእናንተ ምስክርነት የተወዳጅ የቤተሰብ አባል ወይም ጓደኛ መጥፋትን ሀዘን ይቀንሰዋል እናም በአስደሳች ጉጉት እና በፅኑ ውሳኔም ይተካዋል።

ጌታ ለሁላችንም የትንሳኤን ስጦታ ሰጥቶናል፣ በዚህም መንፈሳችን ምንም ባልተጓደለ ሰውነት ውስጥ ይቀመጣል (አለማ 11፥42–44 ተመልከቱ)። እናቴ ወጣት እና የደመቀች ትሆናለች፣ የእድሜና የብዙ አመት የሰውነት ስቃይ ውጤትም ይወገዳሉ። ያም ለእርሷና ለእኛ እንደ ስጦታ ይመጣልናል።

ነገር ግን ከእርሷ ጋር ለዘለአለም ለመሆን የምንፈልገው ለእንደዚህ አይነይ ግንኙነት ብቁ ለመሆን፣ አብ እና ውድ ከሞት የተነሳው ልጁ በግርማ በሚኖሩበት ለመኖር ምርጫዎች ማድረግ አለብን። በዚያ ቦታ ብቻ ነው የቤተሰብ ህይወት ለዘለአለም ለመቀጠል የሚችሉት። የዚያ እውነት ምስክርነት እራሴንና የማፈቅራቸውን የኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ በህይወታችን ውስጥ እየሰራ ለሰለስቲያል መንግስት ከፍተኛ ደረጃ ብቁ እንድንሆን ለማድረግ ያለኝ ውሳኔ እንዲያድግ እድርጎልኛል (ት. እና ቃ. 76:70 ተመከቱ)።

ጌታ ለዘለአለም ህይወት ባለን ፍላጎት እኔን የሚረዳኝ እና እናንተን ሊረዳ የሚችል መመሪያ በቅዱስ ቁርባን ጸሎቶች ውስጥ ሰጥቶናል። በእያንዳንዱ የቅዱስ ቁርባን ስብሰባ ላይ የጥምቀት ቃል ኪዳናችንን ዕንድናድስ ተጋብዘናል።

አዳኝን ሁልጊዜም ለማስታወስ ቃል እንገባለን። የመስዋዕቱ ምልክቶችም የሞትን እስር ለመበጠስ፣ ምህረትን ለእኛ ለማቅረብ፣ እና ንስሀ ለመግባት ከመረጥን ለኃጢያቶቻችን በሙሉ ስርየት ለማቅረብ የከፈለውን ዋጋ ታላቅነት በምስጋና እንድናስብበት ይረዳናል።

ትእዛዛቱን ለማክበርም ቃል እንገባለን። ቅዱስ መጻህፍትን እና የህያው ነቢያትን ቃላት ማንበብና በቅዱስ ቁርባን ስብሰባዎቻችን በመንፈስ የተሞሉ ተናጋሪዎችን ማድመጥ ይህን እንድናደርግ ቃል የገባናቸውን እንድናስታውስ ያደርጉናል። መንፈስ ቅዱስም በዚያ ቀን መጠበቅ ያለብንን ትእዛዛት ወደ አዕምሮአችንና ወደ ልባችን ያመጣቸዋል።

በቅዱስ ቁርባን ጸሎቶች ውስጥ፣ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን ወደ እኛ ለመላክ ቃል ይገባልናል (መሮኒ 4፥35፥2ት. እና ቃ. 20፥77፣ 79 ተመልከቱ)። በዚያም ጊዜ እግዚአብሔር እንደ ግል ቃል-መጠይቅ አይነት መስጠት እንደሚችል ስሜት አግኝቼአለሁ። ያስደሰተው ምን ነገሮች እንዳደረግሁኝ፣ ለንስሀ እና ለምህረት የሚያስፈልጉኝን፣ እና ለእርሱ እንዳገለግል የሚፈልገኝን ሰዎች ስምን አመለካከት እንዳውቅ ያደርገኛል።

በአመቶች ውስጥ፣ ያም የተደጋገመ አጋጣሚ ተስፋን ወደ ልግስና ስሜት ቀይሯል እናም ምህረት በአዳኝ የኃጢያት ክፍያና በትንሳኤው እንደተከፈተ ማረጋገጫ አምጥቷል።

አዳኛችን፣ እና ፍጹም ምሳሌአችንና የዘለአለም ህይወት መመሪያችን ክርስቶስ እንደተንሳ እመሰክራለሁ።

ከዚህ መልእክት ማስተማር።

“ለእኛ ጥቅምና ትምህርት ይሆኑ ዘንድ ሁሉንም ጥቅሶች ከእኛ ጋር [ማመሳሰል]” ይገባናል (1 ኔፊ 19:23)። በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 20፥76–79 ውስጥ የሚገኙትን የቅዱስ ቁርባን ጸሎቶችን ለማንበብ አስቡባቸው። ፕሬዘደንት አይሪንግ ስለቅዱስ ቁርባን ጸሎቶች ያስተማሩትን ካነበባችሁ በኋላ፣ የምታስተምሯቸው እነዚህ ጸሎቶች ህይወታቸውን እንዴት መምራት እንደሚያስችሉ እና ከሰማይ አባትና ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር እንደገና ለመኖር እንደሚርዷቸው እንዲያስቡበት ጋብዟቸው።

አትም