2013 (እ.አ.አ)
ወደ እኔ ኑ
ሜይ 2013


የሴቶች የቤት ለቤት መልእክት፣ ግንቦት 2012 (እ.አ.አ)

“ወደ እኔ ኑ”

በቃላቶቹ እና በምሳሌው፣ ወደ እሱ እንዴት መቅረብ እንደምንችል ክርስቶስ አሳይቶናል።

በዚህ በኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርሰቲን ጉባኤ ከእናንተ ጋር በመሆኔ አመስጋኝ ነኝ። ይህች የእርሱ ቤተክርስቲያን ናት ወደ መንግስቱ ስንገባ ስሙን በእራሳችን ላይ እንቀበላለን። እርሱ እግዚአብሔር፣ ፈጣሪ፣ እና ፍጹም ነው። እኛ ለሞት እና ለኃጢያት ተገዢ የሆንን ሟቾች ነን። ነገር ግን ለእኛና ለቤተሰቦቻችን ባለው ፍቅር፣ ወደ እርሱ እንድንቀርብ ይጋብዘናል። ቃላቱም እንዲህ ይላሉ፥ “ወደ እኔ ቅረቡ እና እኔም ወደ እናንተ እቀርባለሁ፤ ተግታችሁም ፈልጉኝ እናም ታገኙኝማላችሁ፤ ለምኑ፣ ትቀበላላችሁ፤ አንኳኩ፣ ይከፈትላችሁማል።”1

በዚህ በትንሳኤ ጊዜ እርሱን ለምን እንደምናፈቅር እና ታማኝ ደቀ መዛሙርቶቹን የልብ ጓደኞቹ እንደሚያደግር ስለገባው ቃል ኪዳን እንድናስታውስ ተደርገናል። አዳኝ ያን ቃል ኪዳን ገብቷል እናም ለእርሱ በምናገለግልበት እርሱ እንዴት ወደ እኛ እንደሚመጣ ነግሮናል። አንዱ ምሳሌም ኦሊቨር ካውደሪ በመፅሐፈ ሞርሞን ትርጉም ከነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ ጋር ጌታን ሲያገለግል በተሰጠው ራዕይ ነበር፥ “እነሆ፣ አንተ ኦሊቭር ነህ፣ እናም በፈቃድህ ምክንያት ተናግሬሀለሁ፤ ስለዚህ እነዚህን ቃላት በልብህ አከማች። የእግዚአብሔርን ትእዛዝ በመጠበቅ ታማኝ እና ትጉህ ሁን፣ እናም በፍቅሬ እቅፍ ውስጥም አደርግሀለሁ።”2

በብዙ ጊዜ ለትእዛዛት ታዛዥነት በመሆነ ወደ ጌታ የመቅረብ እና እርሱም ወደ እኔ የመቅረቡን ደስታ አገኝቻለሁ።

እናንተም እንደዚህ አይነት አጋጣሚዎች አላችሁ። ይህም በቅዱስ ቁርባን ስብሰባ ለመሳተፍ ስትመርጡ ይሆናል። በልጅነቴበሰንበት ላይ ይህም ለእኔ ደረሰ። በእነዚያ ቀናት ቅዱስ ቁርባንን የምንቀበለው በምሽት ስብሰባ ጊዜ ነበር። ከቤተሰቤና ከቅዱሳን ጋር ለመሰብሰብ ትእዛዝን ሳከብር የነበረበኝ ከ65 አመት በፊት የነበረኝ የአንድ ቀን ትዝታ አሁንም ወደ ጌታ እንድቀርብ ያደርገኛል።

በውጪ ጭለማና ብርድ ነበር። ከወላጆቼ ጋር በቤተክርስቲያን ውስጥ እያለሁ ብርሀን እና ሙቀት ተሰምቶኝ እንደነበር አስታውሳለሁ። ከሰማይ አባታችን ጋር ልጁን ሁልጊዜ ለማስታወስ እና ትእዛዛቱንለማክበር ቃል ኪዳን እየገባን በአሮናዊ ክህነት ባለስልጣኖች የተላለፉትን ቅዱስ ቁርባን ወሰድን።

በስብሰባው መጨረሻ ላይ “Abide with Me ፤ ’Tis Eventide” የሚለውን መዝሙር ዘመርን፣ በዚህም “አቤቱ አዳኝ፣ በምሽት ከእኔ ጋር ቆይ” የሚሉ ቃላት ነበሩ።3

በዚያ ምሽት የአዳኝ ፍቅር እና ቅርብነት ተሰማኝ። እናም የመንፈስ ቅዱስ መፅናኛም ተሰማኝ።

በልጅነቴት በዚያ የቅዱስ ቁርባን ስብሰባ የተሰማኝን የአዳኝ ፍቅር እና የእርሱ ቅርብነትን ስሜት እንደገና ለማግኘት ፈለግሁኝ። ስለዚህ በቅርብ ሌላ ትእዛዝን አከበርኩኝ። ቅዱሳት መጻህፍትን ፈተሽኩኝ። በእነዚህም ውስጥ፣ መንፈስ ቅዱስ ከሞት የተነሳው ጌታ ሁለት ሐዋሪሪያት ወደ ቤታቸው እንዲመጣና ከእነርሱ ጋር እንዲቆይ የጠየቁበትን ግብዣ ሲቀበል የተሰማቸው አይነት ስሜት ለማግኘት እንደገና ለመመለው እንደምችል አወቅሁኝ።

ከተሰቀለበት እና ከተቀበረበት ሶስተኛ ቀን በኋላ ስለነበረው አነብባለሁ። ታማኝ ሴቶች እና ሌሎች ከመቃብሩ ድንጋዮ ተንከባሎ አገኙት እናም ሰውነቱ በዚያ አልነበረም። ለእርሱ ባላቸው ፍቅር ምክንያት ሰውነቱን ለመቀባት ነበር የመጡት።

ሁለት መላእክት መጡ እና እንዲህ በማለት ለምን እንደሚፈሩ ጠየቋቸው፥

“ሕያውን ከሙታን መካከል ስለ ምን ትፈልጋላችሁ?

“ተነሥቶአል እንጂ በዚህ የለም። የሰው ልጅ በኃጢአተኞች እጅ አልፎ ሊሰጥና ሊሰቀል በሦስተኛውም ቀን ሊነሣ ግድ ነው እያለ ገና በገሊላ ሳለ ለእናንተ እንደ ተናገረ አስቡ።”

4

የማርቆስ ወንጌል ከመላእክት አንዱ የሰጠውን መመሪያ ጨምሯል፥ “ነገር ግን ሄዳችሁ ለደቀ መዛሙርቱ ለጴጥሮስም። ወደ ገሊላ ይቀድማችኋል፤ እንደ ነገራችሁ በዚያ ታዩታላችሁ ብላችሁ ንገሩአቸው አላቸው።”5

ሐዋሪያት እና ደቀ መዛሙርቶች በኢየሩሳሌም ተሰብስበው ነበር። ልንሆን እንደምንችልም፣ እነርሱ ስለሙት እና ስለትንሳኤው የሰሙት ሀተታ ምን ትርጉም እንዳለው ሲነጋገሩ ፈርተውና ተደንቀው ነበር።

በዚያ ቀን ከሰዓት በኋላ ሁለቱ ሐዋሪያት ከኢየሩሳሌም ወደ ኤማሁስ በሚመራው መንገድ ላይ ነበሩ። በትንሳኤ የተነሳው ክርስቶስ በመንገዱ መጣላቸው እና ከእነርሱ ጋር ይሄድ ነበር። ጌታ ወደ እነርሱ መጥቶ ነበር።

የሉቃስ መፅሐፍ ከእነርሱ ጋር አብረን እንድንሄድ ያደርጋል፥

“ሲነጋገሩና ሲመራመሩም፥ ኢየሱስ ራሱ ቀርቦ ከእነርሱ ጋር ይሄድ ነበር፤

“ነገር ግን እንዳያውቁት ዓይናቸው ተይዞ ነበር።

“እርሱም። እየጠወለጋችሁ ስትሄዱ፥ እርስ በርሳችሁ የምትነጋገሩአቸው እነዚህ ነገሮች ምንድር ናቸው? አላቸው።

“ቀለዮጳ የሚባልም አንዱ መልሶ። አንተ በኢየሩሳሌም እንግዳ ሆነህ ለብቻህ ትኖራለህን? በእነዚህ ቀኖች በዚያ የሆነውን ነገር አታውቅምን? አለው።”6

የእስራኤል አዳኝ እንደሆነ በእርሱ እምነት ስለነበራቸው ኢየሱስ ሞት ስላላቸው ሀዘን ነገሩት።

በሀዘን ላይ ላሉት እነዚህ ሁለት ሀዘነኛ ደቀመዝሙርቶች ሲናገር ከሞት በተነሳው ጌታ ድምጽ ውስጥ የፍቅር ስሜት ይሰማ ይሆንም ነበር።

“እርሱም፣ እናንተ የማታስተውሉ፥ ነቢያትም የተናገሩትን ሁሉ ልባችሁ ከማመን የዘገየ፤

“ክርስቶስ ይህን መከራ ይቀበል ዘንድና ወደ ክብሩ ይገባ ዘንድ ይገባው የለምን? አላቸው።

“ከሙሴና ከነቢያት ሁሉ ጀምሮ ስለ እርሱ በመጻሕፍት ሁሉ የተጻፈውን ተረጐመላቸው።”7

ከዚያም ከትንሽ ልጅነቴ ጊዜ ጀምሮ ልቤት ያሞቅ የነበረው ጊዜ መጣ፥

“ወደሚሄዱበትም መንደር ቀረቡ፥ እርሱም ሩቅ የሚሄድ መሰላቸው።

“እነርሱ፣ ከእኛ ጋር እደር፥ ማታ ቀርቦአልና ቀኑም ሊመሽ ጀምሮአል ብለው ግድ አሉት፤ ከእነርሱም ጋር ሊያድር ገባ።8

ኤማሁስ ደንበር አቅራቢያ ወዳለው ወደ ደቀመዛሙርቶቹ ቤት ለመግባት አዳኝ በዚያ ምሽት ግብዣን ተቀበለ።

ለመመገብ ከእነርሱ ጋር ተቀመጠ። እንጀራውን አንስቶ ባረከ፣ ቆርሶም ሰጣቸው። ዓይናቸውም ተከፈተ፥ አወቁትም። ከዚያም እርሱም ከእነርሱ ተሰወረ። ሉቃስ የእነዚያ የተባረኩ ደቀመዛሙርቶች ስሜት ለእኛ መዝግቦልን ነበር፥ “እርስ በርሳቸውም፣ በመንገድ ሲናገረን መጻሕፍትንም ሲከፍትልን ልባችን ይቃጠልብን አልነበረምን?” ተባባሉ።9

በዚያም ሰዓት፣ ሁለቱ ሐዋሪያት ምን እንደደረሰባቸው ለአስራ አንዱ ሐዋሪያት ለመንገር ወደ ኢየሩሳሌም በፍጥነት ሄዱ። በዚያም ጊዜ አዳኝ እንደገና ታየ።

ለአባቱ ልጆች ኃጢያቶች በሙሉ ለመክፈል እና የሞትን እስር ለመበጠስ ስለተተነበየበት ተልዕኮው ገመገመ።

“እንዲህም አላቸው። ክርስቶስ መከራ ይቀበላል በሦስተኛውም ቀን ከሙታን ይነሣል፥

“በስሙም ንስሐና የኃጢአት ስርየት ከኢየሩሳሌም ጀምሮ በአሕዛብ ሁሉ ይሰበካል ተብሎ እንዲሁ ተጽፎአል።

“እናንተም ለዚህ ምስክሮች ናችሁ።”10

የአዳኝ ቃላት በዚያ ጊዜ ለደቀመዛሙርቶቹ እንደነበሩ አሁንም ለእኛ እውነት ናቸው። ስለእነዚህ ነገሮች ምስክሮች ነን። ወደ ኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን በምንጠመቅበት ጊዜ የተቀበልናቸው ግርማዊ ሀላፊነቶች ከብዙ መቶ አመቶች በፊት በሞርሞን ውሀዎች ላይ ነቢዩ አልማ ግልፅ አድርጎልን ነበር፥

“እናም እንዲህ ሆነ እንዲህም አላቸው፥ እነሆ፣ የሞርሞን ውሃ ይህ ነው፣ (እንደዚህም ነበር የተጠሩት) እናም አሁን፣ እናንተ ወደ እግዚአብሔር በረት ለመምጣትና፣ ህዝቡ ትባሉ ዘንድ፣ እንዲሁም አንዳችሁ የአንዳችሁን ሸክም ቀላል እንዲሆኑ ዘንድ ለመሸከም ፈቃደኞች በመሆን እንደፈለጋችሁ፤

አዎን፣ እናም ከሚያዝኑት ጋር ለማዘን፤ መፅናናትን ለሚፈልጉም ካፅናናችኋቸው፤ እናም በሁሉም ጊዜ በሁሉም ነገርና፣ በምትኖሩበት ቦታዎች ሁሉ፣ እስከሞት ድረስ፣ የእግዚአብሔር ምስክር በመሆን ትቆሙ ዘንድና፣ በጌታ ትድኑ ዘንድ፣ እናም ዘለዓለማዊ ህይወትም ይኖራችሁ ዘንድና የፊተኛውን ትንሳኤ ከሚያገኙት ጋርም ለመቆጠር ፈቃደኞች ከሆናችሁ —

አሁን እላችኋለሁ፣ ይህ የልባችሁ ፍላጎት ከሆነ፣ እርሱን እንደምታገለግሉ እናም ትዕዛዛቱን እንደምትጠብቁ፣ እርሱም በእናንተ ላይ መንፈሱን በብዛት ያፈስባችሁ ዘንድ በፊቱ እንደምስክርነት ከእርሱ ጋር ቃል ኪዳን በመግባት በጌታ ስም ለመጠመቅ የሚያስቸግራችሁ ምንድን ነው?

“እናም አሁን ህዝቡ ይህንን አባባሉን በሰሙ ጊዜ፣ በደስታ አጨበጨቡ፣ እናም በደስታ ይህ የልባችን ፍላጎት ነው ብለው ጮኹ።”11

እርዳታ የሚያስፈልጋቸውን ከፍ ለማድረግ እና በህይወት እስካለን ድረስ የአዳኝ ምስክር ለመሆን በቃል ኪዳን ስር ነን።

ይህን ያላውድቀት ለማድረግ የምንችለው ለአዳኝ ስላለን ፍቅር እና እርሱ ለእኛ ስላለን ቅፍር ስሜት ሲኖረን ብቻ ነው። ቃል ለገባናቸው ታማኝ ስንሆን፣ ለእርሱ ያለን ፍቅር ይሰማናል። እርሱን በማገልገል ሀይሉና ወደ እርሱ የምንቀርብበት ስለሚሰማን ይህም ይጨምራል።

ፕሬዘደንት ቶማስ ኤስ. ሞንሰን ጌታ ለታማኝ ደቀመዛሙርቶቹ ጌታ ስለገባው ቃል ኪዳን በየጊዜው እንድናስታውስ ያደርጉናል፥ “እናም የሚቀበሏችሁም ቢሆን፣ እኔም በዚያም እገኛለሁ፣ በፊታችሁም እሄዳለሁና። በቀኛችሁ እና በግራችሁ እሆናለሁ፣ እናም መንፈሴም በልቦቻችሁ ውስጥ ይገኛል፣ እናም መላእክቶቼም እንዲያዝሏችሁ ይከብቧችኋል።”12

እኔ እና እናንተ እርሱ ወደ እኛ ሲቀርብ ስሜት የምናገኝበት ሌላ መንገድ አለ። በእርሱ አገልግሎት መለኮታዊ ስንሆን፣ በቤተሰቦቻችን ለምናፈቅራቸው የቀረበ ይሆናል። ለጌታ አገልግሎት ወደ ሌላ ቦታ እንድሄድ ወይም ቤተሰቤን ትቼ እንድሄድ በምጠራበት በእያንዳንዱ ጊዜ፣ ጌታ ባለቤቴን እና ልጆቼን እንደሚባርክ ተመልክቻለሁ። የእርሱን አፍቃሪ አገልጋዮችን እና ቤተሰቤት ወደ እርሱ የሚያቀርቡ እድሎችን ያዘጋጃል።

እንዲህ አይነት በረከቶችንም በህይወታችሁ ተሰምቷችኋል። ብዙዎቻችሁ ከዘለአለም ህይወት መንገድ ተንከራትተው የሚሄዱ የምናፈቅራቸው አሉ። እነርሱን ለመመለስ ምን በተጨማሪ ለማድረግ እንደምትችሉ ታስቡበትም ይሆናል። እርሱን በእምነት ስታገለግሉ ጌታ ወደ እነርሱ እንዲቀርብ ልትመኩበት ትችላላችሁ።

ጆሴፍ ስሚዝ እና ኦሊቨር ካውደሪ ከቤተሰቦቻቸው በተለዩበት ጊዜ ጌታ የገባላቸውን ቃል ኪዳን ታስታውሳላችሁ፥ “በእውነት ባልንጀሮቼ ስድኒ እና ጆሴፍ፣ ጌታ ለእናንተ እንዲህ ይላል፣ ቤተሰቦቻችሁ ደህና ናቸው፤ በእጆቼም ውስጥ ናቸው፣ እና መልካም እንደሚመስለኝም አደርግባቸዋለሁ በእኔ ሁሉም ሀይል አለና።”13

እንደ አልማ እና እንደ ንጉስ ሞዛያ፣ አንዳንድ ታማኝ ወላጆች ጌታን በደንብ እና ለረጅም ጊዜ ቢያገለግሉም፣ ምንም እንኳን ወላጆቻቸው ለጌታ ወስዋዕት ቢያደርጉም የተንከራተቱ ልጆች ነበሯቸው። በሚያፈቅሩ እና በታማኝ ጓደኞች ቢረዱም፣ ለማድረግ የሚችሉትን ሁሉ ምንም ውጤት ያለማየት እድርገዋል።

አልማ እና የዚያ ቀኑ ቅዱሳን ለልጁና ለንጉስ ሞዛያ ልጆች ይጸልዩ ነበር። መልአክም መጣ። የእናንተ ጸሎት እና እምነታቸውን የሚጠቀሙበት ሰዎች ጸሎቶች የቤተሰብ አባላትን ለመርዳት የጌታ አገልጋዮችን ያመጣል። ቤተሰብን በዚህ ህይወት እና በዘለአለምየማጥፋት አላማ ባለው ሰይጣንና በሚከተሉት ቢጠቁም፣ እነርሱም ወደ ቤት ወደ እግዚአብሔር የሚሄዱበትን መንገድ እንዲመርጡም ይረዳሉ።

በአመጻቸው መልአኩ ለታናሹ አልማ እና ለሞዛያ ወንድ ልጆች የተናገራቸውን ቃላት ታስታውሳላችሁ፥ “እናም በድጋሚ፣ መልአኩ አለ፥ እነሆ፣ ጌታ የዚህን ህዝብ ፀሎት፣ እናም ደግሞ የአባትህን የአልማን ፀሎት ሰምቷል። አንተ ወደ እውነት እውቀትም ትመጣ ዘንድ አንተን በተመለከተ በታላቅ እምነት ፀልዮአል፤ ስለዚህ፣ ለዚህ ዓላማ የእግዚአብሔርን ኃይልና ስልጣን ለማሳመን፣ በእምነታቸው መሰረት የአገልጋዮቹ ለፀሎት መልስ ያገኝ ዘንድ ነው የመጣሁት።”14

እናንተ ለምትጸልዩትና ጌታን ለምታገለግሉት ቃል የምገባላችሁ ለራሳችሁና ለቤተሰቦቻችሁ ለማግኘት የምትመኙትን እያንዳንዱን በረከቶች ታገኛላችሁ ለማለት አይደለም። ነገር ግን አዳኝ ወደ እናንተ እንደሚቀርብ እና እናንተንና ቤተሰቦቻችሁ ጠቃሚ በሚሆነ እንደሚባርካችሁ ቃል ልገባላችሁ እችላለሁ። የእርሱ ፍቅር መፅናኛ እና ሌሎችን ለማገልገል እጆቻችሁ ስትዘረጉ እርሱ ወደ እናንተ የሚቀርብበትን መልስ ሊሰማችሁ ትችላላችሁ። እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ቁስሎች ስትጠግኑ እና በኃጢያት ስር በሀዘን ላይ ያሉትን በኃጢያት ክፍያ መጸዳትን ስታቀርቡላቸው፣ የጌታ ሀይል ይደግፋችኋል። ከእናንተ ጋር ለመርዳት እና ከቤተሰባችሁ በተጨማሪ የሰማይ አባታችንን ልጆች ለመባረክ እጆቹ ተዘርግተዋል።

በክብር ወደ ቤት መመለሻም ተዘጋጅቶልናል። ከዚያም ያፈቀርነው ጌታ ቃል ኪዳን ሲሟላ እንመለከታለን። ከእርሱ እና ከሰማይ አባታችን ጋር ወደምንኖርበት ወደ ዘለአለም ህይወት የሚቀበለንም እርሱ ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ ይህን ይህን እንደዚህ ገልጾታል።

“ፅዮንን ወደፊት ለማምጣት እና ለመመስረት ፈልግ። በነገሮች ሁሉ ትእዛዛቴን ጠብቅ።

“እናም፣ ትእዛዛቴን ብትጠብቅ እናም እስከመጨረሻው ብትጸና ከእግዚአብሔር ስጦታዎች ሁሉ ታላቅ ስጦታ የሆነውን ዘለአለማዊ ህይወት ይኖርሀል።”15

“በህይወት ያሉት ምድርን ይወርሳሉ፣ እና የሞቱትም ከሁሉም ድካሞቻቸው ያርፋሉ፣ እናም ስራዎቻቸው ይከተሏቸዋል፤ እናም ባዘጋጀሁላቸው በአባቴም ቤቶች ውስጥ አክሊልን ይቀበላሉ።”16

በመንፈስ እንዲህ የሚለውን የሰማይ አባትን ግብዣ ለመከተል እንደምንችል እመሰክራለሁ፥ “ይህ ውድ ልጄ ነው። አድምጠው!”17

በእርሱ ቃላት እና በምሳሌው፣ ክርስቶስ ወደ እርሱ እንዴት ለመቅረብ እንደምንችል አሳይቶናል። በጥምቀት በር ወደ ቤተክርስቲያኑ ለመግባት የሚመርጠው እያንዳንዱ የሰማይ አባት ልጅ በዚህ ህይወት ወንጌሉን ለመማር እና “ወደ እኔ ኑ” የሚለውን ግብዣ ከተጠሩት አገልጋዮቹ ለመስማት እድል ይኖረዋል።18

በምድር ባለው በመንግስቱ ውስጥ እና በመንፈስ አለም ውስጥ የእርሱ የቃል ኪዳን አገ፤ጋይ የሆነ እያንዳንዱም ለእርሱ ሌሎችን ሲባርኩና ሲያገለግሉ በመንፈስ የእርሱን መመሪያ ይቀበላሉ። የእርሱ ፍቅር እና ደስታ ስሜትም ወደ እርሱ በመቅረብ ይሰማቸዋል።

በኤማሁስ መንገድ በነበረ ቤት ውስጥ ከነበሩት ሁለቱ ደቀመዛሙርቶች ጋር አብሬ እንደነበርኩኝ ያህል በትንሳኤ ለተነሳው ጌታ ምስክር ነኝ። በፓልማይራ ጥሻ ውስጥ በአስደናቂው ጠዋት ብርሀን ውስጥ ጆሴፍ ስሚዝ አብንና ወልድን በማየት እንዳለው እውቀት እኔም እርሱ ህያው እንደሆነ አውቃለሁ።

ይህችም የኢየሱስ ክርስቶስ እውነተኛ ቤተክርስቲያን ናት። በፕሬዘደንትቶማስ ኤስ. ሞንሰን በተያዘው የክህነት ስልጣን ብቻ ነው እንደ ቤተሰብ ተሳስረን ከሰማይ አባታችንና ከጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ለመኖር የምንችለው። በፍርድ ቀን በአዳኝ ፊት፣ ፊት ለፊት እንቆማለን። ይህም በዚህ ህይወት እርሱን በማገልገል ወደ እርሱ ለቀረቡት የደስታ ጊዜ ይሆናል። “መልካም፥ አንተ በጎ ታማኝም ባሪያ” የሚሉትን ቃላት ማድመጥም ያስደስታል።19 ስለዚህ በትንሳኤ ስለተነሳው አዳኝ እና ቤዛችን እንደ ምስክርነት የምመሰክረው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው፣ አሜን።

አትም