2013 (እ.አ.አ)
ታዛዥነት በረከቶችን ያመጣል
ሜይ 2013


የቀዳሚ አመራር መልእክት፣ ግንቦት 2012

ታዛዥነት በረከቶችን ያመጣል

የእውነት እውቀት እና ለታላቅ ጥያቄዎቻችን መልሶች የሚመጡት ለእግዚአብሔር ትእዛዛት ታዛዥ ስንሆን ነው።

ውድ ወንድሞቼና እህቶቼ፣ በዚህ ጠዋት ከእናንተ ጋር በመሆኔ ታላቅ ምስጋና ይሰማኛል። እናንተን ለማነጋገር ያለኝን እድል ስጠቀም የእናንተን እምነትና ጸሎት እጠይቃለሁ።

በዘመናት በሙሉ፣ ወንዶችና ሴቶች ስለዚህ ስጋዊ ህይወት እና በዚህ ቦታ ስላላቸው ሀላፊነትና ስለዚህ ህይወት አላማ፣ እንዲሁም ሰላምና ደስታ ስለሚያገኙበት መንገድ እውቀትና መረጃ ለማግኘት ፈልገዋል። እንደዚህ አይነት ፍለጋ በእያንዳንዳችን ይደረጋል።

ይህ እውቀት እና መረጃ ለሰው ዘር በሙሉ የሚገኝ ነው። ዘለአለማዊ በሆኑ እውነቶች ውስጥ የተያዙ ናቸው። በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ክፍል 1 ቁጥር 39 እንደምናነበው፣ “ስለሆነም፣ እናም አስተውሉ፣ ጌታ አምላክ ነው፣ መንፈስም ይመሰክራል፣ እናም ምስክርነቱም እውነት ነው፣ እናም እውነት ከዘለአለም እስከ ዘለአለም ይኖራል።

ገጣሚው እንደጻፈው

ሰማዮች ቢሄዱም እና የምድር መንጮች ቢፈነዱም

የኑሮ ጠቅላላ ድምር የሆነው እውነት እጅግ የከፋውንም ይቋቋማል፣

ለዘለአለም፣ ዘለአለማዊ፣ የማይቀየር ነውና።1

አንዳንዶች፣ “እንደዚህ አይነት እውነት የት ነው የሚገኘው፣ እናም እንዴት ነው የምናውቀው?” ብለው ይጠይቃሉ። በከርትላንድ ኦሀዩ ፣ በግንቦት 1833 (እ.አ.አ) በነብዩ ጆሴፍ ስሚዝ በኩል በተጸጠው ራእይ ውስጥ፣ ጌታ እንዲህ አወጀ፥

“እውነት ነገሮች እንዳሉ፣ እና እንደነበሩ፣ እና ወደፊት እንደሚሆኑ ማወቅ ነው። …

“የእውነት መንፈስም እግዚአብሔር ነው። …

“እና ትእዛዛቱን ካላከበሩ በስተቀር ማንም ሰው ሙላትን አይቀበልም።

“ትእዛዛቱን የሚያከብርም፣ በእውነት እና በሁሉም ነገሮች እውቀት እስከሚከበር ያክል፣ እውነት እና ብርሀንን ይቀበላል።”2

እንዴት የሚያስገርም ቃል ኪዳን ነው! “ትእዛዛቱን የሚያከብርም፣ በእውነት እና በሁሉም ነገሮች እውቀት እስከሚከበር ያክል፣ እውነት እና ብርሀንን ይቀበላል።”

ሙሉ ወንጌል ዳግሞ በተመለሰበት በዚህ በተብራራ ዘመን እኔና እናንተ ካርታ ባልተሰራለት ባህር ወይም ምልክት በሌለው መንገድ እውነትን የምንፈልግበት ምንም ምክንያት የለም። ወዳጅ የሰማይ አባት መንገዱን በአላማ ሰርቶልናል እናም የማይወቅብንን ካርታ—ታዛዥነት ሰጥቶናል!የእውነት እውቀት እናለታላቁ ጥያቄዎቻችን መልሶች የሚመጡት ለእግዚአብሔር ትእዛዛት ታዛዥ ስንሆን ነው።

በህይወታችን በሙሉ ታዛዥነትን እንማራለን። ከልጅነታችን ጀምሮ፣ እኛን የሚንከባከቡ ደህንነታችንን ለማረጋገጥ መመሪያዎችንና ህግጋትን ይሰጡናል። እንደዚህ አይነት ህግጋትን ብናከብር ህይወት ለሁላችንም ቀላል ይሆናል። ብዙዎቻችን ግን የታዣዝነትን ጥቅም በአጋጣሚዎችን እንማራለን።

በልጅነቴ፣ በየበጋው ከሐምሌ እስከ መስከረም ቤተሰቤ በፕሮቮ ሸልቆ ውስጥ በሚገኝውው ቪቭያን ፓርክ በሽርሽር ቤታችን ውስጥ፡እንቆይ ነበር።

በእነዚይ ችግር በሌለብን ቀናት ከልብ ጓደኛዎቼ አንዱ፣ ቤተሰቡ የሽርሽር ቤት በሺሽያን ፓርክ የነበራቸው፣ ዳኒ ላርሰን ነበር። በየቀኑ እርሱ እና እኔ ልጆች ንዙ ነገር ለማድረግ የሚችሉበትን ይህን ቦታ አሳ በማጥመድ፣ ድንጋዮችንና ሌሎች ውድ ነገሮችን በመሰብሰብ እና ኮረባታዎች ላይ በመውጣት፣ እና የየቀኗን እያንዳንድ ደቂቃና ሰዓት በመደሰት እንዞርበት ነበር።

አንድ ጠዋት ዳኒና እኔ ከሌሎቹ ጓደኞቻችን ጋር እሳት እያነደድን ለመጫወት ወሰንን። በቅርብ ባለው ሜዳ ላይ ቦታ የምንሰበሰብበትን ቦታ ማዘጋጀት ነበረብን። በሳር የተሸፈነው ሜዳ የደረቀና እሾህማ ሆኖ አላማ ለነበረን አላማ የሚጠቅም አልነበረም። ትልቅ ክብ የሆነ ቦታን ለማዘጋጀት በማቀድ፣ ረጅም የሆኑትን ሳሮች ማጨድ ጀመርን። በሀይላችን በሙሉ ሳሩን መሳብ ጀመርን፣ ነገር ግን ለማጨድ የቻልነው ትንሽ አስቸጋሪ አረሞችን ብቻ ነበር። ይህ ስራ ሙሉ ቀን የሚፈጅ እንደሆነ አውቀን ነበር፣ እናም ሀይላችን እና ፍላጎታችን እየቀነሰ መጣ።

ከዚያም ለዚህ ጥሩ መፍትሄ እንደሆነ የመሰለኝ ሀሳብ ወደ ስምንት አመት አዕምሮዬ መጣልኝ። ለዳኒም እንዲህ አልኩት፣ “ማድረግ ያለብን አረሙን በእሳት ማያያዝ ነው። በሜዳው ሳር ክብ የሆነ ቦታ ብቻ እናነዳለን!” እርሱም ወዲያ ባልኩት ተስማማ፣ እናም ክብሪቶች ለማምጣት ወደ ሽርሽር ቤታችን ሮጬ ሄድኩኝ።

በስምንት አመቴ ክብሪት ለመጠቀም ፈቃድ እንደነበረኝ እንዳታስቡ፣ ዳኒ እና እኔ እነዚህን ያለመቆጣጠሪያ ለመጠቀም ፈቃድ አንዳልነበረን ግልጽ ለማድረግ እፈልጋለሁ። ሁለታችንም ስለእሳት አደጋ በተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶን ነበር። ነገር ግን፣ ቤተሰቦቼ ክብሪቶችን የት እንደሚያስቀምጡ አውቅ ነበር፣ እናም ሜዳዎችን ማጽዳት ያስፈልገን ነበር። ሌላ ሀሳብ በአዕምሮዬ ሳይገባ፣ ወደ ሽርሽር ቤታችን ሮጥኩኝ እናም ሌሎች እንደማያዩኝ በማረጋገጥ ክብሪቶችን ወሰድኩኝ። ቶሎ በአንደኛው ኪሴ ውስጥ ደበቅኳቸው።

ለችግራችን መፍትሄ በኪሴ ስላለኝ በመደሰት፣ ወደ ዳኒ በመሮጥ ተመለስኩኝ። እሳቱ እስከምንፈልገው ቦታ ድረስ ነድዶ ራሱን እንደሚያጠፋ አስብ እንደነበር አስታውሳለሁ።

ክብሪቱን ጫርኩኝ እና የደረቀውን ሳር አነደድኩት። በጋዝ እንደተተነከረ አይነት በእሳት ወዲያው ተያዘ። በመጀመሪያ ዳኒ እና እኔ ሳሩ ሲነድ በደቀት ተመለከተው፣ ነገር ግን እሳቱ በብቻው ሊጠፋ እንደማይችል አወቅን። ይህን ለማጥፋት እንደማንችል ስናውቅ፣ ደነገጥን። እሳቱም ሳሩን እያነደደ ዛፎችንና ከዚያ በኋላ ያሉትን በአደጋ ላይ እያደረሰ ወደ ተራራው ተጓዘ።

በመጨረሻም ለእርዳታ ከመሮጥ ሌላ ምንም ምርጫ አልነበረንም። ወዲያም በቭቪያን ፓርክ የነበሩት ሰዎች በሙሉ ውሀ በተነከረ አልጋ ልብሶች እሳቱን በመደብደብለማጥፋት መሯሯጥ ጀመሩ። ከብዙ ሰዓት በኋላ ቀሪው የእሳቱ ፍሞች ጠፋ። ብዙ እድሜ የነበራቸው ዛፎች እና እሳቱ ይደርስባቸው የነበሩ ቤቶች ሁሉ ዳኑ።

ዳኔ እና እኔ በዚያ ቀን አስቸጋሪ ቢሆንም አስፈላጊ የሆነ ትምህርትን ተማርን -- ከእነዚህ ታላቅ የነበረውም የታዛዥነት አስፈላጊነት ነበር።

የሰውነት ደህንነታችንን የሚጠብቁ ህግጋት አሉ። እንደዚህም፣ አስቸጋሪ የሆነውን ይህን ስጋዊ ህይወት በውጤታማነት ለመጓዝ እና በመጨረሻም ወደ ሰማይ አባታችን ለመመለስ እንድንችል ዘንድ ጌታ የመንፈስ ደህንነታችንን የሚያረጋግጡ መመሪያዎችና ትእዛዛት ሰጥቶናል።

ከመቶ አመቶች በፊት፣ በእንሥሣት መስዋዕት የማድረግ ባህል ለነበራቸው ትውልዶች፣ ሳሙኤል እንዲህ በድፋር አወጀ፥ “መታዘዝ ከመሥዋዕት፥ ማዳመጥም የአውራ በግ ስብ ከማቅረብ ይበልጣል።”3

በዚህ ዘመንም፣ ጌታ “ልብን እና መልካም ፈቃድ ያለውን አዕምሮ ይሻል፤ እናም ፈቃድ ያለው እና ታዛዡ የሆነው እርሱ በእነዚህ በመጨረሻዎቹ ቀናት የፅዮንን ምድርን በረከት ይበላሉ” በማለት ለነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ ገልጾ ነበር።4

የጥንት እና የአሁን ዘመን ነቢያት በሙሉ ታዛዥነት ለደህንነታችን አስፈላጊ እንደሆነ ያውቁ ነበር። ኔፊ “ጌታ ያዘዘኝንም ነገሮች አደርጋለሁ።”5 ስለኔፊ እንዳወጀው፣ “እሄዳለሁ፣ ጌታ ያዘዘኝንም ነገሮች አደርጋለሁ።”5ሌሎች በእምነታቸውና በታዛዥነታቸው ቢደናቀፉም፣ ኔፊ አንዴም ቢሆን ጌታ እንዲያደርቅ የጠየቀውን ባለማከናወን አልወደቀም። በዚህም ምክንያት ለመቆጠር የምይችሉ ትውልዶች ተባርከዋል።

ነፍስን የሚያነሳሳ የታዛዥነት ታሪክ የአብርሀምና የይስሀቅ ታሪክ ነው። አብርሀም ታዛዥ በመሆን፣ ውድ ልጁን ይስሀቅን ወደ ሞሪያም ምድር በመሄድ እርሱን እንደ መስዋዕት እንዲያቀርብ በጌታ የታዘዘበትን ማክረቡ እንዴት አስቸጋሪ ይሆንበት ነበር። ወደ ተመደበብት ቦታ ሲጓዝ አብርሀም ያለው ሀዘን ምን እንደሆነ ይሰማችኋልን? ይስሀቅን አስሮ፣ በመሰዊያው ላይ ሲያስተኛው፣ እናም እርሱን ለመግደል ቢላዋውን በእጁ ሲይዝ፣ ሀዘኑ ሰውነቱንና አዕምሮውን አስጨንቀዋቸው እንደነበር እርግጥ ነው። በማይወላወል እምነት እና በጌታ በፍጹም በማመን፣ የጌታን ትእዛዝ አከበረ። እንዲህ የሚለው ጥሪ እንዴት አስደናቂ ነበር ፣ እና በምን በሚያስገርም ሁኔታ መጣ፥ “በብላቴናው ላይ እጅህን አትዘርጋ፥ አንዳችም አታድርግበት፤ አንድ ልጅህን ለእኔ አልከለከልህምና እግዚአብሔርን የምትፈራ እንደ ሆንህ አሁን አውቄአለሁ።”6

አብርሀም ተፈትኖና ተሞክሮ ነበር፣ እናም ለታማኝነቱና ለታዛዥነቱ ጌታ ይህን ግርማዊ ቃል ኪዳን ሰጠው፥ “የምድር አሕዛብ ሁሉም በዘርህ ይባረካሉ፥ ቃሌን ሰምተሃልና።”7

ምንም እንኳን ታዛዥነታችንን በእንደዚህ አይነት አስገራሚና ልብ በሚስብ መንገድ እንድናረጋግጥ ባንጠየቅም፣ ታዛዥነት ከሁላችንም የሚጠበቅብን ነው።

ፕሬዘደንት ጆሴፍ ኤፍ. ስሚዝ በጥቅምት 1873 (እ.አ.አ) እንዳወጁት፣ “ታዛዥነት የሰማይ የመጀመሪያ ህግ ነው።”8

ፕሬዘደንት ጎርደን ቢ. ሒንክሊ እንዳሉት፣ “የኋለኛው ቀን ቅዱሳን ደስታ፣ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን ሰላም፣ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን እድገት፣ እና የዚህ ህዝብ ዘለአለማዊ ደህንነትና ዘለአለማዊነት የሚገኘው በእግዚአብሔርን ምክሮች ታዛዥ በመሆን ነው።”9

ታዛዥነት የነቢያት ልምድ ጸባይ ነው፤ በዘመናት በሙሉ ይህ ለእነርሱ ጥንካሬና እውቀት ሰጥቷል። እኛም ለዚህ ጥንካሬና እውቀት ምንጭ መብት እንዳለን መረጋታችን አስፈላጊ ነው። ይህም የእግዚአብሔርን ትእዛዛት ስናከብር በቀላል እያንዳንዳችን ልናገኘው የምንችል ነው።

በአመታት ሁሉ በልዩ ታማኝና ታዛዥ የሆኑ ለመቁጠር የማይቻሉ ሰዎችን አውቃለሁ። በእነርሱ ተባርኬአለሁ እናም ተነሳስቻለሁ። ከእነዚህ ስለሁለቱ ሰዎች ላካፍላችሁ።

ዋልተር ክራውስ ቤተሰብ ያለው፣ ከሁለተኛው የአለም ጦርነት በኋላ እንደ ምስራቅ ጀርመን በሚባለው ውስጥ የሚኖር የቤተክርስቲያኗ ታማኝ አባል ነበር። በነበረበት የአለም ክፍል ነጻነት ስላልነበረ ችግር ቢኖርበትም፣ ወንድም ክራውስ ጌታን የሚወድና የሚያገለግል ሰው ነበር። በታማኝነት እና በጥንቃቄ የተሰጡትን እያንዳንዱን ሀላፊነቶች ያሟላ ነበር።

ሌላው ሰውም፣ በ1911 (እ.አ.አ) በ17 አመቱ በጀርመኒ ውስጥ ተቀይሮ የተጠመቀ በሀጋሪ የተወለደ ሰው ነበር። ወዲያውም ወደ ሀንጋሪ ተመለሰ። ከሁለተኛው የአለም ጦርነት በኋላ በድብረሰን ከተማ ውስጥ እንደ እስረኛ ይኖር ነበር። በሀንጋሪም ነጻነት ተወስዶባቸው ነበር።

ወንድም ደንዶርፈርን የማያውቀው ወንድም ዋልተር ክራውስ የእርሱ የቤት ለቤት አስተማሪ እንዲሆንና በየጊዜው እንዲጎበኘው ሀላፊነት ተሰጠው። ወንድም ክራውስ አብሮ የሚያስተምረውን ጓደኛ ጠርቶ እንዲህ አለው፣ “ወንድም ዮሀም ደንዶርፈርን እንድንጎበኝ ሀላፊነት ተቀብለናል። ከእኔ ጋር በዚህ ሳምንት እርሱን ለመጎብኘት እና የወንጌል መልእክት ትችላለህን?” እና ከዚያም “ወንድም ደንዶርፈር የሚኖረው በሀንገሪ ውስጥ፡ነው” አለው።

የደነገጠው የአገልግሎት ጓደኛውም “መቼ ነው የምንሄደው?” በማለት ጠየቀ።

ወንድም ክላውስም “ነገ” ብሎ መለሰ።

“መቼ ወደ ቤት እንመለሳለን?” ብሎ ጋደኛው ጠየቀ።

ወንድም ክላውስም፣ “ምናልባት ከሳምንት በኋላ፣ —ከተመለስንም” በማለት መለሰ።

ሁለቱ አስተማሪዎች ወንድም ደንዶርፈርን ለመጎብኘት ረጅም ጉዞ በነበረው በባቡርና በአውቶቡስ ሄዱ። ወንድም ደንዶርፈር የቤት ለቤት አስተማሪዎች ከጦርነቱ በፊት ጀምሮ አልነበራቸው። አሁን፣ እነዚህን ሁለት የጌታ አገልጋዮች ሲመለከት፣ እነርሱ በመምጣታቸው የነበረው ደስታ ታላቅ ነበር። በመጀመሪያ የእነርሱን እጅ ለመጨበት እምቢ አለ። እና ወደ መኝታው ሄዶ ለብዙ አመት ያጠራቀማቸውን አስራት አመጣ። የቤት ለቤት አስተማሪዎቹም ገንዘቡን ሰጠ እናም “አሁን ለጌታ ያለኝን ሀላፊነት አከናውኛለሁ። አሁን የጌታ አገልጋዮችን እጆች ለመጨበት ብቁነት ይሰማኛል” አለ። ይህ ከቤተክርስቲያኗ ጋር ለብዙ አመት ግንኙነት ያልነበረው ታማኝ ወንድም ከነበረው ትንዝ ገቢ አስራቱን የሚከፍልበትን ማጠራቀሙ በጣም ቃላት በሌለው መንገድ እንዳስደነቀው ወንድም ክራውስ ነግረውኝ ነበር። ይህን መቼ ለመክፈል እንደሚችል ሳያውቅ ነበር ያጠራቀማቸው።

ወንድም ዋልተር ክራውስ በ94 አመታቸው ከዘጠኝ አመት በፊት ሞቱ። በህይወታቸው በሙሉ በታማኝነትና በታዛዥነት አገለገሉ እናም ለእኔና ለሚያውቋቸው በሙሉ የሚያነሳሱ ነበሩ። ሀላፊነት ሲሰጣቸው፣ ምንም አይጠይቁም፣ አያጉረመርሙም፣ እናም ለማድረግ የማይችሉበትን ምክንያት በምንም አይሰጡም ነበር።

ወንድሞቼና እህቶቼ፣ የህይወት ታላቅ ፈተና ታዛዥነት ነው። ጌታ እንዳለው፣ “ጌታ አምላክ የሚያዛቸውን ማናቸውንም ነገሮች ሁሉ እንደሚያደርጉ ለማየት፣ በዚህ እንፈትናቸዋለን።”10

አዳኝ እንዳወጀውም፥ “ከእጄ በረከት የሚያገኙም ለዚያ በረከት የተመደበውን ህግና አለም ከመመስረቷም በፊት በስራ ላይ የዋሉትን ቅድመ ሁኔታ ሊኖሩባቸው ያስፈልጋቸዋልና።”11

ከአዳኝ በላይ የሆነ የታዛዥነት ምሳሌ የለም። ስለእርሱም ጳውሎስ እንዳስመለከተው፥

“ምንም ልጅ ቢሆን፥ ከተቀበለው መከራ መታዘዝን ተማረ፤

“ከተፈጸመም በኋላ …ለሚታዘዙለት ሁሉ የዘላለም መዳን ምክንያት ሆነላቸው።”12

ፍጹም የሆነ ህይወትን በመኖር፣ የህይወቱን የተቀደሰ አላማን በማክበር የእግዚአብሔርን ፍቅር አሳይቷል። ኩራተኛም አልነበረም። በኩራት እራሱን አነፋፍቶም አልነበረምም። በምንም ታማኝ ያልነበረበትም የለም። ሁልጊዜም ትሁት ነበር። ሁልጊዜም ልባዊ ነበር። ሁልጊዜም ታዛዥ ነበር።

በታዋቂ አታላዩ፣ እንዲሁን ዲያብሎስ፣ እንዲፈተን በመንፈስ ወደ ዱር ቢመራም፣ እንዲሁም በዲያብሎስ፣ ቢፈተንም፤ ለ40 ቀን እና ለ40 ምሽት በመጾም በሰውነቱ ደካማ ቢሆንም እና “ቢራብም”፤ ግን ክፉው ኢየሱስን የሚያታልሉ እና የሚፈትኑ ቢያቀርብለትም፣ ትክክል እንደሆነ ከሚያውቀው ዞር ለማለት እምቢ በማለት የመለኮታዊ ታዛዥነት ምሳሌ ሰጠን።13

ስቃዩ እንዲህ ሆኖ “ላቡ ወደምድር የሚንጠባጠቡ ደሞች የነበሩትን”14 የሚፅናናበት የገትሰመኒ ስቃይ ሲመጣበትም፣ ታዛዥ ልጅን እንድዚህ በማለት ምሳሌ አሳየ፣ “ብትፈቅድ ይህችን ጽዋ ከእኔ ውሰድ፤ ነገር ግን የእኔ ፈቃድ አይሁን የአንተ እንጂ እያለ ይጸልይ ነበር።”15

አዳኝ የመጀመሪያ ሐዋሪያቱን እንዳስተማረው፣ እኔን እና እናንተን “ተከተሉኝ”14 በማለት ያስተምራል። 16ለመታዘዝ ፈቃደኞች ነን?

የምንፈልጋቸው እውቀቶች፣ ለምንንጓጓቸው መልሶች፣ እናም የሚቀየረው አለም ፈተናዎችን ለመቋቋም የምንፈልጋቸውጥንካሬን የእኛ ለመሆን የሚችሉት የጌታን ትእዛዛት በፈቃደኛነት ስናከብር ስንታዛዝባቸው ነው። የጌታን ቃላት እንደገናም እጠቅሳለሁ፥ “[የእግዚአብሔርን ትእዛዛት] የሚያከብርም፣ በእውነት እና ሁሉንም ነገሮች በማወቅ እስከሚከበር ድረስ፣ እውነት እና ብርሀንን ይቀበላል።”17

ለታዛዦቹ ቃል ለተገባው ብዙ ስልማቶች እንድንባረክ ትሁት ጸሎቴ ነው። በኢየሱስ ክርስቶስ፣ በጌታችንና በአዳኛችን ስም፣ አሜን።

አትም