2013 (እ.አ.አ)
የኢየሱስ ክርስቶስ መለኮታዊ ተልዕኮ፥ ፈጣሪ
ኦክተውበር 2013


የሴቶች የቤት ለቤት ጉብኝት መልእክት፣ ጥቅምት 2013 (እ.ኤ.አ)

የኢየሱስ ክርስቶስ መለኮታዊ ተልዕኮ፥ ፈጣሪ

ይህን መልእክት በጸሎት መንፈስ አጥኑ እና እንደተገቢነቱ ከምትጎበኟቸው እህቶች ጋር ተወያዩት። እህቶቻችሁን ለማጠናከር እና የሴቶች መረዳጃ ማህበርን የህይወታችሁ ተሳታፊ ክፍል እንዲሆን እንዲረዳችሁ ጥያቄዎቹን ተጠቀሙባቸው። ለተጨማሪ መረጃ ወደ reliefsociety.lds.org ሂዱ።

እምነት • ቤተሰብ • እርዳታ

ኢየሱስ ክርስቶስ “ሰማያትን እና ምድርን ፈጠረ” (3 ኔፊ 9፥15) ይህን ያደረገው በዘላለማዊ አባታችን ምሬት ስር በክህነት ሀይል በኩል ነው (ሙሴ 1፥33 ተመልከቱ)።

“የመፈተኛ ጊዜ፣ እግዚአብሔር እኛ እንድንቀበል ላዘጋጀው ሁሉ ብቁ መሆናችንን ለራሳችን የምናረጋግጥበት እድል እንዲያጋጥመን፣ ብልህ ፈጣሪ ምድርን አስውቦ እና እኛን እዚህ በማኖሩ ምን ያህል አመስጋኞች መሆን አለብን” አሉ ፕሬዘዳንት ቶማስ ኤስ. ሞንሰን።1 የእግዚአብሔርን ትእዛዛት ለመጠበቅ እና ንስሀ ለመግባት ነጻ ምርጫችንን ስንጠቀምበት፣ ተመልሶ ከእርሱ ጋር ለመኖር ብቁ እንሆናለን።

ስለ ፍጥረት፣ ፕሬዘዳንት ዴይተር ኤፍ. ኡክዶርፍ፣ በመጀመሪያ አመራር ውስጥ ሁለተኛ አማካሪ፣ እንዲህ አሉ፥

“ሁለንተናን የፈጠረበት ምክንያት እኛ ነን! …

“ይህም ስለሰው የሚያምታታው ነገር ነው፥ ከእግዚአብሔር ጋር ሲነጻጸር፣ ሰው ምንም አይደለም፤ ነገር ግን እኛ ለእግዚአብሔር ሁሉም ነገሮች ነን።2 እኛ ለሰማይ አባታችን ሁሉም ነገር በመሆናችን ምክንያት ኢየሱስ ክርስቶስ ምድርን ለእኛ መፍጠሩን ማወቃችን ለእነርሱ ያለን ፍቅር እንዲጨምር ይረዳናል።

ከቅዱሳት መጻህፍት

ዮሀነስ 1፥3; ዕብራውያን 1፥1–2ሞዛያ 3፥8ሙሴ 1፥30–33፣ 35–39አብረሀም 3፥24–25

ከታሪካችን

በእግዚአብሔር አምሳል ተፈጥረናል (ሙሴ 2፥26–27 ተመልከቱ)፣ እና እኛ መለኮታዊ አቅም አለን። ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በሴቶች መረዳጃ ማህበር ያሉ እህቶች “እንደየመብታዊ ነጻነታቸው እንዲኖሩ” መክሯል።3 በዚያ ማበረታቻ እንደ መሰረት በመጠቀም፣ በየኋለኛው ቀን ቅዱሳን ቤተክርስቲያን ውስጥ ያሉ እህቶች እግዚአብሔር ለእነርሱ ያለውን አላማ በሟሟላት እንደ መለኮታዊ አቅማቸው እንዲኖሩ ተምረዋል። “በትክክል ማን እንደሆኑ—ለማፍቀር እና ለመንከባከብ በተፈጥሮአዊ ችሎታ ያላቸው የእግዚአብሔር ሴት ልጆች፣—ሲረዱ፣ እንደ ቅዱስ ሴቶች አቅማቸው ላይ ይደርሳሉ።”4

“አሁን እናንተ እግዚአብሔር በውስጣቹ በተከለው ርህራሄዎች መሰረት ልትንቀሳቀሱ ወደ ምትችሉበት ሁኔት ተደርጋችኋል፣” አለ ነብዩ ጆሴፍ ስሚዝ። “እንዴት ታላቅ እና ክብራማ ነው እናንተ እንደ እነዚህ መርሆች መሰረት ከኖራችሁ!—በመብታዊ ነጻነታቸው መሰረት ከኖራችሁ፣ መላእክት የእናንተ ጓደኞች ለመሆን አይከለከሉም።”5

ማስታወሻዎች

  1. Thomas S. Monson, “The Race of Life፣” Liahona፣ ግንቦት 2012፣ 91።

  2. ዴይተር ኤፍ. ኡክዶርፍ፣ “You Matter to Him,” Liahona, 2011፣ 20።

  3. ጆሴፍ ስሚዝ፣ በ Daughters in My Kingdom: The History and Work of Relief Society ውስጥ (2011)፣ 171።

  4. Daughters in My Kingdom፣ 171።

  5. ጆሴፍ ስሚዝ፣ Daughters in My Kingdom, 169።

ምን ማድረግ እችላለሁ?

  1. መለኮታዊ ተፈጥሮአችንን ለመረዳት መፈለግ እንዴት ነው ለአዳኝ ያለንን ፍቅር የሚጨምረው?

  2. ለእግዚአብሄር ፍጥረቶች ምስጋናችንን እንዴት ነው ለማሳየት እንችላለን?