2013 (እ.አ.አ)
ኑ ከእኛ ጋር አንድ ሁኑ
ኖቬምበር 2013


የሴቶች የቤት ለቤት መልእክት፣ ህዳር 2013

ኑ ከእኛ ጋር አንድ ሁኑ

ጉዳዮቻችሁ፣ የግል ታሪኮቻችሁ፣ ወይም የምስክራችሁ ጥንካሬ ምንም ቢሆኑም፣ በቤተክርስቲያኗ ለእናንተ ክፍል አላችሁ።

አንድ ጊዜ የአለም ሀይማኖቶች በተሰበሰቡበት አዳራሽ ውስጥ እንደሚገኝ ህልም የነበረው አንድ ሰው ነበር። እያንዳንዱ ሀይማኖት ተፈላጊና ብቁ የሆኑ ብዙ ነገሮች እንዳሉት መሰለው።

የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያንን የሚወክሉ ሰዎችን አገኘና እንዲህ ሲል ጠየቀ፣ “እናንተ ከአባላቶቻችሁ ምን ትጠይቃላችሁ?”

እኛ ምንም አንጠይቅም፣” ብለው መለሱ። “ነገር ግን ጌታ ሁሉንም እንድንቀድስ ይጠይቀናል።”

ሰዎቹም ስለቤተክርስቲያኗ ጢ፣ ስለ ቤት ለቤት ጉብኝት እና ስለሴቶች የቤት ለቤት ጉብኝት፣ ስለሙሉ ጊዜ ሚሲዮን፣ ስለየሳምንት የቤተሰብ የቤት ምሽት፣ ስለቤተመቅደስ ስራ፣ ስለ በጎ ድርገት አገልግሎቶች፣ እና ለማስተማር ስለሚመደቡበት ገለጹለት።

“ለሚሰሩት ስራዎች ሁሉ ሰዎቻችሁን ትከፍሏችዋላችሁን?” ብሎ ሰውየው ጠየቀ።

“አይደለም፣” ሰዎቹ ገለጹ። “ጊዜአቸውን በነጻ ነው የሚሰጡት።”

ሰዎቹም ቀጥለው፣ “ደግሞም በየስድስት ወርም የቤተክርስቲያን አባላቶቻችን ወደ አጠቃላይ ጉባኤ ስብሰባ ለአስር ሰዓት ለመሳተፍ ይሄዳሉ ወይም ያዳምጣሉ።”

“ለአስር ሰዓት ሰዎች የሚናገሩበት?” በማለት ሰውየው ተደነቀ።

“የየሳምንቱስ የቤተክርስቲያን አገልግሎቶችስ? ምን ያህል ረጅም ናቸው?”

‘በእያንዳንዱ እሁድ ለሶስት ሰዓት!”

“ሰውየውም “ወየው” አለ። የቤተክርስቲያን አባላቶቻችሁ እንዳላችሁት በእርግጥ ያደርጋሉን?”

“ያንንም እና ተጨማሪም። “የቤተሰብ ታሪክን፣ የወጣቶች ሰፈራን፣ የሀይማኖት ስብሰባዎችን፣ የቅዱስ መጻህፍት ጥናትን፣ የአመራር ስልጠና፣ የወጣቶች መሳተፊያዎችን፣ የጠዋት ሰምነሪን፣ ቤተክርስቲያኗን መንከባከብን ገና አልጠቀስንም፣ እናም የጌታ የጤንነት ህግጋት፣ ድሆችን ለመርዳት በየወሩ የሚጾምበት፣ እና አስራትም አለ።”

ከዚያም ሰውየም አለ፣ “አሁን ግራ ተጋባሁ። ማንም ሰው ለምን የእንደዚህ አይነት የቤተክርስቲያናችሁ አባል ለመሆን ይፈልጋል?”

ሰዎቹም ፈገግ አሉና፣”ይህን የማትጠይቅ መስሎን ነበር” አሉት።

ማንኛውም ሰው ለምን የእንደዚህ አይነት ቤተክርስቲያን አባል ይሆናል?

በአለም አቀፍ የሚገኙ ቤተክርስቲያኖች በቁጥር እየቀነሱ በሚገኙበት ጊዜ፣ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን፣ ከብዙዎቹ በቁጥር ትንሽ ብትሆንም፣ በአለም ከሚገኙ ቤተክርስቲያኖች በፍጥነት የምታድግ ናት። በመስከረም 2013 (እ.አ.አ) ጀምሮ ቤተክርስቲያኗ በአለም ውስጥ 15 ሚልዮን አባላት አላት።

ለዚህ ብዙ ምክንያቶች አሉ፣ ነገር ግን አንዳንዶችን ላቀርብ እችላለሁን?

የአዳኝ ቤተክርስቲያን

መጀመሪያ፣ ቤተክርስቲያኗ በዚህ በዘመናችን በዳግም የተመለሰችው በኢየሱስ ክርስቶስ ነው። በዚህም በስሙ የመስራት ፣ እንዲሁም ለኃጢያት ስርየት ለመጥመቅ፣ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታን ለመስጠት፣ እና በምድር እና በሰማይ ለማተም፣ ስልጣንን ታገኛላችሁ።1

የዚህ ቤተክርስቲያን አባል የሚሆኑ አዳኝ ኢየሱስ ክርስቶስን ያፈቅራሉ እናም እርሱን ለመከተል ይፈልጋሉ። እግዚአብሔር ለሰው ዘር እንደገና እንደሚናገር ባላቸው እውቀትም ይደሰታሉ። የቅዱስ ክህነት ሹመትን ሲቀበሉ እና ከእግዚአብሔር ጋር ቃል ኪዳን ሲገቡ፣ በህይወታቸው የእርሱ ሀይል ይሰማቸዋል።2 ወደ ቅዱስ ቤተመቅደስ ሲገቡ፣ በእርሱ ፊት እንደሚገኙ ይሰማቸዋል። ቅዱሳት መጻህፍትን ሲያነቡ3 እናም በእርሱ ነቢያት ትምህርት ሲኖሩም፣ በጣም ከሚያፈቅሩት አዳኛቸው ጋር ቅርብ ይሆናሉ።

ንቁ እምነት

ሌላው ምክንያትም ቤተክርስቲያኗ መልካም ለማድረግ እድል መስጠቷ ነው።

በእግዚአብሔር ማመን ሙገሳ የሚያስፈልገው ነው፣ ነገር ግን አብዛኛው ሰዎች ከሚያነሳሳ ስብከቶች ወይም ከበላይ ከሚገኙት ቤቶች ለማዳመጥ በላይ ነው የሚፈልጉት።4 እምነታቸውን ወደስራ ለመለወጥ ይፈልጋሉ። እጅጌአቸውን ጠቅልለው በታላቅ ስራ ለመሳተፍ ይፈልጋሉ።

ከእኛ ጋር አንድ ሲሆኑ የሚደርሰውም ይህ ነው— ችሎታዎቻቸውን፣ ርህራሄአቸውን፣ እና ጊዜአቸውን ወደ መልካም ስራ ለመቀየር ብዙ እድሎች ይኖሯቸዋል። በአለም አቀፍ ጉባኤዎቻችን ውስጥ የሚከፈላቸው መሪዎች ስለሌሉን፣ የአገልግሎት ስራዎችን አባላቶቻችን ያከናውኑታል። በመነሳሳት የተጠሩ ናቸው። አንዳንዴ በገዛ ፈቃደኞች ነን፤ አንዳንዴም ለእኛ ፈቃደኛነታችንን ሌሎች ይናገሩልናል ሀላፊነቶችን እንደ ሸከም ሳይሆን እግዚአብሄርን እና ልጆቹን ለማገልገል በደስታ የገባናቸውን ቃል ኪዳኖች እንደምናሟላበት እድሎች እናያቸዋለን።

እንደ ሀብት የምንመለከታቸው በረከቶች

ሰዎች የቤተክርስቲያኗ አባላት የሚሆኑበት ሶስተኛው ምክንያትም የደቀመዛሙርት መንገድን መከተል ውድ ወደሆኑ በረከቶች ስለሚመሩ ነው።

ጥምቀትን በደቀ መዛሙርትነት ጉዞአችን እንደመጀመሪያ ቦታ እንመለከታለን። ከኢየሱስ ክርስቶስጋር በየቀኑ የምንራመደው በዚህ ህይወት ወደ ሰላም እና አላማ እናም በሚመጣው አለምም ወደ ታላቅ ደስታና ዘለአለማዊ ደህንነት ይመራል።

ይህን መንገድ በታማኝነት የሚከተሉ ብዙ ጉድጓዶችን፣ ሀዘኖችን፣ እና በህይወት ጸጸቶችን ያስወግዳሉ።

በመንፈስ ደሀ እና በልብ ታማኝ የሆነ በዚህ ታላቅ የእውቀት ሀብቶችን ያገኛሉ።

የሚሰቃዩ ወይም የሚያዝኑም መፈወሻን በዚህ ያገኛሉ።

በኃጢያት ሸከም ያላቸውም ምህረትን፣ ነጻነትን፣ እና እረፍትን ያገኛሉ።

ከተሳታፊነት ለሚርቁ

የእውነት ፍለጋ ብዙ ሚልዮን የሚሆኑ ሰዎችን ወደኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶች ቤተክርስቲያን መርቷቸዋል። ነገር ግን፣ አንድ ጊዜ ያፈቅሯት የነበረችውን ቤተክርስቲያን ትተው የሚሄዱ አንዳንዶች አሉ።

አንድም እንዲህ ይጠይቃል፣ “ወንጌል እንደዚህ አስደናቂ ከሆነ፣ ለምንድን ነው ሰው ይህን ትተውት የሚሄዱት?”

አንዳንዴ እነርሱ ተከፍተዋል ወይም ሰነፍ ወይም ኃጢያተኛ በመሆናቸው ነው ብለን እናስባለን። በእርግጥ ይህ እንዲህ ቀላል አይደለም። በእርግጥም ለተለያዩ ጉዳዮች ለመጠቀም የሚቻል አንድ ምክንያት የለም።

አንዳንድ አባላት እራሳቸውን ከቤተክርስቲያኗ ለመለየት እንደሚገባቸው ባላቸው ጥያቄ ለብዙ አመታት ይታገላሉ።

ጥያቄንበጠየቀ እና መልስን በፈለገ ወጣት ሰው በዳግም የተመለሰችው የግል ነጻ ምጫን በጣም በምታከብር በዚህች ቤተክርስቲያን ውስጥ በታማኝነት እውነትን የሚፈልጉትን እናከብራለን። ከምናፈቅራት ቤተክርስቲያን እና ካገኘነው እውነት ወጥተው ሲሄዱ ልባችን ይሰበራል፣ ነገር ግን ሁሉን ቻይ እግዚአብሔርን፣ ልክ እኛ መመብት በምናደርገው፣ በህሊናቸው ውሳኔ መሰረት ለማምለክ ያላቸውን መብት እናከብራለን።5

ያልተመለሱ ጥያቄዎች

አንዳንዶች ከዚህ በፊት በተባሉት ወይም በተደረጉት ላይ ባላቸው ያልተመለሱ ጥያቄዎች ይታገላሉ። በቤተክርስቲያኗ ታሪክ 200 አመታት ውስጥ ካልተቋረጠ ከተነሳሱ፣ ከተከበሩ፣ እና መለኮታዊ ከሆኑ ድርጊቶች ጋር ሰዎች ጥያቄ እንዲኖራቸው የሚያደርጉ የተባሉ እና የተደረጉ ነገሮች እንዳሉ በግልጽ እንቀበላለን።

አንዳንዴ መረጃዎች በሙሉ ስለሌሉን እና ትንሽ ትዕግስት ስለሚያስፈልገን ጥያቄዎች ይነሳሉ። ሁሉም እውነት በመጨረሻ ሲታወቅ፣ ከዚህ በፊት የማይገቡን ነግሮች በሚያረካን መንገድ መፍትሄ ያገኛሉ።

አንዳንዴ “ተጨባጭ ነገር” ምን እንደሆነ ያለ የተለያየ አስተሳሰብ ይገኛል። በአንዳንዶች ጥርጣሪን የሚያመጣው ጥያቄ፣ በጥንቃቄ ከተመረመረ በኋላ በሌሎች እምነትን ይገነባል።

ፍጹም ያልሆኑ ሰዎች ስህተቶች

በግልጽ ለመናገር፣ አባላት ወይም የቤተክርስቲያኗ መሪዎች ስህተት ያደረጉበት ጊዜ አለ። ከመሰረታዊ መርሆቻችን፣ ከመሰረቶቻችን፣ ወይም ከትምህርታችን ጋር የማይስማሙ ነገሮች ተብለው ወይም ተደርገው ይሆናል።የተባሉ ወይም የተደረጉ

ቤተክርስቲያኗ ፍጹም የምትሆነው ፍጹም በሆኑ ሰዎች ከተመራች ነው። እግዚአብሔር ፍጹም ነው፣ ትምህርቶቹም ንጹህ ነው። ነገር ግን —የእርሱ ፍጹም ባልንነው ልጆቹ — በኩል ይሰራል እናም ፍጹም ያልሆኑ ሰዎች ስህተት ይሰራሉ።

በመፅሐፈ ሞርሞን መግቢያ ገጽ ላይ ይህን እናነባለን፣ “እስከማሳመን—እና አሁን፣ ስህተቶች ካሉ ስህተቶቹ የሰዎች ስህተቶች ናቸው፣ ስለዚህ፣ በክርስቶስ የፍርድ ወንበር ያለ እንከን ትሆኑ ዘንድ የእግዚአብሔር የሆኑትን አትኮንኑ።”6

ይህም ሁልጊዜ እንደነበረበት ነው እናም ክርስቶስ በምድር ላይ ለመነገስ እራሱ እስከሚመጣበት ፍጹም ጊዜ ድረስ እንዲህም ይሆናል።

በሚያሳዝን ሁኔታ ግን አንዳንዶች በሰዎች በተሰሩ ስህተቶች ምክንያት ተደናቅፈዋል። ነገር ግን ይህ ቢሆንም፣ በኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ውስጥ የሚገኘው ዳግም የተመለሰው ዘለአለማዊው እውነት አይደበዝዝም፣ አይቀነስም፣ ወይም አይጠፋም።

እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ እና የቤተክርስቲያኗን ሸንጎና ስራዎች በቅርብ እንደተመለከተ ሰው፣ ይህችን ቤተክርስቲያን ወይም አባላቷን በጥብቅ የሚነካ ምንም ነገር ውሳኔ መነሳሻ፣ መመሪያ፣ እና ድጋፍ በቅንነት ሳይፈለግበት የማይደረግ እንደሆነ በጥብቅ እመሰክራለሁ። ይህች የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ናት። ቤተክርስቲያኑ ከተመደበላት መንገድ ያለ አላማ እንድትጓዝ ወይም መለኮታዊ እጣ ፈንታዋን ለማከናወን እንድትወድቅ እግዚአብሔር አይፈቅድም።

ለእናንተም ክፍል አለ።

ከቤተክርስቲያኗ እራሳቸውን ለሚለያዩ ሁሉ፣ እንዲህ እላለሁ፣ ውድ ጓደኞቼ፣ በዚህ ለእናንተ ቦታ አለ።

ነ እናም ችሎታችሁን፣ ስጦታችሁን፣ እና ሀይላችሁን ጨምሩ። በዚህም ምክንያት የተሻልን እንሆናለን።

አንዳንዶችም እንዲህ ይጠይቃሉ,“ግን ስለጥርጣሬዎቼስ?”

ጥያቂ መኖር ከፍጥር የመጣ ነው— የታማኝ ጥያቄ ፍሬ በአብዛኛው ጊዜ ወደ ታላቅ መረጃ ዛፍ ያድጋልም ይጎለምሳልም። በአንድም ጊዜ ይሁን በሌላ፣ በጥብቅ ወይም ከስሜት በሚመጣ ጥያቄ የሚታገሉ ጥቂት የቤተክርስቲያኑ አባላት አሉ። ከቤተክርስቲያኗ አላማዎች አንዱ የእምነት ፍሬን መንከባከብ እና ማሳደግ ነው—ይህም የሚደረገው አንዳንዴ በጥርጣሬ አሸዋማ አፈር ውስጥ ነው። እምነት የሚታዩ ባይሆኑም እውነት በሆኑ ነገሮች ላይ ተስፋ የሚጣልበት ነው።7

ስለዚህ፣ ውድ ወንድሞቼና እህቶቼ—ውድ ጓደኞቼ— እባካችሁ፣ መጀመሪያ እምነታችሁን ከመጠራጠራችሁ በፊት ጥርጣሬያአችሁን ተጠራጠሩ።8 ጥርጣሬ እንደ እስረኛ እንዳይዘን እና በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል የሚመጡት ከመለኮታዊ ፍቅር፣ ሰላም፣ እና ስጦታዎች እንዳናገኝ እንዳያደርገን በምንም መፍቀድ አይገባንም።

አንዳንዱም እንዲህ ሊል ይችላል“በቤተክርስቲያኗ ውስጥ ከእናንተ ጋር የምጣጣም አይመስለኝም

ልባችን ውስጥ ለመመልከት ብትችሉ፣ ከምታስቡት በላይ ከእኛ ጋር አንድ እንደሆናችሁ ታገኛላችሁ። እኛ እንደ እናንተ አይነት ጉጉቶች እና ችግሮች እናም ተስፋዎች እንዳሉን በማወቅ ትደለቃላችሁ። የእናንተ የድሮ ህይወት ወይም አስተዳደግ የኋለኛውቀ ቅዱሳን ናቸው ብላችሁ ከምታስቡበት የተለየ ይመስላል፣ ነገር ግን ያም በረከት ሊሆን ይችላል። ወንድሞችና እህቶች፣ ውድ ጓደኞች፣ የእናንተን ልዩ ችሎታ እና አስተያየት ያስፈልጉናል። የሰው እና በአለም አቀፍ ያሉ ህዝቦች ልዩነት ከቤተክርስቲያኗ ጥንካሬ ነው።

አንዳንዶች እንዲህ ይላሉ “በእናንተ መሰረታዊ መርሆች ለመኖር የምችል አይመስለኝም

ይህም ከሁሉም ይበልጥ ልትመጡበት የሚገባው ምክንያት ነው። ቤተክርስቲያኗ ፍጹም ያልሆኑትን፣ የሚታገሉትን፣ እና የደከሙትን ለመንከባከብ የተነደፈች ነች። ገና እነዚህን ያላሸነፏቸው ቢሆንም፣ በልባቸው በሙሉ ትእዛዛትን ለመጠበቅ ፍላጎትባላቸው ሰዎች የተሞላች ነች።

አንዳንዶች እንዲህ ይላሉ “ግብዝ የሆነ የቤተክርስቲያኗ አባልን አውቃለሁ እንደ እርሱ አይነት አባል ካለው ቤተክርስቲያን ውስጥ አባል መቼም አልሆንም

ግብዝነትን በሚያምንበት ወይም በምታምንበት ሁኔታ ፍጹም በሆነ ሁኔታ ለመኖር እንደወደቀ ትርጉም የምታስቡት ከሆነ፣ ሁላችንም ግብዞች ነን። ማንኛችንም እንደ ክርስቶስ አይነት መሆን እንዳለብን እንደምናውቀው አይደለንም። ነገር ግን ስህተቶቻችንን እና ኃጢያት ለመስራት ያለን ጸባያችንን ለማሸነፍ የልብ ፍላጎት አለን። በልባችን እና በነፍሳችን ከኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ እርዳታ ጋር የተሻለ ለመሆን እንጥራለን።

እነዚህ የእናንተ ፍላጎቶች ከሆኑ፣ ጉዳዮቻችሁ፣ የግል ታሪካችሁ፣ ወይም የምስክራችሁ ጥንካሬ ምንም ቢሆኑ፣ ለእናንተ በዚህች ቤተክርስቲያን ክፍል አላችሁ። ኑ ከእኛ ጋር አንድ ሁኑ!

ኑ ከእኛ ጋር ተቀላቀሉ!

እንደ ሰው ፍጹም ባንሆንም፣ አለም ልታቀርባቸው ከምትችላቸው መልካም ነፍሳት ብዙዎቹን በዚህች ቤተክርስቲያን አባላት ውስጥ ለማግኘት እንደምትችሉ እርግጠኛ ነኝ። የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ደጉን እና የሚንከባከበውን፣ ታማኙን እና ትጉህ የሆነውን የምትስብ ይመስላል።

ፍጹም የሆኑ ሰዎችን ለማግኘት ከጠበቃችሁ፣ ትበሳጫላችሁ። ነገር ግን ንጹህ የክርስቶስ ትምህርትን፣ “የቆሰለ ነፍስን የሚፈውስ”9 የእግዚአብሔርን ቃል እና የሚቀድስ የመንፈስ ቅዱስ ተፅዕኖን የምትፈልጉ ከሆነ፣ በዚህም እነዚህን ታገኛላችሁ። በዚህ በሚቀንሰው እምነት ዘመን— ብዙዎች ከሰማይ እቅፍ እየራቁ እንዳሉ በሚመስለው ዘመን— ልክ እንደ እናንተ እግዚአብሔርን እና ሰዎችን በማገልገል አዳኝን ለማወቅ እና ወደ እርሱ ለመቅረብ የሚጓጉ ሰዎችን ታገኛላችሁ። ኑ፣ ከእኛ ጋር ተቀላቀሉ!

እናንተ ደግሞ ልትሄዱ ትወዳላችሁን?

በአዳኝ ህይወት ውስጥ ብዙ ሰዎች ትተውት ስለሄዱበት ጊዜ አስታውሳለሁ።10 ኢየሱስ አስራ ሁለት ሐዋሪያቱን እዲህ ብሎ ጠየቃቸው፥

“እናንተ ደግሞ ልትሄዱ ትወዳላችሁን?”

“ስምዖን ጴጥሮስም መልሶ፣ ጌታ ሆይ፥ ወደ ማን እንሄዳለን? አንተ የዘላለም ሕይወት ቃል አለህ።”11

እኛም እንደዚህ አይነት መልሶች ለዚህ አይነት ጥያቄ መመለስ ያለብን ጊዜዎች አሉ። እኛ ደግሞ ልንሄድ እንወዳለን? ወይም እንደ ጴጥሮስ የዘላለም ሕይወት ቃልን አጥብቀን እንይዛለን?

እውነትን፣ ትርጉምን፣ እና እምነትን ወደ ስራ የሚቀየርበት መንገድ ከፈለጋችሁ፤ የሚስማማችሁ ቦታ የምትፈልጉ ከሆናችሁ፥ ኑ፣ ከእኛ ጋር አንድ ሁኑ!

ያቀፋችሁን እምነት ትታችሁ የሄዳችሁ ከሆናችሁ፥ ተመለሱ። ከእኛ ጋር ተቀላቀሉ!

ተስፋ ለመቁረጥ ከተፈተናችሁ፥ ለጥቂት ጊዜ ቆዩ። እዚህ ለእናንተ ክፍል አለላችሁ።

እነዚህን ቃላት ለሚሰሙ እና ለሚያነቡ ሁሉ እንዲህ እለምናችኋለሁ፥ ኑ፣ ከእኛ ጋር አንድ ሁኑ! የደጉ ክርስቶስን ጥሪ አድምጡ። መስቀላችሁን አንሱ እና ተከተሉት።12

ኑ፣ ከእኛ ጋር አንድ ሁኑ! በዚህም ዋጋ ካለው በላይ ምን ውድ እንደሆነ ታገኛለችሁ።

የዘለአለም ቃልን፣ የተባረከ ቤዛነት ቃል ኪዳንን፣ እና የሰላምና የደስታ መንገድን እንደምታገኙ እመሰክራለሁ።

ለእውነት የምትፈልጉበት በልባችሁ ውስጥ መጥታችሁ ከእኛ ጋር አንድ እንድትሆኑ ፍላጎት እንዲሰጣችሁ እጸልያለሁ። በቅዱሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።

አትም