2013 (እ.አ.አ)
አልጥልህም፥ አልተውህም
ኖቬምበር 2013


የቀዳሚ አመራር መልእክት፣ ህዳር 2013 (እ.ኤ.አ)

“አልጥልህም፥ አልተውህም”

 … የሰማይ አባታችን የሚያጋጥሙንን ፈተናዎች ስንቋቋምና ስንድናቸው በእነርሱም ለመማር፣ ለማደግና፣ ለመጠናከር እንደምንችል ያውቃል።

በዚህ ምሽት በማስታወሻዬ ውስጥ እንዲህ ብዬ እጽፋለሁ፣ “ይህ ከተካፈልኳቸው አጠቃላይ ጉባኤዎች ውስጥ ሁሉ የኸኛው ከሁሉም በላይ የሚያነሳሳ ነው። ሁሉም ነገሮች ከሁሉም ታላቅ እና የመንፈሳዊ ጉዳዮች ነበሩ።”

ወንድሞችና እህቶች፣ ከስድስት ወር በፊት በዚህ አጠቃላይ ጉባኤ ስንገናኝ፣ ውድ ባለቤቴ ፍራንሲስ በአደገኛ ሁኔታ ወድቃ በሆስፒታል ተኝታ ነበር። በግንቦት ጉዳቷን ለማሸነፍ ከታገለች በኋላ፣ ወደ ዘለአለም ሄደች። የእርሷ ሞት ከባድ ነበር። እርሷ እና እኔ በጥቅምት 7 ቀን 1948 ዓ.ም በሶልት ሌክ ቤተመቅደስ ተጋብተን ነበር። ነገ የተጋባንበት 65 አመትን እናከብር ነበር። እርሷ የህይወቴ ፍቅር፣ የማምናት፣ እና ቅርብ ጓደኛዬ ነበረች። ትናፍቀኛለች ብዬ ብናገር የእኔን ስሜት የሚገልጽ አይደለም።

ይህ ጉባኤ በፕሬዘደንት ዴቪድ ኦ መኬይ እንደ አስራ ሁለት ሐዋርያ የተጠራሁበት 50 አመት ይማከብርበት ነው። በእነዚህ አመቶች በሙሉ የውድ ጓደኛዬን ሙሉ እና ፍጹም ድጋፍ ተሰምቶኛል ። ጥሪዬን እንዳከናውን ያደረገችው መስዋዕቶች መቆጠር አይቻሉም። ከእርሷ እና ከልጆቹ ለብዙ ቀናትና አንዳንዴም ሳምንታት በመራቅ በሀላፊነት የተሰጠኝን ሳከናውን በምንም የቅሬታ ቃል ከእርሷ ሰምቼ አላውቅም። በእርግጥም መልዓክ ነበረች።

ፍራንሲስ ከሞተች በኋላ ለእኛ ለነበረው ምክር የእኔንና የቤተሰቤን ምስጋና ለማቅረብ እፈልጋለሁ። ብዙ መቶ ካርዶችና ደብዳቤዎች ለእርሷ ያላቸውን አድናቆት በመግለጽ እና ለቤተሰባችንም የሀዘን መግለጫን ተልከውልን ነበር። ብዙ ደርዘን የአበባ ቅንብሮችን ተቀብለናል። በእርሷ ስም ለቤተክርስቲያኗ አጠቃላይ የሚስዮን ገንዘብ በበጎ ድርጊት ለተሰጡትም እርዳታዎች አመስጋኝ ነን። ትታን በሄደችው ሰዎች ስምም፣ በልብ ከመጣውና ለደግ ቃላቶቻችሁም ታልቅ ምስጋና አቀርባለሁ።

በዚህ በመለያየታችን ጊዜ ለእኔ ከፍተኛ ምቾት ይሰጠኝ የነበረው ስለኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ያለኝ ምስክርነት እና ውዷ ፍራንሲስ ህያው እንደሆነች በማወቄ ነው። መለያየታችን ጊዜአዊ እንደሆነ አውቃለሁ። በምድር እና በሰማይ ውስጥ ለማስተሳሰር ስልጣን በነበረው ሰው በእግዚአብሔር ቤት እንደተሳሰርን አውቃለሁ። አንድ ቀን እንደገና እንደምንገናኝ እና በፍጹም እንደገና እንደማንለያይ አውቃለሁ። ይህም እውቀት ይደግፈኛል።

ወንድሞችና እህቶች፣ ማንም ሰው ሀዘን እና ስቃይ ሳያገኝ አይኖርም ለማለት አይቻልም፣ ወም በሰው ዘር ታሪክ ውስጥ መተራመስና መሰቃየት ያልነበረበት ጊዜ የለም።

የህይወት መንገድ ወደ መጥፎ ሁኔታ ሲዞር፣ “ለምን እኔን?” የሚል ጥያቄ ለመጠየቅ መገፋፋት ይኖራል። አንዳንዴ ችግሩ መጨረሻ የሌለው ይመስላል፣ ጨለማውን የሚያጠፋ የጸሀይ ብርሀን ያለም አይመስልም። በተሰበረ አላማ ተስፋ በቆረጥ እና በጠፉ ተስፋዎች ፍርሀት ምክንያት እንደተከበብን ይሰማንል። በመፅሐፍ ቅዱስ ያለምንም ልመና እንዲህ እንደግማለን፣ “በገለዓድ የሚቀባ መድኃኒት የለምን?”1 እንደተረሳን፣ ልባችን እንደተሰበረ፣ እና ብቸኛ እንደሆንን ይሰማናል። የግል መጥፎ እድላችንን መጥፎ ሀሳብ ባለበት አስተያየት እንመለከተዋለን። በአብዛኛው ጊዜ የሰማይ ትዕግስት እንደሚያስፈልግ እየረሳን፣ ለችግራችን መፍትሄ ለማግኘት እንቸኩላለን።

የሚመጡብን ችግሮች ለመፅናት ያለንን ችሎታ ይፈትኑልናል። በእያንዳንዳችን መመለስ ያለ መሰረታዊ ጥያቄም አለ፥ ልደናቀፍ፣ ወይስ ልፈፅም? አንዳንዶች ከፈተናቸው በላይ ከፍ ለማለት በማይችሉበት ምክንያት ይደናቀፋሉ። አንዳንዶች ፈተናቸውን ለመቋቋም ባለመቻላቸው እየተደናቀፉ ይገኛሉ። ለመፈጸም እስከ ህይወት መጨረሻ ድረስ መፅናትን ያስፈልገዋል።

የሚደርሱብንን ነገሮች ስናስብባቸው፣ ከጥንቱ ኢዮብ ጋር “ሰው እንዲሁ ለመከራ ተወልዶአል” እንላለን።2 ኢዮብ “ፍጹምና ቅን፥ እግዚአብሔርንም የሚፈራ፥ ከክፋትም የራቀ”3 ሰው ነበር።3 በሚያደርገው ጻድቅ፣ በንብረቱ ሀብታም የነበረው ኢዮብ ማንንም ሰው ሊያጠፋ ይችል የነበረ ፈተና አጋጠመው። ንብረቶቹን አጥቶ፣ በጓደኞቹ ተሰድቦ፣ ተሰቃይቶ፣ ቤተሰቡን በማጣት አዝኖ፣ “እግዚአብሔርን ስደብና ሙት”4 ተብሎ ነበር።4 ይህን ፈተና ተቋቋመ እናም ከልዑል ልቡም እንዲህ በማለት አወጀ፥

“አሁንም፥ እነሆ፥ ምስክሬ በሰማይ አለ፥ የሚመሰክርልኝም በአርያም ነው።”5

የሚቤዠኝ ሕያው እንደ ሆነ አውቃለሁ።6

ኢዮብ እምነቱን ቀጠለ። ወደ እኛ የሚመጡት ፈተናዎች ሲያጋጥሙን እንደ ኢዮብ እናደርጋለን?

በህይወት ምታት ምክንያት ሽከም እንዳለን ሲሰማን፣ ሌሎች እንዲህ አጋጣሚ እንደነበራቸው፣ እናም እንዳሸነፉት እናስታውስ።

በዚህ የጊዜዎች ፍጻሜ ዘመን ውስጥ የቤተክርስቲስያኗ ታሪክ ትግል ቢኖርባቸውም ቀጥተኛና ደስተኛ በሆኑት አጋጣሚዎች የተሞላ ነው። ምክንያቱ ምንድን ነው? የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌልን የህይወታቸው ዋና ክፍል አድርገውታል። ከሚያጋጥመን የሚያድነንም ይህ ነው። አስቸጋሪ ፈተናዎች ይኖሩናል፣ ነገር ግን እነዚህን ለመቋቋ እና ለማሸነፍ ችሎታ ይኖረናል።

ከበሽታ መኝታ፣ በእምባ ከረጠበ ትራስ፣ “አልጥልህም፥ አልተውህም”7 በሚለው በመለኮታዊ ማረጋገጫ እና ውድ ቃል ኪዳን በሰማይ ከፍ እንላለን። እንደዚህ አይነት መፅናኛ ታላቅ ዋጋ አለው።7 እንደዚህ አይነት መፅናኛ ታላቅ ዋጋ ያለው ነው።

በአለም አቀፍ የጥሪዬን ሀላፊነት ለማሟላት እሩቅ እና በስፋት ስጓዝ፣ ብዙ ነገሮችን ለማወቅ ችያለሁ –– ከእነዚህም ታናሽ ያልሆነውም ሀዘን እና ስቃይ ሀለንተናዊ እንደሆነ ነው። በሀዘን ያሉትን፣ የታመሙትን፣ ከጋብቻ መፋታት የሚያጋጥማቸውን፣ መንገዳቸውን ያጡ ልጆች ያላቸውን፣ ወይም በኃጢያት ምክንያት የሚሰቃዩትን ስጎበኝ ለመግለጽ የማይቻል የልብ መሰበር እና ሀዘን ተመልክቻለሁ። ዝርዝሩ ረጅም ነው፣ ምክንያቱም ሊደርሱብን የሚችሉ ችግሮች ለመቆጠር አይቻሉምና። አንድ ምሳሌን አውጥቶ ለመጠቆም አስቸጋሪ ነው፣ ግን ስለፈተና ሳስብ ሀሳቤ በልጅነቴ የሰንበት ትምህርት አስተማሪ ስለነበሩት ወንድም ብረምስ ይሄዳል። እርሳቸውም ወርቃማ ልብ ያላቸው ታማኝ የቤተክርስቲያኗ አባል ነበሩ። እርሳቸው እና ባለቤታቸው ሴዲ ስምንት ልጆች ነበሯቸው፣ እድሜአቸውም ከእኛ ቤተሰብ ካሉት ጋር አንድ የሆነ ነበር።

ፍራንሲስ እና እኔ ከተጋባንና ከዎርዱ ከወጣን በኋላ፣ ወንድም እና እህት በርምስ እና ቤተሰቢቻቸውን በጋብቻና በለቅሶዎች ጊዜ እናያቸው ነበር።

በ1968 ዓ.ም (እ.አ.አ) ወንድም በርምስ ባለቤታቸውን ሴዲን በሞት አጡ። አመቶችም ሲያልፉ ከስምንቱ ሁለት ልጆቻቸውም ሞቱባቸው።

ከ13 አመት በኋላ አንድ ቀን፣ የወንድም ብረም የልጅ ልጅ በስልክ ደወለችልኝ። አያቷ 105ኛ አመታቸው ላይ እንደደረሱ አብራራች። እንዲህም አለች፣ “በትንሽ መንከባከቢያ ቦታ ይኖራሉ፣ ግን በየሳምንቱ በሰንበት ከቤተሰባቸው ጋር ተገናኝነትው የወንጌል ትምህርትን ያስተምራሉ።” ቀጥላም፣ “ባለፈው እሁድ አያታችን እንዲህ አሉን፣ ‘ውዶቼ፣ በዚህ ሳምንት እሞታለሁ። ቶሚ ሞንሰንን እባካችሁ ጥሩልኝ። ምን መደረግ እንደሚገባ ያውቀዋል።’”

ወንድም ብረምስን በሚቀጥለው ምሽት ጎበኘኋቸው። ለብዙ ጊዜ አይቻቸው አላውቅም ነበር። መስማት ስለማይችሉ ላነጋግራቸው አልቻልኩም። አይናቸው ስለማያይ እንዲያነቧቸው የሚችሉትን መልእክት ልፅፍላቸው አልቻልኩም። ቤተሰባቸው ሊያነጋገሯቸው የሚችሉት የቀኝ እጃቸውን ይዘው የሚጎበኘውን ሰው ስም በግራ እጃቸው ላይ በመጻፍ እንደሆነ ተነገረኝ። ምንም መልእክቶች በዚህ ዘዴ ይሰጧቸው ነበር። የነሩኝን ተከትዬ በእጃቸው ላይ በልጅነት በሚያውቁኝ ስም “ቶሚ ሞንሰን” በማለት ጻፍኩኝ። ወንድም ብረምስ ተደሰቱ፣ እናም እጆቼን ወስደው በራሳቸው ላይ አሳረፉ። ፍላጎታቸው የክህነት በረከት ለመቀበል እንደሆነ አወቅሁኝ። ወደ መንከባከቢያው ቦታ የወሰደኝ ሾፌር ከእኔ ጋር ሆኖ እጆቻችንን በወንድም ብረምስ ራሳ ላይ ጫንን እና የተፈለገውን የክህነት በረከት ሰጠን። ከዚያም በኋላ እምባ ብርሀን ከሌላቸው አይኖቻቸው ፈሰሰ። እጆቼንም በምስጋና አጥብቀው ያዙ። ምን እንኳን የሰጠናቸውን በረከት ለመስማት ባይችሉም፣ መንፈስ በዚያ ጠንካራ ነበር፣ እናም ያስፈለጋቸውን በረከት እንደሰጠናቸው ለማወቅ መነሳሻ እንደነበራቸው አምናለሁ። ይህ አስደሳች ሰው ለማየት አይችሉም ነበር። ለመስማትም አይችሉም ነበር። በሚንከባከቡበት ቦታ በቀንም ይሁን በምሽት በትንሽ ክፍል ውስጥ ይቀመጡ ነበር። ነገር ግን በፊታቸው የነበረው ፈገግታ እና የተናገሩት ቃላት ልቤን ነክተው ነበር። “አመሰግናለሁ፣”አሉ። “የሰማይ አባቴ ለእኔ በጣም መልካም ነበር።”

ከሳምንት ውስጥ፣ ልክ ወንድም ብረምስ እንዳሉት ሞቱ። ባልነበራቸው ላይ አላተኮሩም፤ ግን ለነበራቸው ብዙ ለነበራቸው በረከቶች ዝልቅ ምስጋና ሁልጊዜም ነበራቸው።

የሚያስደስቱን ብዙ ነገሮች የሚሰጠን የሰማይ አባታችን መቋቋም ባለብን ፈተናዎች ለመማር፣ ለማደግና፣ ለመጠናከር እንደምንችል ያውቃል። ልባችን የሚሰበርበት እና የምናዝንበት፣ የናለቅስበት፣ እና ምን ያህል እንደምንችል የሚመዝንበት ጊዜም እንደሚኖር ያውቃል። ነገር ግን፣ እንደዚህ አይነት ችግሮች ለሚሻል ሁኔታ እንድንቀየር፣ የሰማይ አባታችን በሚያስተምረን መሰረት ህይወታችንን እንድንገነባ፣ ከነበርንበት የተለየ፣ እንዲሁም የተሻለ እንድንሆን፣ ከዚህ በፊት የተሻለ እውቀት እንዲኖረን፣ የሌሎች ጉዳን የሚሰማን እንድንሆን፣ እና ከነበረን በላይ የሆነ ምስክሮች እንዲኖረን ያደርጉናል።

ይህም አላማችን መሆን ይገባዋል–– በጸሀይ ብርሀን እና በጥላ ስንሄድም የምንቋቋምና የምንጸና፣ አዎን፣ ደግሞም በተጨማሪ በመንፈስ የተጣራን መሆን ይገባናል። በምናሸንፋቸው ፈተናዎች እና በምንቋቋማቸው ችግሮች ባይሆን ኖሮ፣ እንዳለንበት የዘለአለም ህይወት ወደሆነው አላማችን በትንሽም ይሁን በምንም አናድግም ነበር። ገጣሚው በሚቀጥሉት ቃላት ይህንንም ሀሳብ አቅርቦ ነበር፥

ጥሩ እንጨት በቀላሉ አያድግም፣

ጠንካራው ንፋስ፣ ዛፉን ያጠናክራልና።

ሰማይም ሲርቅ፣ ርዝመቱ ታላቅ ነው፣

አውሎ ንፋሱ ሲጨምር፣ ጥንካሪውም ብዙ ነው።

በጸሀይና በብርድ፣ በዝናብና በበረዶ፣

በዛፍና ሰዎች፣ ጥሩ እንጨት ያድጋል።8

መምህር ብቻ የፈተናችንን ዝልቅነት፣ ህመማችንን፣ እና የምንሰቃይበትን የሚያውቅው። በፈተና ጊዜ ዘለአለማዊ ሰላም የሚያቀርብልን እርሱ ብቻ ነው። የሚሰቃየውን ነፍሳችንን በሚያፅናኑ ቃላት የሚነካውም እርሱ ብቻ ነው፥

“እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ።

“ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤”

“ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜም ቀሊል ነውና።”9

መልካም ጊዜ ይሁን መጥፎ፣ እርሱ ከእኛ ጋር ነው። እንደማይቀየርም ቃል ገብቶልናል።

ወንድሞቼና እህቶቼ፣ በህይወት ፈተና ጊዜ የማይቀንስ እና የማይጨምር ለሰማይ አባታችን ታማኝነት ይኑረን። እርሱን ለማስታወስ ችግሮች እንዲያጋጥሙን አያስፈልጉን፣ እናም ለእርሱ እምነታችንን ለመስጠት ወደ ትሁትነት መገፋት አያስፈልገን።

ወደ ሰማይ አባታችን ለመቅረብ ሁልጊዜም እንጣር። ይህን ለማድረግ፣ ወደ እርሱ እንጸልይ እና በየቀኑም እርሱን እናድምጥ። የጸሀይ ብርሀን ወይም የዝናብ ቀን ቢሆኑም፣ በየሰአቱ በእውነት እርሱን እንፈልጋለን። እንዲህ የሚለው የእርሱ ቃል ኪዳን እኛ የምንፈልገው ይሁን፣ “አልጥልህም፥ አልተውህም።”10

በነፍሴ ጥንካሬ በሙሉ እግዚአብሔር ህያው እንደሆነ እንደሚያፈቅረን፣ አንድያ ልጁ ህያው እንደሆነ እና ለእኛ እንደሞተ፣ እናም የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል በህይወታችን ጭለማ ሰብሮ የሚገባው ብርሀን እንደሆነ እመሰክራለኁ። ይህም እንዲሆን የምጸልየው በቅዱሱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው፣ አሜን።

አትም