2014 (እ.አ.አ)
የኢየሱስ ክርስቶስ መለኮታዊ ተልዕኮ፥ ምሳሌ
ጃንዩወሪ 2014


የሴቶች የቤት ለቤት ማስተማሪያ መልእክቶት፣ ጥር 2014 (እ.አ.አ)

የኢየሱስ ክርስቶስ መለኮታዊ ተልዕኮ፥ ምሳሌ

በጸሎት መንፈስ ይህንን መረጃ አንብቡት እና ምን እንደምታካፍሉ ለማወቅ ጣሩ። የአዳኝንን ህይወት እና ተልእኮ መረዳት በእርሱ ያላችሁን እምነት የሚያሳድገው እና በሴቶች የቤት ለቤት ትምህርት ምክንያት የምትንከባከቧቸውን የሚባርከው እንዴት ነው? ለተጨማሪ መረጃ ወደreliefsociety.lds.org

እምነት, ቤተሰብ, እርዳታ

ኢየሱስ ክርስቶስ በሁሉም ነገሮች ምሳሌአችን እንደሆነ እየተረዳን ስንመጣ፣ እርሱን ለመከተል ያለን ፍላጎት ይጨምራል። ቅዱሳት መጻህፍት በክርስቶስ እርምጃ እንድንከተል በማበረታቻዎች በሚሰጡን የተሞላ ነው። ለኔፋውያን ክርስቶስ እንዲህ አለ፣ “እኔ ስሰራው ያያችሁትን ስራ እናንተም ደግሞ ስሩ፤ ስሰራ ያያችሁትን ስራ እናንተም ያን ታደርጋላችሁ” (3 ኔፊ 27፥21)። ለቶማስ ኢየሱስ እንዲህ አለ፣ “እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም” (ዮሀንስ 14፥6)።

ዛሬ መሪዎቻችን አዳኝን እንደ ምሳሌአችን እንድናስቀምጥ እንድናስታውስ ያደርጉናል። ሊንዳ ኬ. በርተን፣ የሴቶች መረዳጃ ማህበር አጠቃላይ ፕሬዘደንት፣ እንዳሉት፣ “እያንዳንዳችን የኃጢያት ክፍያ ትምህርት በዝልቅ ልባችን ላይ ስንፅፍ፣ ጌታ እንድንሆን እንደሚፈልገን አይነት ሰዎች መሆን እንጀምራለን።”1

ፕሬዘደንት ቶማስ ኤስ. ሞንሰን እንዳሉት፣ “ጌታችን እና አዳኛችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌአችን እና ጥንካሬአችን ነው።”2

ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ለመቅረብ፣ ትእዛዛቱን ለማክበር፣ እና ወደ ሰማይ አባታችን ለመመለስ ለመጣር ውሳኔ አንድርግ።

ከቅዱሳት መጻህፍት

2 ኔፊ 31፥16አልማ 17፥113 ኔፊ 27፥27ሞሮኒ 7፥48

ከታሪካችን

ስለኢየሱስ ክርስቶስ ስጋዊ አገልግሎት የሴቶች መረዳጃ ማህበር ሁልተኛ አጠቃላይ ፕሬዘደንት የነበሩት እላይዛ አር. ስኖው እንደጻፉት “መንገዱ አመለከተ እና በመንገዱም መራ።”3 ግለሰቦችንም—አንድ በአንድ አገለገለ። ዘጠና ዘጠኞችን ትተን የጠፋውን አንድ ለማዳን መሄድ እንደሚገባን አስተምሯል (ሉቃስ 15፥3–7ተመልከቱ)። በ2 ሺህ 500 ህዝቦች መካከል ለእያንዳንዱ ሰው ጊዜ በመስጠት፣ ግለሰቦችን ፈወሰ እናም አስተማረ (3 ኔፊ 11፥13–1517፥25 ተመልከቱ)።

ስለኋለኛው ቀን ቅዱሳን ሴቶች የቀዳሚ አመራር ሁለተኛ አማካሪ ፕሬዘደንት ዲየትር ኤፍ ኡክዶርፍ እንዳሉት፥ “እናንተ አስደናቂ እህቶች ለግል ጥቅም ያለን ፍላጎት በመተካት፣ ለሌሎች የርህራሄ አገልግሎት ትሰጣላችሁ። በዚህም የጌታን ምሳሌ ትከተላላችሁ። የእርሱ ሀሳቦች ሁልጊዜ ወደሌሎች የሚመለከት ነበርና።”4

ማስታወሻዎች

  1. ሊንዳ ኬ. በርተን, “Is Faith in the Atonement of Jesus Christ Written in Our Hearts?” Ensign ወይም Liahona፣ ህዳር 2012፣ 114።

  2. ቶማስ ኤስ. ሞንሰን፣ “Meeting Life’s Challenges፣” Ensign፣ ህዳር 1993፣ 71።

  3. “How Great the Wisdom and the Love፣” Hymns፣ ቁጥር 195።

  4. ዲየትር ኤፍ. ኡክዶርፍ፣ “Happiness, Your Heritage፣” Ensign ወይም Liahona፣ ህዳር 2008፣ 120።

ምን ማድረግ እችላለሁ?

  1. ኢየሱስ ክርስቶስ እንዴት እና ለምን ነው የእኔ ምሳሌ የሆነው?

  2. የምጎበኛቸውን እህቶች ማገልገሌ አዳኝን እንድከተን እንዴት ይረዳኛል?

አትም