2014 (እ.አ.አ)
ዛፍ ለመትከል ምርጥ የሆነው ጊዜ
ጃንዩወሪ 2014


የቀዳሚ አመራር መልዕክት፣ ጥር 2014 (እ.አ.አ)

ዛፍ ለመትከል ምርጥ የሆነው ጊዜ

በፕሬዘደንት ዲየትር ኤፍ. ኡክዶርፍ

በጥንት ሮሜ፣ ጃነስ የነገሮች መጀመሪያ ጣዖት ነበር። በአብዛኛው ጊዜ ሁለት ፊት እንዳለው ይሳል ነበር—አንደኛው ስላለፈው ወደኋላ የሚመለከት፣ ሌላኛው ስለሚመጣው ወደፊት የሚመለከት ነበር። በአንዳንድ ቋንቋዎች የጥር ወር በእርሱ ስም ነው የሚጠራው፣ ምክንያቱም የአመት መጀመሪያ የማስተዋል እና የማቀጃ ጊዜ ነው።

ከሺዎች አመታት በኋላ፣ በአለው አቀፍ ያሉ ብዙ ባህሎች በአዲስ አመት ወደፊት ለሚደረጉት ውሳኔ የማድረግ ልምድ አካበቱ። በእርግጥም፣ ስለወደፊት ውሳኔዎችን ማድረግ ቀላል ነው—እነሱን መከተል ግን የተለየ ጉዳይ ነው።

የአዲስ አመት የወደፊት ውሳኔ ረጅም ዝርዝር የነበረው አንድ ሰው ስለእድገቱ ጥሩ ስሜት ይሰማው ነበር። ለእራሱም እንዲህ በማለት አሰበ፣ “እስካሁን ድረስ፣ ምግብ ለመቀነስ የወሰንኩበትን ጠብቄአለሁ፣ ንዴተኛ አልሆንኩም፣ ገንዘብ በጀቲን ጠብቄአለሁ፣ እናም ስለጎረቤቴ ውሻ ምንም ቅሬታ አልገለጽኩም። ነገር ግን ዛሬ ጥር 2 ነው እና አላርሙ ጦኋል እናም ከመኝታ የመነሻ ጊዜ ነው። ይህን በማድረግ ለመቀጠል ታዐምር ይጠይቃል።”

እንደገና መጀመር

እንደገና በመጀመር ውስጥ አስደናቂ የሆነ ተስፋ አለ። በአንድ ጊዜም ይሁን በሌላ እኛ በነጻ መንገድ እንደገና ለመጀመር የምንፈልግበት እንዳለ አስባለሁ።

ንጹህ ዋና ዲስክ ያለው አዲስ ኮምፒውተር ማግኘትን እወዳለሁ። ለጊዜው በደንብ ይሰራል። ነገር ግን ቀናት እና ሳምንታት ሲያልፉ እና ተጨማሪ ፕሮግራሞች በኮምፒውተር ውስጥ ሲጨመሩ (አንዳንዶቹ በእቅድ፣ ሌሎቹ ያለእቅድ)፣ ኮምፒውተሩ ከመስራት ማቆም ይጀምራል፣ እናም በፍጥነት እና በቀልጣፋነት ያደርጋቸው የነበሩ ነገሮች ዘገምተኛ ይሆናሉ። አንዳንዴም ምንም አይሰራም። ዋና ዲስኩ በተለያዩ ትርምሶች እና በኤሌክትሮኒካዊ ፍርስራሾች የተመሰቃቀለ ሲሆንም ኮምፒውተሩን ማስነሳትም አስቸጋሪ ይሆናል። መደረግ የሚቻለው ነገር ቢኖር ኮምፒውተሩን መቅረጽና እንደገና መጀመር የሚሆኑበት ጊዜዎችም አሉ።

ሰዎችም በፍርሀት፣ በጥርጣሬ፣ እና በጥፋተኛነት ሽክም የተመሰቃቀሉ ሊሆኑ ይችላሉ።። የሰራናቸው ስህተቶች (በእቅድም ይሁን ሳናቅድ) ማድረግ እንዳለብን የምናውቀውን ለማድረግ ከባድ እንደሆነ እስከሚመስል ድረስ ሽክም ይሆኑብናል።

በኃጢያት ሁኔታ፣ ልባችን ላይ ሸክም የሚሆነውን የተመሰቃቀለው የውስጣችንን ዋና ዲስክ እነድናነጻ የሚስችል ንስሀ የሚባለው አስደናቂ መልሶ መቅረጫ አለ። ወንጌሉ፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ታዕምራታዊ እና ርህራሄ ባለው የኃጢያት ክፍያ በኩል፣ ነፍሳችንን ከኃጢያት እድፍ የምናጸዳበትን እና እንደገና እንደ ልጅ አዲስ፣ ንጹህ፣ እና የዋህ የምንሆንበትን ያሳየናል።

ነገ ግን አንዳንዴ ሌሎች ነገሮች ለመጀመር አስቸጋሪ እንዲሆኑብን የሚያደርጉ ጥቅም አልባ ሀሳቦች እና ስራዎች እንዲኖሩ በማድረግ ቀስ እንድንል እና ወደኋላ እንድንዘገይ ያደርጉናል።

የተሻለ እኛነታችንን ማምጣት

አላማዎችን ማቀድ ጥቅም ያለው ጥረት ነው። የሰማይ አባታችን አላማዎች እንዳለው እናውቃለን ምክንያቱም የእርሱ ስራ እና ክብር “የሰውን አለሟችነት እና ዘለአለማዊነት ለማምጣት” (ሙሴ 1፥39) እንደሆነ ነግሮናል።

የግል አላማዎቻችን የተሻለ እኛነታችንን ማምጣት ያስችላሉ። ነገር ግን፣ ውሳኔዎች ከማድረግ እና ከመጠበቅ የሚያስወግደን አንድ ነገር ቢኖር ዛሬ ነገ ማለት ነው። እኛ አንዳንዴ ትክክለኛ የሆነውን ጊዜ፣ እንዲሁም የአመት መጀመሪያን፣ የበጋ መጀመሪያን፣ እንደ ኤጲስ ቆጶስ ወይም እንደ ሴቶች መረዳጃ ማህበት ፕሬዘደንት የምንጠራበትን ጊዜ፣ ልጆች ወደ ትምህርት ከገቡ በኋላ፣ ጡረት ከወጣን በኋላ በመጠበቅ መጀመርን እናዘገየዋለን።

ወደ ጻድቃዊ አላማዎቻችሁ ወደፊት ለመግፋት ከመጀመራችሁ ግብዣአያስፈልጋችሁም። እንድትሆኑ በንድፍ የተደረጋችሁት አይነት ሰው ለመሆን ፈቃድ አያስፈልጋችሁም። በቤተክርስቲያኗ ለማገልገል እስከምትጋበዙ መጠበቅ የለባችሁም።

ለመመረጥ በመጠበቅ አንዳንዴ የህይወታችንን ብዙ አመታት ማባከን እንችላለን (ት. እና ቃ. 121፥34–36 ተመልከቱ)። ነገር ግን ይህ የኃሰት መነሻ መርህ ነው። እናንተ አሁንም የተመረጣችሁ ናችሁ!

በህይወቴ ስለጉዳዮች፣ ችግሮች፣ ወይም በግል ሀዘናትን በመጨናነቅ ምክንያት ለመተኛት ያልቻልኩባቸው ምሽቶች ነበሩ። ነገር ግን ምሽቱ ምንም የጨለመ ቢሆንም፣ በዚህ ሀሳብ ሁልጊዜም ተበረታትቻለሁ፥ በጠዋት ጸሀይ ትወጣለች።

በእያንዳንዱ አዲስ ቀን፣ አዲስ ንጋት ይመጣል—ለምድር ብቻ ሳይሆን ለእኛም። በአዲስ ቀንም እንደገና ለመጀመር እድል የሚሰጠን አዲስ ጀምሮ ይመጣል።

ነገር ገን፣ ብንወድቅስ?

አንዳንዴ ወደኋላ የሚይዘን ነገር ቢኖር ፍርሀት ነው። ስኬታማ አንሆንም፣ ስኬታማ እንሆናለን፣ እናፍራለን፣ ስኬታማነት ይቀይረናል፣ ወይም የምንወዳቸውን ሰዎች ይቀይራቸዋል በማለት እንፈራ ይሆናል።

ስለዚህ እንጠብቃለን። ወይም እንተወዋለን።

አላማዎችን ስናቅድ ማስታወስ ያለብን ሌላ ነገር ቢኖር ይህ ነው፥ ለአጭር ጊዜ ቢሆንም በእርግጠም እንወድቃለን። ነገር ግን ተስፋ መቁረጥ ሳይሆን ሀይል ይሰጠናል ምክንያቱም ይህ መረጃ አሁን ፍጹም መሆን አለባችሁ የሚለውን መገፋፊያ ያስወግድልናል። ይህም በአንድ ጊዜም ይሁን በሌላ እንደምንወድቅ ከመጀመሪያው እንድናውቅ ያደርጋል። ይህን በመጀመሪያ ማወቅ በመውደቅ የሚመጣውን አብዛኛውን ድንጋጤ እና ተስፋ መቁረጥ ያስወግድልናል።

አላማዎቻችንን በዚህ ሁኔታ ስንቀርብ፣ ውድቀት ሊገድበን አይገባውም። የመጨረሻ፣የምንፈልገውን አላማ ወዲያው ለማግኘት ባንችልም፣ ወደዚያ በሚመራው መንገድ ላይ እርምጃዎችን እንደወሰድን እናስታውስ።

ይህም ዋጋ አለው—ብዙ ትርጉሞችም አለው።

ወደምንጨርስበት ለመድረስ ባንችልም፣ ጉዞውን መቀጠል በፊት ከነበርንበት የተሻልን እንድንሆን ያደርጋል።

ለመጀመር ምርጡ ጊዜ ቢኖር አሁን ነው።

የጥንት ምሳሌያዊ አነጋገር እንደሚለው፥ “ዛፍን የመትከል ጥሩ ጊዜ ቢኖር ከሀያ አመት በፊት ነው። ሁለተኛው ጥሩ ጊዜም አሁን ነው።”

አሁን የሚለው ቃል የሚያስገርም እና ተስፋ የሚሰጥ አንድ ነገር አለው። አሁን ለመወሰን በመምረጥ፣ ወዲያው በዚህ ጊዜ ወደ ፊት ለመግፋት የሚያስችለንን ሀይል የሚሰጠን አንድ ነገር አል።

ከ20 አመት በኋላ ብቻ ሳይሆን ለዘለአለም፣ ወደፊት ለመሆን የምንፈልገው ሰው አይነት ለመሆን የምንጀምርበት ጊዜ አሁን ነው።

ከዚህ መልእክት ማስተማር

ፕሬዘደንት ኡክዶርፍ እንደገለጹት አላማዎቻችንን ለመድረስ በማንችልበት ጊዜ “ሀይል [ለማግኘት እንችላለን]። ወደምንጨርስበት ለመድረስ ባንችልም፣ ጉዞውን መቀጠል በፊት ከነበርንበት የተሻልን እንሆናለን።” የቤተሰብ አባላት ከትምህርት ቤት መመረቅ ወይም ሽልማትን ማግኘት አይነት ውጤት ሳይሆን ይህን ለማግኘት ካደረጉት ነገሮች ተጨማሪ ትምህርት ያገኙባቸው አጋጣሚዎቻቸውን እንዲካፈሉ ጠይቁ።