የሴቶች የቤት ለቤት ማስተማሪያ መልእክት፣ የመጋቢት 2014 (እ.አ.አ)
የኢየሱስ ክርስቶሰ መለኮታዊ ተልእኮ፥ የአለም ብርሀን
በጸሎት መንፈስ ይህንን መረጃ አንብቡት እና ምን እንደምታካፍሉ ለማወቅ ጣሩ። የአዳኝንን ህይወት እና ተልእኮ መረዳት በእርሱ ያላችሁን እምነት የሚያሳድገው እና በሴቶች የቤት ለቤት ትምህርት ምክንያት የምትንከባከቧቸውን የሚባርከው እንዴት ነው? ለተጨማሪ መረጃ ወደwww.reliefsociety.lds.org ሂዱ።
ኢየሱስ ክርስቶስ የአለም ብርሀን መሆኑን እየተረዳን ስንመጣ፣ በእርሱ ያለንን እምነት እንጨምራለን እናም ለሌሎች ብርሀን እንሆናለን። ክርስቶስ የእርሱን የስራ ፋንታ ለእያንዳንዱ ሰው ሁሉ [የማያበራ] የእውነት ብርሀን መሆን ነው (3. ት. እና ቃ. 93:2) በማለት መስክሯል እና “ወደ አለም ያበራ ዘንድ ብርሀን (የእርሱን) ከፍ አድርጋችሁ ያዙ” ብሎ ጠይቆናል (3ኛ ኔፊ 18፥24)።
ስለ ክርስቶስ ብርሀን ነብያቶቻችንም መስክረዋል። ፕሬዘዳንት ሄነሪ ቢ. አይሪንግ፣ በቀዳማዊ አመራር የመጀመሪያ አማካሪ፣ እንዲህ ብለዋል፥ “የበለጠ እንደ አዳኝ መስሎ ለመኖር መሞከርን በመረጣችሁ ቁጥር፣ ምስክርነታችሁን ታጠነክራላችሁ። ከጊዜም በኋላ እርሱ የአለም ብርሀን እንደሆነ ለራሳችሁ ታውቃላችሁ። … በህይወታችሁ ውስጥ የክርስቶስን ብርሀን ለሌሎች ታንጸባርቃላችሁ።”1
ሽማግሌ ኩዌንቲን ኤል. ኩክ የአስራ ሁለቱ ሐዋርያት አባል እኛ የአለም ብርሀን ስለመሆናችን እንዲህ አሉ፥ “ቤተሰቦቻችንን መጠበቅ አለብን አናም በማህብረሰቦቻችን ውስጥ ብርሀንን፣ ተስፋን እና ግብረ ገብነትን ጠብቆ ለመያዝ የቻልነውን ሁሉ በማድረግ ከሁሉም መልካም ስሜት ካላቸው ሰዎች ጋር ፊት ለፊት መሆን አለብን።”2
ከቅዱሳት መጻህፍት
ከታሪካችን
የኋለኛው ቀን ቅዱሳን ሴቶች ዛሬም ብርሀናቸውን ከፍ አድርገው መያዝን ቀጥለዋል።
በቻይና፣ሆንግ ኮንግ በሚገኝ ትልቅ ሕንጻ 80ኛው ፎቅ ላይ፣ አንድ ያላገባች አካል ጉዳተኛ የሆነች እህት፣ በቤተሰቧ ብቸኛ የኋለኛው ቀን ቅዱስ የሆነች ሴት፣ እርሷ እና ጎብኚዎች የመንፈስ ቅዱስን ተጽእኖ ሊሰማቸው የሚችሉበትን መጠለያ ቤት ፈጠረች። ቅዱሳት መጽሐፍቶቿን፣ የሴቶች መረዳጃ መመሪያ መጽሐፍቶቿን እና መዝሙር መጽሐፏን በቅርብ አስቀመጠች። ለአለፉት ዘመዶቿ ስርዐቶችን ለመፈጸም ወደ ቤተ-መቅደስ ተጓዘች።3
በብራዚል ውስጥ አንዲት ጻድቅ እናት ልጆቿን በወንጌል ብርሀን ውስጥ አሳደገች። የመጀመሪያ ክፍል መዝሙሮች የቀይ ብሎኬት ቤቷን አየር ሞሉት፣ እና ከLiahona ላይ የነበሩ የቤተ-መቅደሶች፣ የእግዚአብሔር ነብያቶች እና የአዳኝ ምስሎች ግድግዳዎቹን ሸፈኑት። ልጆቻቸው በቃል-ኪዳን ውስጥ ይወለዱ ዘንድ እርሷና ባለቤቷ በቤተ-መቅደስ ውስጥ ለመታተም መስዋትነትን ከፈሉ። በወንጌል ብርሀን፣ እውነት እና ጥንካሬ ውስጥ ልጆቿን እንድታሳድግ ጌታ እንዲረዳት የእርሷ ቋሚ ጸሎት ነበር።4
© 2014 by Intellectual Reserve, Inc. መብቶቹ በህግ የተጠበቁ። በዩ.ኤስ.ኤ የታተመ። እንግሊዘኛ የተፈቀደበት፥ 6/13 (እ.አ.አ) ትርጉም የተፈቀደበት፥ 6/13 (እ.አ.አ) Visiting Teaching Message, March 2014. Amharic. 10863 506 ትርጉም