2014 (እ.አ.አ)
ጉባኤ እና እኔ
ኤፕረል 2014


ወጣቶች

ጉባኤ እና እኔ

ደራሲዋ በቶሮንቶ፣ ካናዳ ነው የምትኖረው።

የአጠቃላይ ጉባኤ የሳምንት መጨረሻ ረጅም እና አሰልቺ ይመስለኝ ነበር፣ ነገር ግን ጊዜ ካለፈ በኋላ እየወደድኩት እና እየጓጓሁለት መጥቻለው። የአጠቃላይ ጉባኤ የሳምንት መጨረሻ መንፈስን እንደገና የሚሞላ ሊሆን ይችላል፣ ነገር ግን የተለመደው ሕይወት በሰኞ ሲቀጥል እነዚህን ስሜቶች እንዲደበዝዙ ማድረግ ቀላል ነው። ከሚከተሉት ሃሳቦች ውስጥ የተወሰኑት ከጉባኤ እስከቻልኩት ድረስ የበለጠ ማግገኘቴን እንድቀጥል እረድተውኛል።

ጥያቄዎችን በመጻፍ ለጉባኤ እራሴን አዘጋጃለው እናም ከዛ ጥያቄዎቼ በሚመለሱበት ሰአት ማስታወሻዎችን እይዛለው። ከዛ በኋላ፣ የጉባኤ ንግግሮችን እና መዝሙሮችን ከ LDS.org እቀዳለሁ እና የተለመደውን የሁልቀን ተግባሬን ሳከናውን ንግግር ወይም መዝሙር ማዳመጥ እንድችል በMP3 ማጫወቻ ላይ አደርጋቸዋለው። የ Liahona የጉባኤ እትምን ማጥናትም እወዳለው። በግሌ ግልባጭ ላይ በቀለም አሰምርበታለው እንዲሁም ዳርቻዎቹ ላይ ማስታወሻዎችን እይዛለው። ቀጣዩ ጉባኤ በሚመጣበት ጊዜ መጽሔቴ በደንብ ጥቅም ላይ ውሏል። ቤተሰቦቼ አንዳንድ ጊዜ መልዕክቶቹን በቤተሰብ ምሽት ውስጥ በጋራ ያጠኑታል።

በጉባኤው ጊዜ የተሰማንን መንፈስ ከእኛ ጋር ለማቆየት እና ከመልዕክቶቹ መማርን ለመቀጠል ስራ ይጠይቃል፣ ነገር ግን ይሄንን ማድረግ ታላቅ በረከት ነው የሆነልኝ። የአጠቃላይ ጉባኤ መልዕክቶችን በማጥናት በአስፈላጊ ጊዜዎች ውስጥ እጅግ ብዙ ጥንካሬን እና ምሬትን ተቀብያለው። እናም እነዚህ መልዕክቶች በመንፈስ የተነሳሱ እንደሆኑ አውቃለሁ።