የቀዳሚ አመራር መልእክት፣ ሚያዝያ 2014 (እ.አ.አ)
በጥብቅ የተቀመጠ መልህቅ
ብዙም ከመራቁ በፊት በትልቅ መርከብ ላይ በድንቁ የዩ ኤስ ኤ፣ አላስካ የባህር ዳርቻ ላይ የመጓዝ እድሉን አግኝቼ ነበር። ካፒቴኑ መርከቧ ከሌሎች ቦታዎች በራቀ ባልተበላሸ የባሕረ-ሰላጤ ውስጥ ለምታደረገው ያንድ ምሽት ቆይታ በሚዘጋጅበት ጊዜ፣ በጥንቃቄ ቦታውን እና እንደ የመአበሎቹን ተከታታይነት፣ የውሀዎቹን ጥልቀት እና ከአደገኛ መሰናክሎች ያለውን እርቀት የመሳሰሉትን ሁኔታዎች ገመገመ። ካረጋገጠ በኋላም፣ ተሳፋሪዎቹ የእግዚአብሔርን በጣም አስደናቂ ውብ ፍጥረቶችን እያዩ እንዲደነቁ እየፈቀደላቸው መርከቧ ደህና ሆና እንድትቆይ እና በጥንካሬ ሳትነቃነቅ እንድትቆይ መልህቅን ጣለ።
የባሕር ወለሉን እየተመለከትኩኝ በነበረበት ሰአት፣ መርከቧ ጎልቶ በማይታይ ሁኔታ ትንሽ መጠን ባለው አየር እና ከስሩ ባለው ሞገድ እየተንሸራተተች መሆኗን መገንዘብ ጀመርኩኝ። ይሁን እንጂ፣ በመልህቁ መስመር ርቀት እና በመልህቁ ጥንካሬ ውስጥ በተወሰነው የክብ ርቀት መሃከል መርከቧ በጥንካሬ እና በማይቋረጥ ሁኔታ ቆየች።
ካፒቴኑ መልህቁን መአበል የሚመጣ ከሆነ ብቻ እንዲወርዱ በማለት አዘጋጅቶ በመርከቡ ላይ አከማችቶ አላስቀመጠውም። አይደለም፣ መርከቧን እንደመከላከያ እርምጃ መልህቅ አደረገባት እናም ደህና ወዳልሆኑ ውሀዎች እንዳትሄድ ወይም ተሳፋሪዎች እና መርከበኞች ደህንነት በተሰማቸው ሰአት በዝግታ በመሬት ላይ እንዳትንሸራተት መርከቧን ጠበቀ።
ይህንን ትዕይንት እያሰላሰልኩኝ በነበረበት ሰአት፣ ይሄ ለምሳሌ የሚቻል ባይሆን ኖሮ አውሮፕላንን ፈጽሞ እንደማላበር መጣልኝ።
መልህቆችን ለምን እንደምንፈልግ
የመልህቅ ጥቅም መርከብን በተፈለገበት ስፍራ በደህና እና በጥንካሬ ለመጠበቅ ወይም በመጥፎ አየር ወቅት መርከቧን ለመቆጣጠር እንዲረዳ ነው። ይሁን እንጂ፣ እነዚህን እጅግ አስፈላጊ ጥቅሞች ለማከናወን የመልህቅ ብቻ መኖር በቂ አይደለም። መልህቁ ጠንካራ፣ አስተማማኝ እና በተገቢው መንገድ በትክክለኛው ጊዜና ቦታ ላይ መጠቀም አለበት።
ግለሰቦች እና ቤተሰቦችም እንዲሁ መልህቆችን ያስፈልጋቸዋል።
መከራ ከመስመራችን ሊበታትነን እንደ ትልቅ አውሎ ነፋስ ሊመጣ ይችላል እናም ከአለቶች ጋር ሊፈጠፍጠን ሊያስፈራራን ይችላል። ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ ሁሉም ነገር ደህና መስሎ ሲታይ—ነፋሶቹ ለስላሳ እና ውኃዎቹ ጸጥ ያሉ ሲሆኑ በአደጋም ውስጥ ነን። በእርግጥ፣ ስንንሸራተት እና እንቅስቃሴዎች መገንዘብ በማንችልበት ሁኔታ አነስተኛ ሲሆኑ በታላቁ አደጋ ውስጥ ልንሆን እንችላለን።
ወንጌል መልህቃችን ነው
መልህቆች ጠጣር፣ ጠንካራ እና ሲፈለጉ ዝግጁ እንዲሆኑ በድንብ የተያዙ መሆን አለባቸው። በተጨማሪም፣ ከመሰረቱ ጋር የተቃራኒ ጉልበቶችን ክብደት መቋቋም እንዲችሉ መያያዝ አለባቸው።
በእርግጥ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል እንደዚህ አይነት መልህቅ ነው። የአለም ፈጣሪ በሆነው ለመለኮታዊ አላማ እና ለልጆቹ ደህንነትን እና አመራርን ለመስጠት ተነድፎ የተዘጋጀ ነበር።
ያም ሆነ ይህ፣ ልጆቹን የማዳን እና እርሱ ወዳለበት መልሶ የማምጣት እግዚአብሔር እቅድ ከመሆኑ በስተቀር ወንጌል ምንድን ነው?
መንሸራተት በሁሉም ነገሮች ተፈጥሮ ውስጥ እንዳለ በማወቅ መልህቆቻችንን በወንጌል እውነታ የመሰረት ድንጋይ ላይ በፅኑነት ማስቀመጥ አለብን። በኩራት አሸዋዎች ላይ ቀስ ብለው ወይም የጥብቅ እምነቶቻችንን ወለል በትንሹ እየነኩ መውረድ የለባቸውም።
በዚህ ወር በቤተክርስቲያኗ አጠቃላይ ጉባኤ ውስጥ ከእግዚአበሔር አገልጋዮች ለመስማት እድል አለን። ቃሎቻቸው ከቅዱሳን መጽሐፍቶች እና ከመንፈስ ግፊቶች ጋር ተገናኝተው በሕይወት ትግሎችና ሙከራዎች ውስጥ ጽኑ እና ጠንካራ ሆነን መቆየት እንድንችል መልህቆቻችንን የምናያይዝበትን ጥብቅና ቋሚ የሆነ የዘለአለም ጥቅሞችና መርሆች መሰረተ-ድንጋይ ይሰጡናል።
የጥንቱ ነቢይ ሔለማን እንደዚህ አስተማረ፣ “የእግዚአብሔር ልጅ በሆነው በክርስቶስ፣ አዳኝ በሆነው በአለቱ መሰረታችሁን መገንባት እንዳለባችሁ፤ ዲያብሎስ ኃይሉን፣ ንፋሱን፣ አዎን፣ በአውሎ ነፋስ እንደሚወረወረው ዘንጉን በላከ ጊዜ፤ አዎን ትክክለኛ መሰረት በሆነው ሰዎች ከገነቡበት ሊወድቁበት በማይችሉበት አለት ላይ ስለገነባችሁ በረዶው፣ እናም ኃይለኛው ውሽንፍር በሚመታችሁ ጊዜ እናንተን ወደ ስቃይና መጨረሻ ወደሌለው ባህረ ሰላጤ ጎትቶ ለመጣል ኃይል አይኖረውም” (ሔለማን 5፥12)።
በጥንካሬ የተቀመጡ መልህቆች ጥቅም
ሕይወት መልህቆቻችንን የመፈተሻ እና እንድንንሸራተት የመገፋፊያ መንገድ አላት። ይሁን እንጂ፣ መልህቆቻችን በትክክል በአዳኛችን አለት ውሰጥ ከተቀመጡ፣ ምንም እንኳን የአየሩ ኃይል፣ የመአበሉ ጥንከሬ ወይም የሞገዶቹ ቁመት ከፍተኛ ቢሆንም ይይዛሉ።
በእርግጥ፣ መርከቧ የተሰራችው መልህቅን በማንሳት እና የሕይወትን ባሕሮች እንድትዞር ነው እንጂ ወደብ ውስጥ እንዳለች በቦታዋ እንድትቆይ አይደለም። ነገር ግን ይሄ ለሌላ ጊዜ የሚሆን ምሳሌ ነው።
ለአሁን፣ የወንጌል መልህቅ እና የአዳኛችን አለት ቋሚ እና ደህና እንድንሆን እንደሚጠብቁን በማወቄ እፅናናለው።
እንደዚ አይነት መልህቅ ወደ አደጋ እና መከራ ከመንሸራተት ይጠብቀናል። የማይነፃፀሩትን ሁሌ ተለዋዋጭ ውበቶች እና ልብ የሚማርክ የሕይወት ትዕይንት የሚያኮራውን እድል እንድናጣጥም ይፈቅድልናል።
ሕይወት ቆንጆ እና ለመኖር የምታሰፈልግ ናት። ነፋስ፣ መአበል እና ሞገዶች ወደሚታዩና የማይታዩ አደጋዎች እንድንንሸራተት ሊፈትኑን ይችላሉ፣ ነገር ግን የወንጌል መልዕክት እና መለኮታዊ ኃይሉ ወደ ደህናው የሰማይ አባታችን ወደብ መመለሻ መንገዳችን ላይ ይጠብቁናል።
ስለዚህ የሚያዝያው አጠቃላይ ጉባኤ ንግግሮችን ማድመጥ ብቻ ሳይሆን፣ ነገር ግን መልዕክቶቻቸውን ለሁልቀን ኑሯችን በጥብቅ እንደተቀመጠ መልህቅ እንዲሁተግባራዊእናድርግ።
በዚህ ትርጉም ባዘለ እና አስፈላጊ በሆነ ሙከራ እግዚአብሔር ይባርከን እናም ይምራን!
© 2014 በ Intellectual Reserve, Inc. መብቶቹ በህግ የተጠበቁ። በዩ.ኤስ.ኤ የታተመ። እንግሊዘኛ የተፈቀደበት፥ 6/13 (እ.አ.አ) ትርጉም የተፈቀደበት፥ 6/13 (እ.አ.አ) First Presidency Message, April 2014. Amharic. 10864 506 ትርጉም