ልጆች
መልህቃችሁን አስቀምጡ
እናንተን ከወንጌል ጋር እንዳትነቃነቁ እና በቦታችሁ እንድትቆዩ የሚይዛችሁ ነገር ምንድን ነው? የአንድ መርከብን እና መልህቅን ምስል ለመሳል ትፈልጉ ይሆናል። ከዛም ከመልህቃችሁ አጠገብ መርከባችሁን በደህና እንድትቆይ የሚረዳችሁን ማንኛውንም የሰዎችን ወይም የነገሮችን ምስሎች ማጣበቅ ወይም በፕላስተር ማያያዝ ትችላላችሁ። ፕሬዘደንት ኡክዶርፍ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ ዘመናዊ ነብያቶች እና ቅዱሳን መጽሐፍቶች ለሕይወቶቻችን ምርጥ መልህቆች ናቸው እንዳሉ አስታውሱ።