2014 (እ.አ.አ)
የቅድመ አያቶችን ስም በፊደል በተራ መዘርዘርን ልወደው እችላለሁን?
ጁን 2014


ወጣቶች

የቅድመ አያቶችን ስም በፊደል በተራ መዘርዘርን ልወደው እችላለሁን?

ደራሲዋ በቬራክሩዝ፣ ሜክሲኮ ትኖራለች

50 ሺህ የቅድመ አያት ስሞችን በፊደል በተራ ለመዘርዘር ካስማችን በነበራት አላማ ተሳትፌ ነበር። በመጀመሪያ አስቸጋሪ ነበር። በተለያዩ ጊዜዎች ከኮምፒውተር ያገኘኋቸው መዝገቦች ለማንበብ በሚያስቸግር የእጅ ጽሁፍ የተጻፉ ነበሩ፣ እናም አንዳንዴም ለመመለስ እና ሌላ መዝገብ ከኮምፒውተር ለማግኘት እፈልግ ነበር። ነገር ግን ሁሉም ሰዎች እንደዚህ የሚያስቡ ከሆኑ፣ እነዚህ መዝገቦች በመጨረሻ ለመፈጸም እንደሚቀሩ ገባኝ። በመንፈስ አለም የተሰለፉ ብዙ ሰዎች በአዕምሮዬ ማየት እችል ነበር፣ እናም እነዚህን ስሞች ለማንበብ እና ያለስህተት ለመጻፍ በመሞከር ለመቀጠል ወሰንኩኝ።

ለእነዚያ ሰዎች ፍቅር እንዲኖረኝ ተማርኩኝ። እነርሱ በእውነትም እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው፣ እና እኛም ከእነርሱ እርዳታ እደሚያስፈልገን ተረዳሁ። የሰማይ አባት ፍጹም አላማ በሁሉም ሰዎች ላይ እንደሚያስብበት በደንብ ለመረዳት ቻልኩኝ። በእርሱ የተመረጡ መሪዎችን መመሪያዎች እና ትምህርቶች ስንከተል፣ ስለእርሱ ምህረት እና መጨረሻ ስለሌለው ፍቅር ምስክር ለመሆን እንችላልን።

የቅድመ አያቶችን ስም በፊደል በተራ መዘርዘር ለእኔ የሚያስደስት አጋጣሚ ነበር። ስለቤተሰብ ታሪክ ብዙ ነገሮችን እንዳፈቅር እና ታላቅ ዋጋ እንድሰጥ ተማርኩኝ። የቅድመ አያቶችን ስም በፊደል በተራ በመዘርዘር ላይ በመሳተፍ ታዛዥ በመሆንም ከጌታችን ታላቅ ዋጋ ያላቸው ን ስጦታዎች አገኘሁ።