የሴቶች የቤት ለቤት ማስተማሪያ መልእክት፣ ሰኔ 2014 (እ.ዓ.ዓ)
የኢየሱስ ክርስቶስ መለኮታዊ ተልዕኮ፥ ምሳሌ
በጸሎት መንፈስ ይህንን መረጃ አንብቡት እና ምን እንደምታካፍሉ ለማወቅ ጣሩ። የአዳኝንን ህይወት እና ተልእኮ መረዳት በእርሱ ያላችሁን እምነት የሚያሳድገው እና በሴቶች የቤት ለቤት ትምህርት ምክንያት የምትንከባከቧቸውን የሚባርከው እንዴት ነው? ለተጨማሪ መረጃ ወደ ሂዱ reliefsociety.lds.org።
ሌሎችን ስናገለግል፣ ለእኛ ምሳሌ ለነበረው ኢየሱስ ክርስቶስ እውነተኛ ተከታዮች እንሆናለን። ፕሬዘደንት ቶማስ ኤስ. ሞንሰን እንዳሉት፥ “እርዳታ በሚያስፈልጋቸው ተከበናል። በዚህ ምድር ላይ እኛ ልጆቹን የማገልገል እና የማንሳት ጭምር አደራ ያለን የጌታ እጆች ነን።”1
የሴቶች መረዳጃ ማህበር አጠቃላይ ፕሬዘደንት ሊንዳ ኬ. በርተን እንዳስተማሩት፥ “በልምምድ፣ የእግዚአብሔርን ልጆች ስናገለግል እያንዳንዳችን እንደ አዳኝ ለመሆን እንችላለን። እርስ በራስ [ለማገልገል] እንድንችል እንዲረዳን፣ የምናስታውሳቸው አራት ቃላቶችን በሀሳብ አቀርባለው፥ ‘መጀመሪያ ተመልከቱ፣ ከዚያም አገልግሉ።’ … ይህን ስናደርግ፣ ቃል ኪዳኖችን እንጠብቃለን፣ እናም ፕሬዘደንት ሞንሰን እንዳሉትም፣ አገልግሎታችንም የደቀመዛሙርትነታችን ምልክት ይሆናል።2
በየጠዋት ሌሎችን ለማገልገል ያሉንን እድሎች ለማወቅ መጸለይ እንችላለን። የወጣት ወንዶች አጠቃላይ ፕሬዘደንት ዴቪድ ኤል. ቤክ እንዳሉት “የሰማይ አባት ይመራችኋል፣ እናም መላእክቶችም ይረዷችኋል።” “ህይወቶችን ለመባረክ እና ነፍሶችን ለማዳን ሀይል ይሰጣችኋል።”3
ከቅዱሳት መጻህፍት
ከታሪካችን
በጥቅምት 1856 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ፣ፕሬዘደንት ብሪገም ያንግ (1801–77) የእጅ ጋሪ የሚገፉ ፈር ቀዳጆች ሜዳዎችን እየተሻገሩ እንዳሉ እና ሁሉም የሚያስፈልጋቸውን ወዲያው በመሰብሰብ እንዲረዱ አወጁ። ሴቶች “ሽርጦቻቸውን ፣ የእግር ሹራቦቻቸውን፣ እና በትርፍ ያላቸውን ነገሮች በሙሉ በዚያው በታበርናክል ውስጥ አወለቁ፣ እናም በጋሪዎች ውስጥ ኮለሏቸው” ብለው ሉሲ ሜሰርቨ ስሚዝ ጻፉ።
እንዲድኑ የተደረጉት ፈር ቀዳጆች ወደ ሶልት ሌክ ስቲ ሲደርሱ፣ ሉሲ እንደጻፉት “በህይወቴ በሙሉ ከሰራኋቸው ስራዎች ሁሉ ከዚህ በላይ የሆነ የሚያስደስት አልነበረም፣ እንደዚህ የሚስማማ ስሜት ያሸንፍ ነበር። ወደ ሱቅ ገብቼ የምፈልገው ን ማሳወቅ ብቻ ነበር የሚያስፈልገኝ፤ ልብስ ከሆነ፣ ያለ ክፍያ የርዝመትና የስፋት መጠን ይለካ ነበር።”4
ፕሬዘደንት ጆርጅ አልበርት ስሚዝ (1870–1951) ሌሎችን ስለማገልገል እንዲህ ብለዋል፥ “የዘለአለም ደስታችን ሌሎችን ለመርዳት እራሳችንን በመስዋዕት በምናሳልፍበት መንገድ የሚመዘን ይሆናል።”5
© 2014 by Intellectual Reserve, Inc. መብቶቹ በህግ የተጠበቁ። በዩ.ኤስ.ኤ የታተመ። እንግሊዘኛ የተፈቀደበት፥ 6/13 (እ.አ.አ) ትርጉም የተፈቀደበት፥ 6/13 (እ.አ.አ) Visiting Teaching Message, June 2014. Amharic. 10866 506 ትርጉም