2014 (እ.አ.አ)
ታሪካችሁን እወቁ
ጁን 2014


ልጆች

ታሪካችሁን እወቁ

ወላጆቻችሁ እና አያቶቻችሁ ብዙ ጀብዶች ነበሯቸው—አንዳንዶቹን እናንተም አታውቋቸውም! ከታሪኮቻቸው አንዳንዶቹ፣ ያስቋችኋል፣ እናም በሰማይ አባት እምነት እንዲኖሯችሁ ሊረዷችሁም ይችላሉ። ነገር ግን አንዳንዴ ጎልማሶችም ሊያፍሩ ይችላሉ። የሚወዷቸውን ታሪኮች እንዲያስታውሱ ለመርዳት እነዚህን ጥያቄዎች ተጠቀሙ እናም መልሳቸውን ጻፉ ወይም በስ እል ሳሉ።

  1. ከትዝታዎቻችሁ የሚያስደስቷችሁን ሶስቱን ንገሩኝ።

  2. ከሁሉም በላይ የሚያሳፍራችሁ የነበረ ሁኔታ ምን ነበር?

  3. ስለተወለድኩበት ቀን ንገሩኝ?

  4. በልጅነታችሁ ምን ማድረግ ትወዱ ነበር?

  5. ስለወንጌል ምስክርነታችሁን እንዴት አገኛችሁ?