2014 (እ.አ.አ)
የሴት አያቴን መግባባት
ጁላይ 2014


ወጣቶች

የሴት አያቴን መግባባት

ደራሲዋ በቨርጂንያ ዩኤስኤ ነው የምትኖረው።

ለወጣት ሴቶች ለማደርገው አንዱ ፕሮጀክት፣በሜሳ አሪዞና፣ ዩ.ኤስ.ኤ በሚገኘው የቤተሰብ ታሪክ በሚፈተሽበት ቦታ የሴት አያቴ ስለቅድመ አያቶቿ እውቀት እንድታገኝ ለመርዳት ፈቃደኛ ነበርኩኝ። ጎን ለጎን ተቀምጠን ቤተሰቦቻችንን ስንፈልግ፣”በርግጥ አኔአሁን ከጎኔ ስላለችው የሴት አያቴ አውቃለሁን?” ብዬ ማሰብ ጀመርኩኝ።

ብዙ የቤተሰብ አባሎችን አገኘን፣መረጃቸውን አዘጋጀን፣ እናም ጥምቀታቸውን አና የመንፈስ ቅዱስ ስጦታቸውን ለመፈፀም ወደ ሜሳ አሪዞና ቤተመቅደስ ሄድን። ብዙም ሳይቆይ የሴት አያቴ የእሷን ቤተሰብ ታሪክ ፅንፍ ቅንብር ሰጠችኝ።

የመገጣጠሚያ ቁርጥማት በሽታ ስላሰቃያት፣ ለሴት አያቴ ኮምፒተር ላይ መፃፍ በጣም ሕመም ነበረው። ኮምፒተር ላይ እሷን መርዳት ያስደስተኛል። ለቤተሰባችን መንፈሳዊ ጥቅም ከእሷ ሕይወት ታሪኮቹን አብረን ፃፍን። በእነዚህ የጥናት ፅሁፎች ላይ ግብረ አበር ስንሆን፣ የእሷየሕይወት አካል መሆንና ስለቤተክርስቲያን ታሪክ ብዙ መማር እወዳለሁ።