የቀዳሚ አመራር መልእክት፣ ሐምሌ 2013 (እ.አ.አ)
የልቦች መመለስ ቃል ኪዳን
እናቴ፣ ሚልድረድ በኚዮን አይሪንግ፣በዩታ፣ ዩ.ኤስ.ኤ፣ በግረንጀር የእርሻ መንደር ውስጥ አደገች። ከእሷ ወንድሞች አንዱ፣ ሮይ፣ የቤተሰቡን በግ እርባታ ስራ ተከተለ። ወጣት አንደመሆኑ ብዙ ሳምንታትን ከቤት ርቆ አሳለፈ። ከጊዜ በኋላ በቤተክርስቲያን ላይ ያለው ጉጉት ያነሰ ሆነ። በመጨረሻም ወደ አይዳሆ፣ዩ.ኤስ.ኤ ሄደ፣ አገባ፣ እናም ሶስት ልጆች ነበሩት። ሚስቱ 28 አመቷ እንዲሁም ልጆቹ ትናንሽ እያሉ በ34 ዓመቱ ሞተ።
ምንም እንኳን የሮይ ትንሽ ቤተሰብ በአይዳሆ ቢሆኑምና እናቴ 2,500 ማይል (4,025 ኪ.ሜ ) ወደ ኒው ጀርዝይ፣ ዩ.ኤስ .ኤ. ለቃ ብትሄድም፣ የፍቅር አና የብርታት ደብዳቤዎችን አብዛኛውን ጊዜ ትፅፍላቸው ነበር። የአጎቴ ቤተሰብ ወዳጃዊ በሆነ አጠራር እናቴን “አክስት ሚድ” ብለው ይጠሯት ነበር።
አመታት አለፉ፣ አንድ ቀን ከአጎቴ ልጆች መካከል ከአንዱ የስልክ ጥሪን ተቀበልኩ። ባሏ የሞተባት የሮይ ሚስት አንደሞተች ተነገረኝ። የአጎቴ ልጅ “አክስት ሚድ እንድታቁ ትፈልጋለች” አለኝ። አክስት ሚድ ከሞተች ረጅም ጊዜ ሆኗል፣ ነገር ግን ቤተሰቡ የእሷ ፍቅር አሁን ድረስ ይሰማቸዋል እናም ለእኔ ይህን ለመንገር በቅተዋል።
የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌልን ለቤተሰቦቻቸው ለማምጣት ከዘመዶቻቸው ጋር በቅርብ በመቆየት የኔፍያውያን ነብያት ሚናቸው ን ያሟሉበት እንዴት በተመሳሳይ ምን ያህል እናቴ በቤተሰቦቿ ውስጥ ሚና እንደሞላች ሳስብ ተደነኩኝ። ኔፊ የወንድሞቹን ልጆች ወደ ቤተሰባቸው መሪ ሌሂ እምነት እንዲመለሱ ተፅዕኖ እንዲያሳድርባቸው በማለት መዝገብን ፃፈ። የሞዛያ ልጆች ወንጌልን ለሌሂ ተወላጆች በሚሰብኩበት ጊዜ ተመሳሳይ ፍቅርን አሳዩ።
ጌታ ለዘላለም መቀጠል በሚችል ቤተሰብ ውስጥ ፍቅርእንዲሰማን መንገዶችን አዘጋጅቷል። ዛሬ በቤተክርስቲያን ውስጥ ያሉ ወጣቶች ልቦቻቸው ወደ ቤተሰቦቻቸው ሲመለስ ይሰማቸዋል። በዚህ ምድር ላይ የመዳንን ስርዓት ለመቀበል እድሉን ላላገኙ የቤተሰብ አባል ስሞችን እያሰሱ ነው። እነኛን ስሞች ወደ ቤተመቅደስ ይወስዳሉ። የጥምቀት ውሃዎች ውስጥ ሲገቡ፣ የጌታን ፍቅር እና የወኪልነት ስርዓት የምያከናውኑላቸውን ፍቅር የመሰማት እድሉን ያገኛሉ።
“እናታችን ሞታለች እና አክስት ሚድ አንድታውቅ ትፈልጋለች” በማለት ደውሎልኝ በነበረው በአጎቴ ልጅ ድምፅ ውስጥ የነበረውን ፍቅር አሁንም ድረስ አስታውሳለሁ።
ለቤተሰቦቻችሁ አባሎች ስራቶችን የምታከናውኑ ልክ እንደ ሞዛያ ልጆች እና እንደ ነብዩ ኔፊ በፍቅር እየደረሳችሁላቸው ነው። ልክ እንደ እነሱ፣ ግብዣችሁን ለሚቀበሉት ደስታ ይሰማችኋል። በርቀት ባሉ የቤተሰብ አባሎች ስለነበረው የምስዮን አገልግሎት ልክእንደ አሞን እርካታን እንዲሰማችሁ እናንተም መጠበቅ ትችላላችሁ፥
“ስለዚህ፣ እኛ እንመካለን፣ አዎን በጌታ እንመካለን፤ አዎን፣ ደስታችን በመፈፀሙ ሐሰት እናደርጋለን፣ አዎን፣ አምላካችንን ለዘላለም እናወድሰዋለን። እነሆ በጌታ በብዙ መመካት የሚችል ማን ነው? አዎን፣ ስለታላቁ ኃይል፣ እናም ስለምህረቱ፣ እናም ለሰው ልጆች ስላለው ፅናት አብዝቶ መናገር የሚችል ማን ነው? እነሆ እንዲህ እላችዋለሁ፣ ከተሰማኝ ጥቂቱን ለመናገር አልችልም” (አልማ 26፥16)።
ለቤተሰባችሁ አባሎች ያላችሁ የፍቅር ስሜት—የትም ቢሆኑ—ኤልያስ ይመጣል ያለው የፍፃሜ ቃል እንደሆኑ ምስክርነቴን አካፍላችዋኋለሁ ። መጥቷል። የልጆች ልቦች ወደ አባቶቻቸው እየተመለሱ ናቸው፣ እናም የአባቶች ልቦች ወደ ልጆቻቸው እየተመለሱ ነው: ናቸው (ሚልክያስ 4፥5–6፤Joseph Smith—History 1፥38–39 ተመልከቱ). የዘራችሁን ስሞች ለማግኘት እና እነኛ ስሞችን ወደ ቤተመቅደስ ለመውሰድ መነሳሳት ሲሰማችሁ፣ የትንቢቱን ፍፃሜ እየተለማመዳችሁ ነው።
የልቦች መመለስ የሚፈፀሙበት ዘመን ላይ መኖር በረከት ነው። ሚልድረድ በኚዮን አይሪንግ በልቧ ውስጥ መነሳሳት ተሰማት። የወንድሞችዋን ቤተሰብ ወደደች፣ እናም ደረሰችላቸው። ልቦቻቸው ወደ አክስት ሚድ በፍቅር እንደተመለሰ ተሰማቸው ምክንያቱም እሷ እንደምትወዳቸው አውቀዋልና።
© 2014 በ Intellectual Reserve, Inc. መብቶቹ በህግ የተጠበቁ። በዩ.ኤስ.ኤ የታተመ። እንግሊዘኛ የተፈቀደበት፥ 6/14 (እ.አ.አ) ትርጉም የተፈቀደበት፥ 6/14 (እ.አ.አ) First Presidency Message, July 2014. Amharic. 10867 506 ትርጉም