2014 (እ.አ.አ)
ዝግጁዎች ነን?
ሴፕቴምበር 2014


የቀዳሚ አመራር መልእክት፣ መስከረም 2014 (እ.አ.አ)

ዝግጁዎች ነን?

በአንድ ወቅት በኖርኩበት እና ባገለገልኩበት አከባቢ፣ ቤተክርስቲያኗ በአካባቢው በሚገኙ ዎርድ አባላት በመጡ ፈቃደኞች የተሞላ ክንፋማ እንስሳት የማርባት ስራ ታከናውን ነበር። በአብዛኛው ስራው በወቅቱ ይከናወን ነበር፣ በሺዎች የሚቆጠሩ እንቁላሎችን እና በመቶዎች የሚቆጠሩ ነዋሪ የቤት ክንፋማ እንስሳትን ወደ ኤጲስ ቆጶስ የማጠራቀሚያ ቤት ያቀርብ ነበር። በጥቂት ሁኔታዎች፣ በእርግጥ፣ ፍቃደኛ የከተማ አርሶ አደር መሆን የእጆች ማባበጥ ብቻ ሳይሆን የልብ እና አእምሮ ስልቹነትም ማለት ነበር።

ለምሳሌ፣ ለተቋሙ የበልግ ጽዳት ለማከናወን የአሮናዊ ክህነት ወጣት ወንዶችን የሰበሰብንበትን ጊዜ ሁሌም አስታውሰዋለሁ። ወኔ እና ሀይል ያለው ህዝባችን አንድ ላይ በተቋሙ ተሰበሰበ እና ፍጥነት ባለው ሁኔታ ነቀለ፣ ሰበሰበ እና በጣም ብዙ አረሞችን እና የተጠራቀሙ ቆሻሻዎችን አቃጠለ። በሚያበራው የእሳቱ ብርሀን፣ ሆት ዶግ በላን እና ጥሩ በሰራነው ስራ እራሳችንን እንኳን ደስ አለን አልን።

ቢሆንም፣ አንድ ክፉኛ የሆነ ችግር ነበር። ጩኸቱ እና እሳቱ ተኝተው የነበሩትን 5000 ዶሮዎች በጣም በመረበሹ አብዛኞቹ በድንገት አሮጌ ላባቸውን አጡ እና መተኛት አቆሙ። ከዛም በኋላ የበለጠ እንቁላል ለማምረት ጥቂት አረሞችን ከመንቀል ተቆጠብን።

ለተቸገሩት በማቅረብ የተባበረ ማንም የቤተክርስቲያን አባል ተሞክሮውን አይረሳም ወይም አይጸጸትበትም። ኢንደስትሪ፣ ጥንቁቅነት፣ እራስ መቻል፣ እና ለሌሎች ማካፈል ለእኛ አዲስ አይደሉም።

ምርጡ የማጠራቀሚያ ቤት አሰራር በቤተክርስቲያን ውስጥ ያሉ ሁሉም ቤተሰቦች የምግብ፣ አልባሳት፣ እና አስፈላጊ ከሆነ ሌላ ለህይወት አስፈላጊ ነገሮችን ማኖር መሆኑን ማስታወስ አለባችሁ። የጌታ የማጠራቀሚያ ቤት አማኝ የቤተክርስቲያን አባላትን ጊዜ፣ ተሰጥኦ፣ ሩህሩነት፣ ቅዱስ እቃዎችን፣ እና የገንዘብ ማግኛን ያካትታል። እነዚህ ግብአቶች ኤጲስ ቆጶስ የተቸገሩትን እንዲረዳ ያስችላሉ።

ሁሉንም የኋለኛ ቀን ቅዱሳን በእቅዳቸው ጥንቁቅ፣ በኑሮአቸው ወግ አጥባቂዎች እንዲሆኑ እና ከመጠን ያለፈ ወይም አላሰፈላጊ የሆነ ዕዳ እንዲያስወግዱ እናበረታታለን። አብዛኛዎቹ ሰዎች የምግብ እና የአልባሳት አቅርቦት ቢኖራቸው እና ከዕዳ የነፁ ከሆነ በኢኮኖሚ ሕይወታቸው በመአበል በጦዙ ሞገዶች ውስጥ ነድተው መውጣት ይችላሉ ። ዛሬ ብዙዎች ይሄንን ምክር በተቃራኒው ተከትለው እናገኛለን፥ የዕዳ አቅርቦቶች አላቸው እና ከምግብ የነፁ ናቸው።

የቀዳሚ አመራሩ ከትንሽ አመታት በፊት ያወጁትን እደግማለው፥

የኋለኛ ቀን ቅዱሳኖች ለብዙ አመታት ትንሽ ገንዘብ በማስቀመጥ ለመከራ ጊዜ እዲዘጋጁ ተመክረዋል። ይህን ማድረግ በማይለካ ሁኔታ ለደህንነት እና ለሰላም መሆን እገዛ ያደርጋል። እያንዳንዱ ቤተሰብ ለየራሱ ፍላጎት እስከቻለው ድረስ ለማሟላት ሀላፊነት አለው።

በምትኖሩበት የአለም ቦታ ውስጥ ለመከራ ጊዜ የገንዘቦቻችሁን ሁኔታ በማየት እንድትዘጋጁ እናበረታታችኋለን። በወጪያችሁ መጠነኛ እንድትሆኑ፤ በግዢያችሁ ውስጥ ዕዳን ለማሰወገድ እንድትለማመዱ እናበረታታችኋለን። ዕዳን እንደምትችሉት በፍጥነት ክፈሉ፣ እና እራሳችሁን ከእዚ ምርኮ ነፃ አድርጉ። ቀስ በቀስ ተቀማጭ የሚሆን ገንዘብን ለመገንባት በተደጋጋሚ ትንሽ ገንዘብ አስቀምጡ።1

በሕይወታችን ውስጥ ለድንገተኛ ጊዜያት ዝግጁ ነን? ችሎታችን ፍፁም ሆነዋልን? በቁጠባ እንኖራለን? ተተኪ የሆነው አቅርቦት በእጃችን ላይ አለን? ለእግዚአብሔር ትዕዛዛት ታዛዦች ነን? ለነብያት ትምርቶች ሀላፊነት ይሰማናልን? ለድሆችና ለሚያስፈልጋቸው ቁሳችንን ለመስጠት ዝግጁ ነን? ጌታን እየተከተልነው ነውን?

በአስቸጋሪ ዘመን ነው የምንኖረው። ብዙውን ጊዜ የወደፊቱ አይታወቅም፤ ለማይታወቁት ነገሮች እንድንዘጋጅ ግድ ይለናል። የውሳኔ ጊዜ ሲደርስ፣ የመዘጋጃ ጊዜ አልፏል።

ማስታወሻ

  1. ቀዳሚ አመራር ሁሉም በደህና ተሰብስቧል፥ የቤተሰብ ገንዘብ አያያዞች (ፓምፍሌት፣) 2007 (እ.አ.አ.)።

ከዚህ መልእክት ማስተማር

የምትጎበኙትን ሰዎች ፍላጎት ከግምት ውስጥ በማስገባት በስራቸው የበለጠ ራሳቸውን የቻሉ እንዲሆኑ፣ በገንዘብ አያያዝ፣ በምግብ ክምችት፣ ወይም በድንገተኛ አደጋ እንዲዘጋጁ የምትረዷቸውን መንገዶች አስቡ። ከእነርሱ ጋር ማካፈል የምትችሉትን ክህሎት እንደ የአትክልት ቦታ አያያዘ ወይም የገንዘብ አመራር የፕሬዘደንት ሞንሰን ምክርን ለመከተል ኃይል የሚሰጣቸውን ነገሮች አስቡ።

አትም