2014 (እ.አ.አ)
የኢየሱስ ክርስቶስ መለኮታዊ ተልዕኮ፥ አፅናኝ
ሴፕቴምበር 2014


የሴቶች የቤት ለቤት ጉብኝት ማስተማሪያ መልእክት፣ መስከረም 2014 (እ.አ.አ)

የኢየሱስ ክርስቶስ መለኮታዊ ተልዕኮ፥ አፅናኝ

በጸሎት መንፈስ ይህንን መረጃ አንብቡት እና ምን እንደምታካፍሉ ለማወቅ ጣሩ። የአዳኝን ህይወት እና ተልእኮ መረዳት በእርሱ ያላችሁን እምነት የሚያሳድገው እና በሴቶች የቤት ለቤት ትምህርት ምክንያት የምትንከባከቧቸውን የሚባርከው እንዴት ነው? ለተጨማሪ መረጃ ወደ reliefsociety.lds.org ሂዱ።

እምነት • ቤተሰብ • እርዳታ

ኢየሱስ ክርስቶስ ቃል ገባ፣ “አልተዋችሁም፥ ወደ እናንተ አመጣለው” (ዮሐንስ 14፥18 )። “በአመድ ፋንታ አክሊልን፣ በለቅሶ ፋበ,ንታ የደስታን ዘይት ”ይሰጠናል (ኢሳያስ 61፥3) ። ምክንያቱም ክርስቶስ ለእያንዳንዳችን የሀጢያት ክፍያውን ስለተሰቃየ አይረሳንም። “የሚሰማን ስሜት እንዲኖረው እና እንዴት እንደሚያፅናናን ማወቅ ይችል ዘንድ አዳኛችን ህመማችንን፣ ስቃያችንን እና መቅሰፍታችንን በራሱ ላይ ወስዷል” አሉ የሴቶች መረዳጃ ማህበር አጠቃላይ አመራር ሁለተኛ አማካሪ ሊንዳ ኤስ ሪቭስ።1

ክርስቶስ እደሚያፅናናን ማወቁ ሰላምንና ምሳሌውን ለሌሎች አገልግሎት በመስጠት መነሳሳትን ሊያመጣልን ይችልላ። ፕሬዘደንት ቶማስ ኤስ. ሞንሰን ተናገሩ፥ “የወንጌል እውቀታችን እና ለሰማይ አባታችን እና ለአዳኛችን ያለን ፍቅር ያፅናናናል፣ ይደግፈናል እንዲሁም ቀና ብለን ስንራመድና ትዕዛዛትን ስንጠብቅ ወደ ልቦቻችን ደሰታን ያመጣልናል። በዚህች አለም ውስጥ የሚያሸንፈን ምንም ነገር አይኖርም።2

ከቅዱሳት መጽሐህፍት

ዮሐንስ 14፥18፣ 23አልማ 7፥11–13ት እና ቃ 101፥14–16

ከታሪካችን

እሌኒ ኤል ጃክ፣ 12ኛዋ የሴቶች መረዳጃ ማህበር አጠቃላይ ፕሬዘደንት፣ ተናገሩ “በቤት ለቤት ትምህርት ለእርስ በራሳችን እንደራረሳለን። ድምፆች እንደማይችሉት ብዙውን ጊዜ እጆች ይናገራሉ። ሞቅ ያለ እቅፍ ብዙ ትርጉምን ያስተላልፋል። የጋራ ሳቀ ያጣምረናል። በማካፈል ላይ ያለ ጊዜ መንፈሳችንን ያድሳል። የተቸገረን ሰው ሸክም ሁልጊዜ ለማንሳት አንችልም፣ ነገር ግን በደምብ መሸከም እንድትችል እሷን ማንሳት እንችላለን ።3

የመስራቾቻችን የሴቶች መረዳጃ ማህበር ሴቶች “በእርስ ለእርስ ፍቅራቸው እና ርህራሄያቸው ውስጥ መንፈሳዊ ጥንካሬን አገኙ። በህመም እና በሞት ፈተናዎች ሲሰቃዩ፣ እርስ ለራሳቸው በእምነት ፀለዩ እንዲሁም እርስ በራሳቸው ተፅናኑ። ‘ክፉው በእኛና በጌታ መሀል ለመግባት በሚያደርገው ሙከራ ኃይል አልባ እስኪመስል ድረስ፣ እና አንዳንዴም ጨካኝ ተወርዋሪዎቹ መርዛቸውን እስከሚያጡ ድረስ የእግዚአብሔር ፍቅር ከልብ ወደ ልብ ፈሰሰ’ ብላ ሔለን ማር ውትኒ ጻፈች።”4

ማስታወሻዎች

  1. ሊንዳ ኤስ ሪቭስ፣ “ጌታ አልረሳችሁም፣” Ensign ወይም Liahona፣ህዳር 2012፣ (እ.አ.አ.) 120።

  2. ቶማስ ኤስ ሞንሰን፣ “ደስተኛሁኑ፣” Ensign ወይም Liahona፣ ግንቦት 2009 (እ.አ.አ.)፣ 92።

  3. እሌኒ ኤል ጃክ፣ Daughters in My Kingdom: The History and Work of Relief Society 2011 (እ.አ.አ.)፣ 119።

  4. Daughters in My Kingdom፣ 171።

ይህን አስቡበት

ጌታ እንደሚያስታውሳችሁ መረዳቱ እንዴት መፅናናትን ያመጣላችኋል?

አትም