2014 (እ.አ.አ)
የኢየሱስ ክርስቶስ መለኮታዊ ተልዕኮ፥ የህይወት እንጀራ
ኦክተውበር 2014


የሴቶች የቤት ለቤት ጉብኝት መልእክት፣ ጥቅምት 2014 (እ.አ.አ)

የኢየሱስ ክርስቶስ መለኮታዊ ተልዕኮ፥ የህይወት እንጀራ

በጸሎት መንፈስ ይህንን መረጃ አንብቡት እና ምን እንደምታካፍሉ ለማወቅ ጣሩ። የአዳኝንን ህይወት እና ተልእኮ መረዳት በእርሱ ያላችሁን እምነት የሚያሳድገው እና በሴቶች የቤት ለቤት ትምህርት ምክንያት የምትንከባከቧቸውን የሚባርከው እንዴት ነው? ለተጨማሪ መረጃ፣ ወደwww.reliefsociety.lds.org ሂዱ

እምነት • ቤተሰብ • እርዳታ

ኢየሱስ እንዳለው፣ “ከሰማይ የወረደ ሕያው እንጀራ እኔ ነኝ፤ ሰው ከዚህ እንጀራ ቢበላ ለዘላለም ይኖራል፤ እኔም ስለ ዓለም ሕይወት የምሰጠው እንጀራ ሥጋዬ ነው” (ዮሀንስ 6፥51)። የአስራ ሁለት ሐዋሪያት ሸንጎ አባል ሽማግሌ ዲ. ቶድ ክርስቶፈርሰን “እኛ ደቀመዛሙርቱን በየቀኑ በዚያ ቀን ለሚያስፈልገን እንጀራ —እርዳታ እና ለድጋፍ— ወደ እግዚአብሔር እንድንመለከት ኢየሱስ ያስተምረናል፣” ብለዋል። “የጌታ ግብዣ ስለ አፍቃሪ አምላክ፣ ለትንሹ እንኳን ሳይቀር የልጆቹን የቀን ለቀን ፍላጎት እና እያንዳንዱን ለመደገፍ ያለውን ጉጉት ይናገራል። ‘ሳይነቅፍ በልግስና ለሁሉ በሚሰጠው’ በዚያ ፍጡር በማመን ለመጠየቅ እንችላለን እያለ ነው (ያዕቆብ 1፥5)።”1 ኢየሱስ ክርስቶስ ፍላጎታችንን እንደሚያሟላ ስንረዳ፣ ለመንፈሳዊ ድጋፍ ወደ እርሱ እንዞራለን።

የአስራ ሁለት ሐዋሪያት ሸንጎ አባል ሽማግሌ ጀፍሪ አር. ሆላንድ “ለህይወት እንጀራ በጉጉት ይፈልጉ ከነበሩት— ሳይመለሱ ወደ እርሱ ከመጡት፣ ከእርሱ ጋር ከቆዩት፣ እና ለደህንነት የሚሄዱበት ማንም እንደሌለ ካወቁት ከመጀመሪያዎቹ የክርስቶስ ደቀ መዛሙርቶች ጋር በጀብዱ አንድ እንድንሆን” ጋብዘውናል።2

ተጨማሪ ቅዱሳት መጻህፍቶች

ዮሀንስ 6፥32–35አልማ 5፥343 ኔፊ 20፥3–8

ከቅዱሳት መጽሐህፍት

ኢየሱስ ክርስቶስ ከ4 ሺህ በላይ ሰዎችን እያስተማረ ነበር። ከሶስት ቀናት በኋላ፣ ለደቀመዛሙርቶቹ እንዲህ አለ፥ “የሚበሉት ስለሌላቸው አዝንላቸዋለሁ

“ጦማቸውን ወደ ቤታቸው ባሰናብታቸው በመንገድ ላይ ይዝላሉ። …

“ደቀ መዛሙርቱም። በዚህ በምድረ በዳ እንጀራ ከየት አግኝቶ ሰው እነዚህን ማጥገብ ይችላል? ብለው መለሱለት።

“[ኢየሱስም፣] ስንት እንጀራ አላችሁ? ብሎ ጠየቃቸው፥ እነርሱም። ሰባት አሉት።”

ከዚያም ክርስቶስ “ባቱንም እንጀራ ይዞ አመሰገነ፥ ቈርሶም እንዲያቀርቡላቸው ለደቀመዛሙርቱ ሰጠ፥ ለሕዝቡም አቀረቡ፤ …

“ጥቂትም ትንሽ ዓሣ ነበራቸው፤ ባረከውም ይህንም ደግሞ እንዲያቀርቡላቸው አዘዘ።

“በሉም ጠገቡም፥ የተረፈውንም ቍርስራሽ ሰባት ቅርጫት አነሡ።” (ማርቆስ 8፥1–9ተመልከቱ።)

ማስታወሻዎች

  1. ዲ. ቶድ ክርስቶፈርሰን፣ “Recognizing God’s Hand in Our Daily Blessings፣” Liahona፣ ጥር 2012፣ 25።

  2. ጀፍሪ አር. ሆላንድ፣ “He Hath Filled the Hungry with Good Things፣” Liahona፣ ጥር 1998፣ 76።

ይህንን ተገንዘቡ

ወደ ክርስቶስ ስንመጣ፣ እርሱ እንዴት ይመግበናል?