2014 (እ.አ.አ)
ከመጸለያችሁ በፊት ተዘጋጁ
ኦክተውበር 2014


ወጣቶች

ከመጸለያችሁ በፊት ተዘጋጁ

ፕሬዘደንት አይሪንግ ጸሎት “በእግዚአብሔር እና በልጆቹ መካከል ያለ የሁለት መንገድ ግንኙነት ነው” ብለው እንድናስታውስ አድርገውናል።። ለጸሎታችን ለመዘጋጀት ጊዜ በመውሰድ የሁለት መንገድ ንግግር እንዲቻል ሊያደርግ ይችላል። በየቀኑ ለጸሎት ለመዘጋጀት ማስታወሻችሁን ለጥቂት ደቂቃዎች ለመጠቀም ትችላላችሁ። የሰማይ አባትን ለማመስገን የምትፈልጉበትን በረከቶች፣ ጸሎታችሁ የሚያስፈልጓቸውን ሰዎች፣ እና መልስ የምትፈልጉባቸው ጥያቄዎች ዝርዝር ለምዘጋጀትም ትችላላችሁ። ከዚያም መዝሙር በመዘመር ወይም ከቅዱሳት መጻህፍት አንዳንድ አንቀጾችን በማንበብ መንፈስን ጋብዙ። ስትጸልዩ፣ መንፈስ ቅዱስ ምን ማለት እንደሚገባችሁ እንዴት እንደሚመራችሁ ላይ ትኩረት አድርጉ፣ እናም በስሜታችሁ እና በሀሳባችሁ ላይም ትኩረት አድርጉ (ት እና ቃ 8፥2–3ተመልከቱ)። አጋጣሚያችሁን በማስታወሻችሁ ውስጥ ለመጻፍ እና የተቀበላችሁትን መልስ ለመገምገም አስቡበት። Preach My Gospel: A Guide to Missionary Service [ወንጌሌን ስበኩ፥ የሚስዮን አገልግሎት መመሪያ] ውስጥ በገጽ 95–97 የሚገኙትን መሳተፊያዎች ጸሎታችሁን ለመመዘን እንዲረዳችሁ እና መንፈስ ቅዱስን ለመረዳት እንድትማሩ ሙከራዎቹን መጠቀም ትችላላችሁ።