2015 (እ.አ.አ)
የቤተመቅደስ በረከቶች
ሜይ 2015


የቤተመቅደስ በረከቶች

ቤተመቅደስን ስንካፈል፣ የመንፈሳዊነት ስፋት እና የሰላም ስሜት ወደ እኛ ሊመጣ ይችላል።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣ ሀሳባችን የአለም አዳኝ ወደሆነው በሚዞርበት በዚህ የፋሲካ ማለዳ ከእናንተ ጋር በመሆኔ ምን ያህል አመስጋኝ ነኝ። ለእያንዳንዳችሁ ፍቅሬን እና ሰላምታዬን አደርሳለሁ እና ቃላቶቼን የሰማይ አባት ያነሳሳ ዘንድ እፀልያለሁ።

ይህ ጉባኤ የቤተክርስቲያን ፕሬዘዳንት እንድሆን ድጋፍ ያገኘሁበት ሰባተኛ አመት ሆኗል። በጥቂት አስቸጋሪ ሁኔታዎች ብቻ ሳይሆን በማይቆጠሩ በረከቶች የተሞሉ ስራ የበዛባቸው አመታት ነበሩ። በጣም አስደሳች እና ቅዱስ ከሆኑት በረከቶች መካከል አዲስ ቤተመቅደሶችን ቡራኬ መስጠት እና ለቆዩት ቤተ መቅደሶች በድጋሚ ቡራኬ መስጠት ነበር።

በጣም በቅርብ፣ አሁን ባለፈው ህዳር የሚያምረውን አዲስ የአሪዞና ፎኒክስ ቤተመቅደስ ቡራኬ የመስጠት እድል ነበረኝ። ፕሬዘዳንት ዴይተር ኤፍ ኡክዶርፍ፣ ሽማግሌ ዳሊን ኤች ኦክስ፣ ሽማግሌ ሪቻርድ ጄ ማየንስ፣ እና ሽማግሌ ላይን ጂ ሮቢንስ አብረውኝ ነበሩ። ከቡራኬው በፊት ባለው ምሽት፣ከቤተመቅደስ አውራጃ 4000 የሚሆኑ ወጣቶቻችን በአስደናቂ የባህል ክብረበአል የሚያምር ትእይንት አቀረቡ። በቀጣዩ ቀን በሶስት ቅዱስ እና አነሳሽ ክፍለ ጊዜያት ቤተመቅደሱ ቡራኬ ተሰጠው።

የቤተመቅደስ ግንባታዎች የቤተክርስቲያን እድገት በጣም ግልፅ ማሳያ ናቸው። በአሁኑ ወቅት 144 በአገልግሎት ላይ ያሉ ቤተመቅደሶች በአለም ላይ አሉን፣ 5 እንደገና እየተገነቡ እና ሌላ 13 አዲስ እየተሰሩ ነው። በተጨማሪም፣ ቀደም ብለው የተዋወቁ 13 ቤተመቅደሶች ግንባታ ከመጀመራቸው በፊት በተለያየ የዝግጅት ደረጃ ላይ ናቸው። በዚህ አመት 2 ቤተመቅደሶችን እንደ ገና ቡራኬ ለመስጠት እና 5 ለመጨረስ የታቀዱ አዲስ ቤተመቅደሶችን ቡራኬ ለመስጠት እናስባለን።

‎ላለፉት ሁለት አመታት፣ ከዚህ በፊት እንደሚገነቡ ማስታወቂያ የተደረጉትን ቤተመቅደሶች ለመፈፀም በምናደርገው ጥረት ላይ በማተኮር፣ ተጨማሪ ቤተመቅደሶችን መገንባት አቁመን ነበር። በዚህ ጠዋት ግን በሚከተሉት ቦታዎች ላይ የሚገነቡትን ሶስት ቤተመቅደሶች ለማስተዋወቅ እደሰታለሁ፥ በአቢጃን፣ አይቭሪ ኮስት፤ በፖርት ኦ ፕሪንስ፣ ሄቲ፤ እና በባንኮክ፣ ታይላንድ። በእነዚህ ክልሎች ውስጥ ለሚገኙ፣ እንዲሁም ቤተመቅደሶች በሚገኙበት በአለም ክፍሎች በሙሉ ለሚገኙ አባላቶቻችን ምን አይነት በረከቶች ይጥብቋቸዋል።

ፍላጎትን መመዘን እና ለተጨማሪ ቤተመቅደሶች ቦታ መፈለግ ቀጣይነት ያለው ስራ ነው፣ ምክንያቱም የሚቻለውን ያህል ሁሉም አባላት ያለ ትልቅ የጊዜ እና የወጪ መስዋእትነት ቤተመቅደስ እንዲካፈሉ እንፈልጋለን። ከዚህ በፊት እንዳደረግነው፣ በዚህ ጉዳይ ውሳኔዎች ሲተላለፉ ለእናንተ እናሳውቃለን።

ቤተመቅደሶችን ሳስብ፣ በእነርሱ ውስጥ ስለምንቀበላቸው በረከቶች አስባለሁ። በቤተመቅደስ በሮች ስንገባ፣ የአለምን ጥፋት እና ግራ መጋባት ከኋላችን እንተዋለን። በዚህ ቅዱስ ቦታ ውስጥ፣ ውበት እና ስርአትን እናገኛለን። ለነፍሳችን እረፍት እና ከህይወታችን ሀሳቦች ፋታን እናገኛለን።

ቤተመቅደስ ስንካፈል፣ የመንፈሳዊነት ስፋት እና የሰው ልብ ውስጥ ሊመጣ ከሚችል ከማንኛውም ሌላ ስሜት የሚልቅ የሰላም ስሜት ወደ እኛ ሊመጣ ይችላል። አዳኝ የተናገረውን እነዚህን ቃላት እውነተኛ ትርጉም እናገኛለን፤ “ሰላምን እተውላችኋለሁ፣ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ፣… ልባችሁ አይታወክ አይፍራም።”1

ይሄ ሰላም የትኛውም ልብ ውስጥ ሊሰራጭ ይችላል—ማለትም የተረበሹ ልቦች፣ በሀዘን የተቃጠሉ ልቦች፣ ግራ መጋባት የሚሰማቸው ልቦች፣ ለእርዳታ የሚማፀኑ ልቦችም ቢሆኑ።

በቅርብ አንድ ወጣት ወንድ ልቡ ለእርዳታ በመማፀን ቤተመቅደስ ሲካፈል እራሴ አስተዋልኩ። ከብዙ ወራት በፊት በደቡብ አሜሪካ ሚስኦን ውስጥ ለማገልገል ጥሪ ተቀብሏል። ቢሆንም፣ ለረጅም ጊዜ ቪዛው ስለዘገየ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ እንዲያገለግ እንደገና ተመደበ። በዋናው ጥሪ ቦታ ላይ ማገልገል ባለመቻሉ ቢበሳጭም፣ በአዲሱ ጥሪው ጠንክሮ ሰራ፣ በአቅሙ የተቻለውን ያህል ለማገልገል በቁርጠኝነት ሰራ። ሆኖም፣ ወንጌል ከማካፈል ይልቅ ጥሩ ጊዜ ለማሳለፍ የበለጠ ፍላጎት ያላቸው በመሰለው ሚስኦኖች ባጋጠመው አሉታዊ ተሞክሮ ተስፋ ቆረጠ።

ከጥቂት አጭር ወራት በኋላ ይሄ ወጣት በከፊል ፓራላይዝ ባደረገው ከባድ የጤና ችግር ተሰቃየ፣ እና በህክምና ፍቃድ ወደ ቤቱ ተላከ።

ከጥቂት ወራት በኋላ ወጣቱ ሙሉ በሙሉ ተፈወሰ፣ እና ፓራላይዙ ተወገደ። እንደገና እንደ ሚስዎናዊ ማገልገል እንደሚችል ተነገረው፣ ያም የየቀን ፀሎቱ በረከት ነበር። አናዳጁ ዜና ትቶት ወደመጣው ተመሳሳይ ሚስዎን መመልስ ነበር፣ ያም የአንዳንድ ሚስዎኖች ባህሪያት እና አመለካከቶች መሆን ካለባቸው ያነሰ ንቁ እንደነበር የተሰማው ቦታ ተመልሶ መሄዱ ነበር።

ቤተመቅደስ የመጣው እንደ ሚስዎን ጥሩ ተሞክሮ ሊኖረው እንዲችል መፅናናትን እና ማረጋገጫን ለመሻት ነበር። ይሄ የቤተመቅደስ ጉብኝት ወንድ ልጃቸው ያስፈለገውን እርዳታ ይሰጠው ዘንድ ወላጆቹም ፀልየው ነበር።

ክፍለጊዜውን ተከትሎ ወጣቱ ወደ ሰለስቲያል ክፍል ሲገባ፣ ወንበር ላይ ተቀመጠ እና ከሰማይ አባቱ ምሬትን ለማግኘት መፀለይ ጀመረ።

ከጥቂት ጊዜ በኋላ ወደ ሰለስቲያል ክፍል የገባው ሌላው ወጣት ወንድ ስሙ ላንዶን ነው። ወደ ክፍሉ እየተራመደ ሲገባ፣ አትኩሮቱ ወዲያው ወንበር ላይ ወደተቀመጠው ወጣት ተስቦ ነበር፣ አይኖቹን ጨፍኗል እና በእርግጥም እየፀለየ ነው። ላንዶን ከወጣቱ ጋር መነጋገር እንዳለበት ያልተሳሳተ መነሳሳት ተቀበለ። ላለመረበሽ በማመንታት፣ ለመጠበቅ ወሰነ። ብዙ ደቂቃዎች ካለፉ በኋላ ወጣቱ አሁንም በጸሎት ላይ ነበር። ላንዶን መነሳሳቱን ከዛ በላይ ማሳለፍ እንደማይችል አወቀ። ወደ ወጣቱ ጠጋ አለ እና በዝግታ ትከሻውን ነካው። ወጣቱ አይኑን ከፈተ፣ በመረበሹ ተደናገረ። ላንዶን በዝግታ እንዲህ አለ፣ “ከአንተ ጋር መነጋገር እንዳለብኝ ተሰማኝ፣ ለምን እንደሆነ በትክክል ባላውቅም።”

መነጋገር ሲጀምሩ፣ ወጣቱ የልቡን አውጥቶ ለላንዶን ነገረው፣ ስለ ሁኔታው እና ሚስዎኑን አስመልክቶ መፅናናት እና ብርታት ለመቀበል ስላለው ፍላጎት አብራራ። ላንዶን፣ ከአንድ አመት በፊት ከነበረው ስኬታማ ሚስዎን ተመልሶ የነበረ ነው፣ ስለእራሱ የሚስዎን ተሞክሮ ነገረው፣ ያጋጠሙትን ችግሮች እና ጭንቀቶች፣ ወደ ጌታ ለእርዳታ የዞረበትን ሁኔታ፣ እና የተቀበላቸውን በረከቶች ነገረው። ቃላቶቹ አፅናኝ እና አረጋጊ ነበሩ፣ እና ለሚስዎኑ ያለው ስሜት ተላላፊ ነበር። ቀስ በቀስ፣ ፍርሀቱ ጋብ ሲል፣ የሰላም ስሜት ወደ ወጣቱ መጣ። ፀሎቱ መመለሱን ሲያስተውል ጥልቅ አመስጋኝነት ተሰማው።

ሁለቱ ወጣት ወንዶች አብረው ፀለዩ፣ ወደ እርሱ የመጣውን መነሳሳት በማዳመጡ በመደሰት ላንዶን ለመሄድ ተዘጋጀ። ለመሄድ ሲቆም፣ ወጣቱ ላንዶንን እንዲህ ጠየቀው፣ “የት ነበር ሚስዎንህን ያገለገልከው?” እስከዚህ ጊዜ፣ ያገለገሉበትን ሚስዎን ስም አንዳቸውም ለሌላው አላነሱም ነበር። ላንዶን የሚስዎኑን ስም መልስ ሲሰጥ፣ በወጣቱ አይኖች ላይ እንባዎች መነጩ። ላንዶን ያገለገለው ሚስዎን ወጣቱ ከሚመለስበት ጋር አንድ ነው!

በቅርብ ለእኔ በመጣ ደብዳቤ፣ የወጣቱን የመጨረሻ ቃለት ላንዶን ለእኔ አካፈለኝ፤ “የሰማይ አባት እንደሚባርከኝ እምነት ነበረኝ፣ ነገር ግን ከእራሴ ሚስዎን ሰው እንዲረዳኝ ይልካል ብዬ በፍፁም አላሰብኩም። ሁሉም መልካም እንደሚሆን አሁን አውቄአለሁ።”2 የቀና ልብ ትሁት ጸሎት ተሰማ እና ተመለሰ።

ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣ በህይወታችን ፈተናዎች ይኖሩብናል፤ መከራዎች እና አስቸጋሪ ሁኔታዎች ይኖሩብናል። ወደ ቤተመቅደስ ስንሄድ፣ እዚያ የምንፈፅማቸውን ቃል ኪዳኖች ስናስታውስ፣ እነዚያን ፈተናዎች ለማለፍ እና መከራዎችን ለመቋቋም በተሻለ ሁኔታ እንችላለን። በቤተመቅደስ ሰላም ማግኘት እንችላለን።

የቤተመቅደስ በረከቶች ዋጋቸው ሊገመት አይችልም። በህይወቴ ሁል ቀን አመስጋኝ ከሆንኩበት አንዱ ውድ ሚስቴ፣ ፍራንሲስ፣ እና እኔ በቅዱሱ መሰዊያ ላይ ተንበርክከን ለዘለአለም የሚያስረንን ቃልኪዳን ስንገባ የተቀበልነው ነው። እርሷ እና እኔ እንደገና አንድ ላይ እንደምንሆን ባለኝ እውቀት ከማገኘው ሰላም እና መፅናናት የበለጠ ውድ በረከት ለእኔ የለም።

ቤተመቅደስ የማምለክ መንፈስ እንዲኖረን፣ ለእርሱ ትእዛዛት ታዛዥ እንድንሆን፣ እና የጌታችንን እና የአዳኛችንን፣ የኢየሱስ ክርስቶስን መንገድ በጥንቃቄ እንድንከተል የሰማይ አባታችን ይባርከን። እርሱ ቤዛችን እንደሆነ እመሰክራለሁ። እርሱ የእግዚአብሔር ልጅ ነው። እርሱ በዚያ በፋሲካ ማለዳ ከመቃብር የመጣው ነው፣ ለእግዚአብሔር ልጆች በሙሉ የዘለአለም ህይወት ስጦታን አምጥቷል። በዚህ በሚያምር ቀን፣ ያንን የክንውን ክስተት ስናከብር፣ ለሰጠን ታላቅ እና ድንቅ ስጦታው የምስጋና ፀሎት እናቅርብ። ይሄ ይሆን ዘንድ፣ በቅዱስ ስሙ እፀልያለሁ፣ አሜን።

አትም