2016 (እ.አ.አ)
በሰንበት ቀን ምስጋና
ኖቬምበር 2016


የቀዳሚ አመራር መልእክት፣ ህዳር 2016 (እ.አ.አ)

በሰንበት ቀን ምስጋና

ለኋለኛው ቀን ቅዱሳን፣ ሰንበት የምስጋና እና የፍቅር ቀን ነው።

በኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ውስጥ በአለም አቀፍ የምትገኙ ውድ ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣ ፕሬዘደንት ቶማስ ኤስ. ሞንሰን በዚህ በሰንበት ቀን በጉባኤው ንግግር እንዳቀርብ ስለጠየቁኝ አመሰግንለሁ። መንሰፍ ቅዱስ ቃላቴን ወደ ልባችሁ ይዞ እንዲገባ እጸልያለሁ።

ዛሬ ስለልብ ስሜቶች ለመናገር እፈልጋለሁ። ከማተኩርበት አንዱ ምስጋና ነው—በተለይም በሰንበት ቀን።

ለብዙ ነገሮች ምስጋና አለን፥ ለእንግዳ ሰው ደግነት፣ ሲርበን ለምንበላው፣ ማእበሎች ሲመጡ በበላያችን ለሚገኘው ለደረቀው ጣራ፣ ለተፈወሰው የተሰበረ አጥንት፣ እና ከልብ ለሚያለቅሰው አዲስ ለተወለደ ልጅ። በእንደዚህ አይነት ጊዜዎች ምስጋና ሲሰማን ብዙዎቻችን እናስታውሳለን።

ለኋለኛው ቀን ቅዱሳን፣ ሰንበት እንደዚህ አይነት ጊዜ፣ እንዲሁም የምስጋና እና የፍቅር ቀን ነው። በ1831 (እ.አ.አ) በጃክሰን ካውንቲ፣ ምዙሪ ውስጥ ጌታ ቅዱሳን ጸሎታቸውን እና ምስጋናቸውን ወደሰማይ እንዲልኩ ምሬት ሰጠ። ቀዳሚዎቹ ቅዱሳን ሰንበትን እንዴት እንደሚጠብቁ እና እንዴት እንደሚጾሙና እንደሚጸልዩ ራዕይ ተሰጥቷቸው ነበር።1

እነርሱ፣ እናም እኛ፣ በሰንበት እንዴት ጌታን እንደምናመልክ እና ምስጋና እንደምንሰጥ ተነግሮናል። እንደምታውቁት፣ ከሁሉም በላይ አስፈላጊ የሚሆነው ለስጦታዎች ሰጪው ያለን ስሜት ነው። በዚህም በሰንበት እንዴት ምስጋና እንደምንሰጥ እና እንደምናፈቅር ጌታ የሰጠው ቃላት ናቸው፥

“እንዲህ በማለት ትእዛዛትን እሰጣቸዋለሁ፥ ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ፣ በፍጹም ነፍስህ፣ በፍጹም አዕምሮህ፣ እና በፍጹም ሀይልህ ውደድ፤ እናም በኢየሱስ ክርስቶስ ስምም አገልግለው። …

“ጌታ አምላክህን በሁሉም ነገሮች አመስግን።

“የተሰበረ ልብን እና የተዋረደ መንፈስን መስዋዕት አድርገህ ለጌታ አምላካህ በፅድቅ አቅርብ።”2

እና ቀጥሎም የስጦታ ሰጪዎች የሆኑትን የሰማይ አባትን እና ኢየሱስ ክርስቶስን ለማፍቀርና ለማምስገን ያለመቻልን አደጋ ጌታ አስጠናቀቀን፤ “በሁሉም ነገሮች ውስጥ የእርሱ እጅ እንዳለበት ካለመመስከር እና ትእዛዙን ካለማክበር በቀር፣ በምንም መንገድ ሰው እግዚአብሔርን አያስቀይመውም፣ ወይም በማንም ላይ ቁጣው አይቀጣጠልም።”3

ይህን የምታዳምጡ ብዙዎቻችሁ ስታስታውሱ እና እግዚአብሔርን ለበረከቶች ስታመስግኑ በሰንበት ቀን ደስታን አግኝታችኋል። የተለመደውን መዝሙር ታስታውሳላችሁ፥

በህይወት ነፋሶች ላይ በአውሎ ንፋስ ስትወረወሩ፣

ተስፋ ስትቆሮጡ፣ ሁሉም ጠፍቷል ብለን ስናስብ፣

በረከቶቻችሁን ቁጠሩ፤ አንድ በአንድ ስም ስጧቸው፣

እናም ጌታ ያደረገው ያስገርማችኋል።

በረከታችሁን ቁጠሩ

አንድ በአንድ ስም ስጧቸው።

በረከታችሁን ቁጠሩ

እግዚአብሔር ምን እንዳደረገ እዩ። …

የህይወት ችግር ሸከም አለባችሁን?

እንድትሸከሙት የተጠየቃችሁት መስቀል ከባድ ይመስላልን?

በረከታችሁን ቁጠሩ፣ ጥርጣሪዎች በሙሉ ይበራሉን፣

እናም ቀኑ ሲቀጥል ትዘምራላችሁና።4

የመንከባከቢያ ሸክም በከበደባቸው ታማኝ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን በደብዳቤ እና በጉብኝት እሰማለሁ። እንዳንዶች፣ ለራሳቸውም ቢሆን፣ ሁሉም የጠፋ ይመስልቸዋል። ጥርጣሪ እንዲጠፋ እና በልባችሁ፣ በልዩም በምትገኙበት በእያንዳንዱ የቅዱስ ቁርባን ስብሰባ ውስጥ፣ መዘመር እንድትጀምሩ እንዲያደርግ ተስፋዬ እና ጸሎቴ ነው።

እናንተ ምስጋና የሚኖራችሁ አንዱ በረከት ቢኖር እናንተ በቅዱስ ቁርባን መገኛታችሁ ነው፣ በእርሱ ስም ከአንድ ወይም ሁለት በላይ ከሆኑ ደቀመዛሙርቱ ጋር በመሆን። ከአልጋዎቻቸው መነሳት ያቃታቸው አንዳንድ በቤት ውስጥ ይገኛሉ። እናንተ በምትገኙበት ለመሆን የሚፈልጉ ግን በሆስፒታል ውስጥ እና በህብረተሰብ ደህንነት እያገለገሉ የሚገኙ ወይም የራሳቸውን ህይወት አደጋ ላይ በመጣል በምድረበዳ ወይም በጫካ ውስጥ የሚገኙ አንዳንዶች አሉ። ከአንድ ሌላ ቅዱሳን ጋር ለመሰብሰብ እና ቅዱስ ቁርባንን ለመቀበል በመቻላችሁ ነው ለእግዚአብሔር ደግነት ምስጋና እና ፍቅር ሊሰማችሁ የሚገባችሁ።

በነቢዩ ዮሴፍ ስሚዝና በዳግም በተመለሰው ወንጌል፣ ሁለተኛው የምንቆጥረው በረከት ቢኖር ስልጣን ባለው የእግዚአብሔር አገልጋይ የተዘጋጀውን፣ የተባረከውን፣ እና የተሰጠውን ቅዱስ ቁርባን በየሳምንቱ ለመቀበል ላለን እድል ነው። በትሁት የክህነት ተሸካሚ የቀረቡት የቅዱስ ቁርባን ጽሎቶች በሰማይ አባት እንደሚከበሩ በመንፈስ ቅዱስ ሲረጋገጥም ምስጋና ሊኖራችሁ ትችላላችሁ።

ለመቁጠር ከምንችላቸው በረከቶች ሁሉ ታላቁ፣ ቅዱስ ቁርባን ስንቀበል የሚመጣው የምህረት ስሜት ነው። ከሀጢያታችን እንድንጸዳ ዘለአለማዊ መስዋዕት ላደረገው ለአዳኝ ከሁሉም በላይ የሆነ ታላቅ ፍቅር እና ምስጋና ይሰማናል። ዳቦውን እና ውሀውን ስንቀበል፣ ለእኛ እንደተሰቃየ እናስታውሳለን። ለእኛ ላደረገው ምስጋና ሲሰማንም፣ እርሱ ለእኛ ያለው ፍቅር እናም ለእርሱ ያለን ፍቅርም ይሰማናል።

የምንቀበለው የፍቅር በረከት “[እርሱን ሁልጊዜ ለማስታወስ]”5 ያለብንን ትእዛዝ ለመጠበቅ ቀላል ያደርገዋል። የሰማይ አባት እናንተ ለገባችሁት ቃል ኪዳን ታማኝ ከሆናችሁ ከእናንተ ጋር ሁልጊዜ እንደሚገኝ ቃል ለገባበት መንፈስ ቅዱስም ፍቅርና ምስጋና፣ እኔ እንደሚሰማኝ፣ እናንተም ይሰማችኋል። እነዚያን በረከቶች በሙሉ በእያንዳንዱ እሁድ መቁጠር እና ምስጋና ሊሰማን ይችላል።

ሰንበትም የሰማይ አባት ልጆችን ለማፍቀር እና ለማገልገል የገባችሁትን ቃል ኪዳን ለማስታወስ ፍጹም የሆነ ቀን ነው። ይህን ቃል ኪዳን ማሟላትም በተጨማሪ በወንድሞቻችሁ እና በእህቶቻችሁ መካከል እምነት እና ፍቅርን ለመገንባት ከክፍል ወይም ከቡድን ጋር በሙሉ የልብ አላማ መሳተፍንም ያካትታል። ይህም በተጨማሪ በደስታ የምትቀበሉትን ማንኛውንም ጥሪ ማሟላት ያካትታል።

በባውንቲፉል፣ ዩታ ውስጥ በዲያቆን ቡድን እናም በአይደሆ የሰንበት ትምህርት ክፍል ውስጥ ስላስተማርኩባቸው ብዙ እሁዶች አመስጋኝ ነኝ። ዋናው ሀላፊነቴ መጫወቻዎችን መምረጥ እና መስጠት በሆነበት በህጻናት ክፍል ውስጥ እንደባለቤቴ ረጂ ያገለግልኩበትንም አስታውሳለሁ።

የእኔ አገልግሎት ለሰማይ አባት ልጆች ጠቃሚ እንደነበር በመንፈስ ያወቅኩት ከአመታት በፊት ነበር። በሚያስገርመኝ ሁኔታም፣ አንዳንዶቹ በእነዛ የሰንበት ቀናት መምህርን ለማገልገል የምጥረውን ከብዙ አመቶች በኋላ ያስታውሳሉ እናም ያመሰግኑኝ ነበር።

በሰንበት የምንሰጠውን አገልግሎት ውጤት በብዙ ጊዜ እኛ ለማየት እንደማንችል ሁሉ፣ የሌሎች የጌታ አገልጋዮች የተጠራቀሙ ውጤት ለማየት አንችል ይሆናል። ነገር ግን ጌታ በታማኝ እና ትሁት አገልጋዮቹ አማካኝነት በጸጥታ እና በትንሽ ትእይንት ግርማዊ ሺህ አመት ወደሆነው መንግስቱን እየገነባት ነው። አዳጊ የሆነውን ታላቅነት ለማየት መንፈስ ቅዱስ ያስፈልጋል።

በኒው ጀርዚ ቅርጫፍ ውስጥ ከትንሽ አባላት እና አንድ ቤተሰብ ጋር ለቅዱስ ቁርባን ስብሰባ በመሄድ ነበር ያደግኩት። ከሰባ አምስት አመት በፊት፣ በፔንስልቬኒያ እና በኒው ጀርዚ ውስጥ በቤተክርስቲያኗ በብቻነት በተገነባ የጸሎት ቤት ውስጥ በፊለደልፊያ ነበር የተጠመቅኩት። በፕርስንተን ውስጥ አንድ ትንሽ ቅርንጫፍ በነበረበት፣ አሁን ሁለት ትትልቅ አጥቢያዎች አሉ። ከትንሽ ቀናት በፊት፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች ከፊለደልፊያ፣ ፔንስልቬንያ ቤተመቅደስ መመሪቂያ በፊት ባለው በአል ተጫውተው ነበር።

እንደ ወጣትነቴ፣ በአልበከርኪ፣ ኒው ሜክሲኮ ውስጥ በምትገኘው ብቸኛ ቤተክርስቲያን ውስጥ እንደ አውራጃ ሚስዮን እንዳገለግል ተጠርቼ ነበር። ዛሬ ቤተመቅደስ እና አራት ካስማዎች ይገኛሉ።

ከአልበከርኪ ወደ ካምብሪጅ፣ ማሳቹሴት ለትምህርት ሄድኩኝ። በዚያም አንድ ቤተክርስቲያን እና ማሳቹሴት እና ሮድአይላንድን በሙሉ ያካተተ አንድ አውራጃ ነበር። በዚያ ውብ ከተማ ኮረብታ ላይ እየነዳሁ ወደ ትንሿ ቅርንጫፎች ለቅዱስ ቁርባን ስብሰባ እሄድ ነበር፣ አብዛኛዎቹም የኪራይ ህንጻዎች ወይም ትትንሽ ቤቶች ነበሩ። አሁን የእግዚአብሔር ቤተመቅደስ በቤልሞንት እና በሀገሩ የተሰራጩ ካስማዎች ይገኛሉ።

በዚያ ጊዜ በግልጽ ለማየት ያልቻልኩት ጌታ በነዚያ የቅዱስ ቁርባን ስብሰባዎች እና በቤቶቻቸው ውስጥ መንፈሱን እያፈሰሰባቸው እንደነበር ነው። ይህም ይሰማኛል፣ ነገር ግን እንዴት የተስፋፋ እንደነበረ እና ጌታ መንግስቱን ለመገንባት እና ግርማ ለመስጠት ያለመበትን እቅድ ጊዜ አላውቅም ነበር። ነቢይ፣ በራዕይ፣ አሁን ለማየት የምንችለውን እና የሚሰማንን አይቶና መዝግቦ ነበር። ኔፊ ቁጥራችን ታላቅ አይሆንም ብሏል፣ ነገር ግን የነዚህ ተጨማሪ ብርሀኖች የገፅታ ማሳያሆች ይሆናሉ፤

“እናም እንዲህ ሆነ የእግዚአብሔር በግ ቤተክርስቲያንን ተመለከትኩ፣ ቁጥሯ ጥቂት ነበሩ። …

“እናም እንዲህ ሆነ እኔ ኔፊ በበጉ ቤተክርስቲያን ቅዱሳንና በምድር ገፅ ላይ ሁሉ በተበተኑት የጌታ የቃልኪዳን ህዝቦች ላይ የእግዚአብሔር በግ በኃይል ሲወርድ ተመለከ ትኩ፤ እናም እነርሱ ፅድቅንና የእግዚአብሔ ርን ኃይል በታላቅ ክብር የታጠቁ ነበሩ።”6

በዚህ ዘመን ውስጥም፣ ወደፊት ያለውን የኛን ሁኔታ እና እድል የሚገልፅ እንዲህ አይነት የትንቢት መግለጫ በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ውስጥ ተመዝግበዋል።

“አብ በእጆቹ ምን አይነት ታላቅ በረከቶች እንዳለው እና ለእናንተም እንዳዘጋጀ ገና አልገባችሁም፤

“እናም ሁሉንም ነገሮች አሁን መሸከም አትችሉም፤ ይህም ቢሆን፣ ተደሰቱ፣ እንደሚገባችሁ እመራችኋለሁና። መንግስት የእናንተ ናት እናም በእዚያም ያሉ በረከቶች የእናንተ ናቸው፣ እናም የዘለአለም ባለጠግነትም የእናንተ ናቸውና።

ጌታ ቃሎቹን ሰቶናል “ሁሉንም ነገሮች በአመስጋኝነት የሚቀበሉ ሁሉ ክብራማ ይደረገሉ፤ እናም የዚህ ምድር ነገሮች ይጨመርላቸዋል።”7

ለበረከቶች እና ለእግዚአብሔር ፍቅር ያለ የሚቀይር የምስጋና እድገት በቤተክርስቲያኗ ውስጥ ሲጨምር ተሰምቶኛል። የእምነታቸው ፈተና ባላበት፣ ወደፊት ለመሄድ እንኳን እግዚአብሔርን በሚለምኑበት ጊዜ ይህ በቤተክርስቲያኗ አባላት መካከል በፍጥነት የሚያድግ ይመስላል።

የአልማ ህዝብ ለመሸከም የማይችሉትን ሸክም በጣለባቸው በክፉው በአሙሎን ገዢነት ስር እንደነበረው እኛም በታላቅ ችግር ጊዜዎች ውስጥ እያለፍን ነን፥

“እናም እንዲህ ሆነ የጌታ ድምፅ በስቃያቸው እንዲህ በማለት መጣ፥ እራሳችሁን አቅኑ እናም መልካም መፅናኛ ይኑራችሁ፤ ከእኔ ጋር የገባችሁትን ቃል ኪዳን አውቀዋለሁና፤ እናም ከህዝቤ ጋር ቃል ኪዳን እገባለሁ እናም ከባርነት አስለቅቃቸዋለሁ።

“እናም ደግሞ በትከሻችሁ ላይ ያለውን ሸክም አቃልልላችኋለሁ፣ በጀርባችሁም እንኳን ሊሰማችሁ እንዳይቻላችሁ፤ በባርነት በነበራችሁ ጊዜም ቢሆን፣እናም ይህንን የማደርገው ከዚህ በኋላ ለእኔ ምስክርነት እንድትቆሙ ነው፤ እናም እኔ ጌታ እግዚያብሄር በእውነት በመከራቸው ጊዜ ህዝቤን እንደምጎበኝ ታውቁ ዘንድ ነው።

“እናም አሁን እንዲህ ሆነ በአልማና በወንድሞቹ ላይ የሆነው ሸክም ቀለለላቸው፣ አዎን፣ ሸክማቸውን ማቅለል እንዲችሉ እናም በደስታና በትዕግስት ለጌታ ፈቃድ እንዲሰጡ ጌታ ብርታትን ሰጥቷቸዋል።”8

እኔ እና እናንተ፣ ከባድ በሚሆንበት ጊዜም፣ የጌታን ትእዛዛት ስናከብር፣ ለእኛ ላደረገው የምስጋና ጸሎት እንደሰማ እና በታማኝነት ለመፅናት ጥንካሬ እንዲሰጠን ለምንጸልየው መልስ እንደሚሰጥ ምስክሮች ነን። እናም ከአንድ ጊዜ በላይ እርሱ እኛን ደስተኛ እና ጠንካራ አድርጓናል።

ወደፊት ላሉት ፈተናዎች ምስጋና እና ጥንካሬ ለራሳችሁ እና ለሌሎች ለማሳየት በዚህ ሰንበት ለመኖር እና ለማምለክ ምን ማድረግ እንደምትችሉታስቡም ይሆናል።

በግል እና በቤተሰብ ጸሎት እግዚአብሔር ላደረገላችሁ በሙሉ በማመስገን ዛሬ መጀመር ትችላላችሁ። እርሱን እና ሌሎችን ለማገልገል ጌታ ምን እንድታደርጉ እንደሚፈልጋችሁ ለማወቅ መጸለይ ትችላላችሁ። በተለይም፣ መንፈስ ቅዱስ ጌታ እንድትሄዱላቸው የሚፈልጋችሁን ብቸኛ ስለሆነ ወይም እርዳታ ስለሚያስፈልገው ሰው እንዲነግራችሁ መጸለይ ትችላላችሁ።

ጸሎታችሁ መልስ እንደሚያገኝ፣ እና በተቀበላችሁት መልስ ስትሰሩም፣ በሰንበት ደስታ እንደምታገኙና በልባችሁ ደስታ እንደሚኖራችሁ እመሰክራለሁ።

እግዚአብሔር አብ ያውቃችኋል እናም ያፈቅራችኋል። አዳኝም ለእናንተ ባለው ፍቅር ምክንያት ለእናንተ የኃጢያት ክፍያን አድርጓል። ልክ ለእርሱ በታዩበት ጊዜ የነቢዩ ዮሴፍን ስም እንዳወቁት የእናንተንም ስም ያውቃሉ። ደግሞም ይህች የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን እንደሆነች እና ከእግዚአብሔር ጋር የገባችሁትን እና የምታድሱትን ቃል ኪዳን እንደሚያከብር እመሰክራለሁ። ፍጥረታችሁም ተቀይሮ እንደ አዳኝ ትሆናላችሁ። ከፈተናዎች እና እውነትን ከመጠራጠር ስሜትም ትገደባላችሁ። በሰንበት ደስታን ታገኛላችሁ። ስለዚህም ቃል ኪዳን የምገባው በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው፣ አሜን።

አትም