2017 (እ.አ.አ)
ጌታን ሁልቀን ማስታወስ
ጥቅምት 2017 (እ.አ.አ)


ወጣቶች

ጌታን ሁልቀን ማስታወስ

ጓደኞች፣ የቤት ስራዎች ሃላፊነት፣ የትምህርት ቤት ስራዎች፣ ቲቪ—ብዙ ነገሮች የኛን ትኩረት ይጠይቃሉ። ነገር ግን በየሳምንቱ፣ የሰማይ አባትን “[የሱን ልጅ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ] ሁልጌዜ እንደምናስታውስ” ቃል እንገባለታለን (ት እና ቃ 20፥79)።

ፕሬዘደንት አይሪንግ ወደ አዳኝን እንድናስታውስ የሚረዱንን የለት ተለት ምርጫዎችን መምረጥ እንደምንችል ተናገሩ። በእያንዳንዱ ቀን አዳኝን አብዝታችሁ ለማስታወስ በዚህ ወር ግብ ለማድረግ አስቡበት። ከእርሱ ጋር ያላችሁን ዝምድና ለመገንባት ካሌንደር አዘጋጁ እናም በቀን አንድ ነገር ለማድረግ ወስኑ። ፕሬዚዳንት አይሪንግ ቅዱሳት መጽሃፍትን ማንበብ፣ በእምነት መጸለይ እና አዳኝን እና ሌሎችን ማገልገል እንደምንችል ዘርዝረዋል። ደግሞም የለት ተለት ሁኔታን በማስታወሻ መመዝገብ፣ የቤተክርስቲያን ስብሰባዎች ላይ መገኘት፣ የጠቅላይ ጉባዬ ንግግሮችን ማዳመጥ፣ ቤተመቅደስ መሄድ፣ መዝሙሮችን መዘመር አሉ—ዝርዝሩም ይቀጥላል። በየለቱ ጌታን ስናስታውስ፣ ፕሬዝዳንት አይሪንግ “ በረከቶቹ በዝግታ እና ያለማቋረጥ እንደሚመጡ እና የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀመዝሙር እንድንሆን እንደሚያዘጋጀን” ቃል ገብተዋል።

አትም