2017 (እ.አ.አ)
እውነተኛ ደቀ መዝሙራን መሆን
ጥቅምት 2017 (እ.አ.አ)


የቀዳሚ አመራር መልእክት፣ ጥቅምት 2017 (እ.አ.አ)

እውነተኛ ደቀ መዝሙራን መሆን

በእያንዳንዱ የቅዱስ ቁርባን ስብሰባ ላይ፣ ሁልጊዜ አዳኝን እንደምናስታውስ እና የሱም መንፈስ ከኛ ጋር እንዲሆን ትእዛዛቱን ለመጠበቅ ቃል የመግባት እድሉ አለን። ( ሞሮኒ 4፥3፤5፥2፤ ት. እና ቃ. 20፥77፣ 79ተመልከቱ)። የሱን ስም በላያችን ላይ ስንወስድ እርሱን ማስታወስ ሁልጊዜ በተፈጥሮ ወደ እኛ ይመጣል። በብዙ መንገዶች ይህንን እናደርጋለን ነገር ግን በተለይ ደግሞ የምናደርገው በስሙ ሌሎችን ስናገለግል፣ ቅዱስ ቃላቱን ስናነብ፣ እና እርሱ እኛ ምን እንድናደርግ እንደሚሻ ለማወቅ ስንጸልይ ነው።

ለእኔ የተከሰተው ለአንድ ወጣት ጥምቀትን በማደርግበት ወቅት ነበር። በአዳኝ በተሾሙ አገልጋዮች የሚስዮን አገልጋይ እንድሆን እና ወንጌሉን እንዳስተምር እናም ስለ እርሱ እና ስለ እውነተኛው ቤተክርስቲያን እንድመሰክር እንደተጠራሁ አወኩኝ። የአገልግሎት አጋሪዬ እና እኔ ለወጣቱ ልጅ በኢየሱስ ክርስቶስ የሃጢያት ክፍያ ሃይል ምክንያት ንስሃ በአዳኝ ላይ ባለው እምነት ከገባ እና ስልጣን በተሰጣቸው አገልጋዮች ከተጠመቀ እንደሚነጻ ቃል ገባንለት።

ወጣቱን ከጥምቀት የገንዳ ውሃ ውስጥ ከፍ ሳደርገው በጆሮዬ ላይ “ንጹህ ነኝ፣ ንጹህ ነኝ” በማለት አንሾካሾከ። በዛ ቅጽበት፣ በዮርዳኖስ ወንዝ በመጥምቁ ዮሃንስ የተደረገውን የአዳኝን ጥምቀት አስታወስኩኝ። በተጨማሪም እንኳ፣ ትንሳኤ ባደረገውና በህይወት ያለውን የአዳኝን የማዳን ስራ ለዮሃንስ እንደሆነው በመንፈስ ቅዱስ ታጅቤ እየሰራሁ እንደሆነ አስታወስኩኝ።

ለእኔና ለእያንዳንድችን፣ አዳኝን ማስታወስ ካሉን የትውስታ እውቀት እና ከእርሱ ጋር ባሉን ተሞክሮዎች ከመመርኮዝ ይልቅ የበለጠ ሊሆን ይችላል። ይበልጥ ወደ እሱ በአሁኑ ወቅት እንድንቀርብ የሚያደርጉ ምርጫዎችን በየቀኑ ማድረግ እንችላለን።

ቀላሉ ምርጫ ቅዱሳት መጻህፍትን ማንበብ ሊሆን ይችላል። እንዲህ በማድረግ፣ ለእርሱ ቅርብ የመሆንን ስሜት ማግኘት እንችላለን። ለእኔ፣ መፅሐፈ ሞርሞንን በማነብበት ጊዜ ቅርብ የመሆን ስሜት አብዛኛውን ጊዜ ወደ እኔ ይመጣል። በሁለተኛ ኔፊ ካሉት ምዕራፎች ውስጥ በማነብበት በመጀመሪያ ደቂቅዎች ውስጥ፣ የኔፊንና የሌሂን ድምጾች በአይምሮዬ ውስጥ አዳኝን በግል እንደሚያውቁት ሲገልጹ ይሰማኛል። የቅርበት ስሜት ይመጣል።

ለእናንተ፣ ሌሎች የቅዱስ መጽሃፍት ቃሎች በተለይ ወደእርሱ ሊያቀርባችሁ ይችላል። ነገር ግን የትም ቢሆን መቼም የእግዚአብሄርን ቃላት በምታነቡበት ወቅት፣ በትህትና እና በቀና አመለካከት አዳኝን ስትመለከቱ፣ በለት ተለት ህይወታችሁ የእርሱን ስም በላያችሁ ለመውሰድ ያላችሁን መሻት ትጨምራላችሁ።

ያም መሻት በጌታ ቤተክርስቲያን ውስጥ የምትሰጡትን የአገልግሎት መንገድ ይቀይራል። ለእናንተ ትንሽ ጥሪ መስሎ የሚታየውን እንኳ እንዲያጎላው እርዳታ ለማግኘት የሰማይ አብን ተለምናላችሁ። የምትጠይቁትም እርዳታ ራስህን የመርሳት እና አዳኝ እናንተ እንድታገለግሏቸው ለተጠራችሁባቸው ሰዎች፣ ለእነርሱ የሚፈልገው ነገር ላይ ይበልጥ ትኩረት ለማድረግ ነው።

በልጆቻችን አገልግሎት ውስጥ ወንጌል ብቻ የሚያመጣውን ሰላም እነሱ እንዲያገኙ እንዴት ለመርዳት ማወቅ እንድችል በጸለይኩበት ጊዜ የእርሱ እጅ እና ቅርበት ተሰምቶኛል። በእነዚህ ጊዜያት፣ ውጤታማ ወላጅ ሆኖ መታየቱ ግድ አላለኝም፣ ነገር ግን ስለልጆቼ ውጤታማነትና ደህና መሆን በጥልቀት ግድ አለኝ።

አዳኝ ሊሰጣቸው የሚችለውን ነገሮች ለምናገለግላቸው ሰዎች የመስጠት ፍላጎት ወደሰማያዊው አባታችን የተማጽኖ፣ በእውነቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንድንጸልይ ያደርገናል። በዚህ መልኩ ስንጸልይ—በአዳኝ ስም፣ በእርሱ ላይ እምነትን በማድረግ—አብ ይመልሳል። እሱም መመሪያ፣ መጽናናትን፣ እና እኛን ለማበረታታት መንፈስ ቅዱስን ይልካል። መንፈስ ሁልጊዜ ስለ አዳኝ ስለሚመሰክር ( 3 ኔፊ 11፥32፣ 36፤ 28፥11፤ኤተር 12፥41ተመልከቱ)፣ ጌታን በሙሉ ልባችን፣ አእምሮ፣ እና ጥንካሬ የማፍቀር ያለን አቅም እየጨመረ ይሄዳል ( ማርቆስ 12፥30፤ሉቃስ 10፥27፤ት. እና ቃ. 59፥5 ተመልከቱ)።

በየቀኑ እና በየጊዜው የማስታወስ በረከት በዝግታ እና ያለማቋረጥ በምናገለግለው ጊዜ፣ ቃሉን ስንመገብ እናም በስሙ በእምነት ስንጸልይ ይመጣል። እናም ይህም ማስታወስ የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር ላይ ባለው መንግስቱ እና በኋላ ደግሞ በሚመጣው በክብር በተሞላው አለም እውነተኛ ደቀመዝሙር እንድንሆን ያዘጋጀናል።

አትም