2017 (እ.አ.አ)
ከመስመር የወጡትን በፍቅር ማቀፍ
ጥቅምት 2017 (እ.አ.አ)


የሴቶች የቤት ለቤት ጉብኝት ማስተማሪያ መልእክት፣ ጥቅምት 2017 (እ.አ.አ)

ከመስመር የወጡትን በፍቅር ማቀፍ

በጸሎት መንፈስ ይህንን መረጃ አንብቡት እና ምን እንደምታካፍሉ ለማወቅ የመንፈስ ምሪትን እሹ። የሴቶች መረዳጃ ማህበር እቅድን ማወቅ እንዴት የእግዚአብሔር ሴት ልጆችን ለዘለአለማዊ ህይወት በረከቶች ያዘጋጃል?

ምስል
Relief Society seal

እምነት ቤተሰብ እርዳታ

የቀዳሚ አመራር ሁለተኛ አማካሪ ፕሬዘደንት ዲየተር ኤፍ. ኡክዶርፍ እንዳሉት፣ “እውነታው ምንም ፍጹም ቤተሰቦች የሉም … ፣”። “ቤተሰባችሁ የትኛውም አይነት ችግሮች ቢጋፈጡም፣ ችግሩን ለመፍታት ምንም አይነት ነገር ብታደርጉም፣ የመፍትሄው መጀመሪያ እና መጨረሻ የክርስቶስ ንፁህ ፍቅር የሆነው ልግስና ነው።”1

ወንጌልን በሙሉነት ለማይከታተሉ፣ ሊንዳ ኬ. በርተን፣ የቀድሞ የጠቅላይ የሴቶች መረዳጃ ማህበር ፕሬዝዳንት የነበሩት እንዳሉት፥ “የሰማይ አባት ሁሉንም ልጆቹን ይወዳል። … የትም ቢሆኑ—በመንገዱም ሆነ ከመንገዱ ውጪ ያሉ—ወደቤት እንዲመለሱ ይወዳል።”2

“ሆኖም ግን ምንም ያህል [ልጆቻችሁ] ዓመጸኛ ቢሆኑም፣ … ስታናግሯቸው፣ በንዴት ውስጥ አታድርጉት፣ በመንቀፍም አታድርጉት፣ በመኮነን መንፈስ አታድርጉት፣” ብለው ፕሬዝዳንት ጆሴፍ ኤፍ. ስሚዝ (1838-1918 እ.አ.አ) አስተማሩ። “በቀናነት አናግሯቸው።”3

ሽማግሌ ብረንት ኤች. ኔልሰን የሰባ ጉባኤ አባል አስር ድሪም ላላቸው እና አንዱ ለጠፋባቸው፣ “እስከምታገኙት ድረስ ፈልጉት” ያለውን የአዳኝን ምሪት ደግመው ተናግረዋል። የጠፋው የወንድ ወይም የሴት ልጃችሁ፣ ወንድማችሁ ወይም እህታችሁ ስትሆን፣ … ለምድረግ ከምንችለው ነገሮች ሁሉ በኋላ፣ ያንን ሰው በሙሉ ልባችን እንወደዋለን። …

“እናንተ እና እኔ ሌሎችን በሕይወታችን ውስጥ የጠፉትን ሰዎች እንዴት እንደምንቀርብ ለማወቅ እናም፣ አስፈላጊ ሲሆንም፣ አባካኙን ለማፍቀር፣ ለመመልከት እና ለመጠበቅ የሰማይ አባታችን እና የልጁ የኢየሱስ ክርስቶስ ትዕግስት እና ፍቅር እንዲኖረን ራዕይ እንቀበል።”4

ፕሬዘደንት ሔንሪ ቢ. አይሪንግ፣ የቀዳሚ አመራር የመጀመሪያ አማካሪ፣ እንዳሉት፥ “የምወደው ሰው የቤዛነቱን ሃይል እንዲፈልጉና እንዲሰማቸው በእምነት ጸልያለሁ። የሰው መላእክትም ለእርዳታ ወደነርሱ እንዲመጡ ጸልያለሁ፣ እናም መጥተዋል።

“እግዚአብሄር እያንዳንዱ ልጆቹን ለማዳን መንገድ አዘጋጅቷል።”5

ተጨማሪ የቅዱሳት መጻህፍት ጥቅሶች እና መረጃ

ማቴዎስ 18፥12፤አልማ 31፥35፤ 3 ኔፊ 13፥32፤ ት. እና ቃ. 121፥41–42

reliefsociety.lds.org

ማስታወሻዎች

  1. ዲየትር ኤፍ. ኡክዶርፍ፣ “In Praise of Those Who Save,” Liahona, ግንቦት 2016 (እ.አ.አ)፣ 79፤ 80።

  2. ሊንዳ ኬ. በርተን፣ በሳራህ ጄን ዊቨር፣ “Sister Burton, Sister Wixom Visit Church’s Pacific Area፣” ውስጥ Church News ሚያዝያ 2፣ 2013 (እ.አ.አ)፣ lds.org/church/news{64}።

  3. Teachings of Presidents of the Church: Joseph F. Smith (1998), 254።

  4. ብረንት ኤች. ኔልሰን፣ “Waiting for the Prodigal፣” Liahona፣ ግንቦት 2015 (እ.አ.አ)፣103።

  5. ሔንሪ ቢ. አይሪንግ፣ “To My Grandchildren፣” Liahona፣ ህዳር. 2013 (እ.አ.አ)፣ 71።

አትም