2017 (እ.አ.አ)
የእርስ በራስን ሸከም ለመሸከም ፈቃደኛ መሆን
ታህሳስ 2017 (እ.አ.አ)


የሴቶች የቤት ለቤት ጉብኝት ማስተማሪያ መልእክት፣ ታህሳስ 2017 (እ.አ.አ)

የእርስ በራስን ሸከም ለመሸከም ፈቃደኛ መሆን

በጸሎት መንፈስ ይህንን መረጃ አንብቡት እና ምን እንደምታካፍሉ ለማወቅ የመንፈስ ምሪትን እሹ። የሴቶች መረዳጃ ማህበር እቅድን ማወቅ እንዴት የእግዚአብሔር ሴት ልጆችን ለዘለአለማዊ ህይወት በረከቶች ያዘጋጃል?

እምነት ቤተሰብ እርዳታ

ፕሬዘደንት ቶማስ ኤስ. ሞንሰን እንዳሉት፣ “የእኛን እርዳታ፣ የእኛን ማበረታታት፣ የእኛን ድገፋ፣ የእኛን ማፅናናት፣ የእኛን ደግነት በሚፈልጉት እንከበባለን” “በዚህ ምድር ላይ እኛ ልጆቹን የማገልገል እና የማንሳት ጭምር አደራ ያለን የጌታ እጆች ነን።” በእያንዳንዳችን ላይ ጥገኛ ነው።”1

የቀዳሚ አመራር የመጀመሪያ አማካሪ ፕሬዘደንት ሔንሪ ቢ. አይሪንግ እንዳሉት፣ “ወደ ቤተክርስቲያኗ ስንመጣ ታላቅ ለውጥ በልባችን ውስጥ ይጀምራል። ቃልኪዳን ገብታችኋል፣ እናም ዋና ተፈጥሮአችሁን መቀየር የጀመረውን ቃል ኪዳን ተቀብላችኋል። …

“… [ሸክማቸውን] ቀላል ለማድረግ እና እንዲፅናኑ አመቺ በማድረጉ ላይ ጌታን ለመርዳት ቃል ገብታችኋል። መንፈስ ቅዱስ ስጦታን ስትቀበሉ እነኛን ሸክሞች ለማቅለል የመርዳትን ሀይል ተሰጥቷችሁ ነበር።”2

የሴቶች መረዳጃ ማህበር አጠቃላይ ፕሬዘደንት ጂን ቢ. ቢንገም እንዳሉት፣ “ሌሎችን አዳኙ በሚያቸው እኛ እንድናያቸው—በፍቅር በርህራሔ በተስፋ እና በልግስና—የወንጌሉን ብርሀን መጠቀም እንፈልጋለን። “ስለሌሎችም ልብ ሙሉ የሆነ መረዳት የሚኖረን ቀን ይመጣል እንዲሁም ምህረት ሲሰጠን አመስጋኝ እንሆናለን—ልክ በዚህ ህይወት እኛ ለሌሎች በልግስና የተሞላ ሀሳብ እና ቃላቶች እንደምንሰጠው። …

“ልክ እንደ አዳኛችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለመሆን በምናደርገው የእኛ ግዴታ እና በረከት ጥረት የሁሉንም ሰዎች መሻሻልን መቀበል ነው።”3

የእርስ በራስን ሸከም ስንሸከም እና ቃል ኪዳኖቻችንን ስናከብር፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ሌሎችን የሚፈውስበትን መንገድ እንከፍታለን። የአስራሁለት ሐዋሪያት ሸንጎ አባል ሽማግሌ ጄፍሪ አር. ሆላንድ እንዳስተማሩት፥ “የመሰቀል እና የኃጢያት ክፍያን ለመረዳት የማይቻል ዋጋ ሲታሰብበት፣ እርሱ ወደ እኛ ጀርባውን እንደማያዞር ቃል እገባላችኋለሁ። በመንፈስ ደሀ ለሆኑት ‘ወደእኔ ኑ’ ሲል፣ እርሱ የሚወጣበት መንገድን ያውቃል እና እርሱ ከፍ የሚባልበትን መንገድ ያውቃል ማለት ነው። የሚያውቀውም እርሱ ስለተራመደበት ነውና። እርሱ መንገዱን ያውቀዋል፤ በእርግጥም እርሱ መንገዱ ነውና።”4

ተጨማሪ ቅዱሳት መጻህፍቶች

ማቴዎስ 25፥40ገላትያ 6፥2ሞዛያ 2፥1718፥8–9

ማስታወሻዎች

  1. ቶማስ ኤስ. ሞንሰን፣ “ጌታን በፍቅር አገልግሉ፣” Liahona፣ የካቲት 2014 (እ.አ.አ)፣ 4።

  2. ሔንሪ ቢ. አይሪንግ፣ “አፅናኙ፣” Liahona፣ ግንቦት 2015 (እ.አ.አ)፣ 18።

  3. ጂን ቢ. ቢንገም፣ “የወንጌልን ብርሀን ወደቤቴ አመጣለሁ” Liahona፣ ህዳር 2016 (እ.አ.አ)፣ 6፣ 8።

  4. ጀፍሪ አር. ሆላንድ፣ “Broken Things to Mend፣” Liahona ግንቦት 2006 (እ.አ.አ)፣ 71።

አትም