2017 (እ.አ.አ)
ክርስቶስን በገና በዓል ላይ መፈለግ
ታህሳስ 2017 (እ.አ.አ)


የቀዳሚ አመራር መልእክት፣ ታህሳስ 2017 (እ.አ.አ)

ክርስቶስን በገና በዓል ላይ መፈለግ

እኛ እንደ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባላት ማን እንደሆንን ለመረዳት ለሚፈልጉት ሁሉ፣ በእነዚህ ሶስት ቃላት በሚተረጎሙ የመጀመሪያ ነጥቦች ለማቅረብ እፈልጋለሁ፥ ክርስቶስን እንሻለን።

ስለእርሱ ለመማር እንፈልገዋለን። እርሱን ለመከተል። በተጨማሪ እንደ እርሱ ለመሆንም።

በአመት ሁሉ በየቀኑ፣ እንፈልገዋልን። ነገር ግን በአመቱ በዚህ ጊዜ—በገና፣ የውድ አዳኛችንን መወለድ በምናከብርበት ጊዜ—ልባችን ወደ እርሱ በይበልጥ ያዘነብላል።

ገናን ለማክበር በምንዘጋጅበት ክፍል፣ ከሁለት መቶ አመት በፊት የአዳኝን መምጣት በሰላምታ ለመቀበል ተዘጋጅተው የነበሩትን አስቡባቸው።

እረኞቹ

“በዚያም ምድር መንጋቸውን በሌሊት ሲጠብቁ በሜዳ ያደሩ”1 እንደነበሩ በስተቀር፣ ስለእረኞች ብዙ አናውቅም። የለት ተለት የሚኖሩበትን ለማግኘት በየቀኑ እንደሚሰሩ እንደሚሞገሱ ሰዎች ሁሉ፣ እረኞቹ ተራ ሰዎች ነበሩ።

በጊዜው ክርስቶስን የማይፈልጉ ፣ ግን ሰማይ ሲከፈት እና ክርስቶስ ለእነርሱ ሲታዋጅ ልባቸው የተቀየረላቸውን ሰዎች ሊወክሉ ይችላሉ።

የሰማይ መልእክተኞችን ካዳመጡ በኋላ፣ ወዲያው ለማየት በመፈለግ ወደ ቤተልሔም የሄዱትም እነርሱ ናቸው።2

ጠቢብ ሰዎቹ

ጠቢብ ሰዎቹ የመሲህን፣ የእግዚአብሔር ልጅን፣ መምጣት ያጠኑ የተማሩ ሰዎች ነበሩ። ባጠኑባቸውም ስለውልደቱ የሚያጠቁሙትን ምልክቶች አወቁ። ሲያውቋቸውም፣ እንዲህም በመጠየቅ “የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው?”3 ቤቶቻቸውን ትተው ወደ ኢየሩሳሌም ተጓዙ።

ስለክርስቶስ ያላቸው እውቀት በትምህርት ላይ ብቻ በመመካት አልቀረም። የመወለዱን ምልክት ከተመለከቱ በኋላ፣ ድርጊትን አከናወኑ። ክርስቶስን ለማግኘት ሄዱ።

ጠቢብ ሰዎችም ክርስቶስን በመማር እና በጥናት የሚፈልጉትን ሊወክሉ ይችላሉ። ለእውነት ያላቸው ፍቅር ክርስቶስን ወደማግኘት እና እርሱን እንደ ንጉሰ ነገስት፣ እንደ ሰው ዘር አዳኝ ወደማምለክ መራቸው።4

ስምዖን እና አና

ስምዖን እና አና ክርስቶስን በመንፈስ የሚፈልጉትን ሰዎች ለመወከል ይችላሉ። እነዚህ አስደናቂ ነፍሶች ታማኝ አምላኪዎች ነበሩ እናም፣ በጾምና ጸሎት በኩል እናም የታማኝነት እና ታዛዥነት ህይወት በመኖር፣ የእግዚአብሔር ልጅ መምጣት ቀንን ለማየት በጉግት ይጠብቁ ነበር።

በታማኝነት፣ በትህትና፣ እና በእምነት፣ የአዳኝን መጣት በትዕግስት ጠበቁ።

በመጨረሻም፣ ማርያም እና ዮሴፍ አንድ ቀን በራሱ ላይ የሰውን ዘር ኃጢያቶች የሚወስደውን ህጻን ለእነርሱ በማቅረብ ታማኝነታቸው ተክሷል።5

በኔፋውያን እና ላማናውያን መካከል የነበሩ አማኞች

የአዲሱ አለም አማኞች የአዳኝ መወለድን ምልክቶች ሲመለከቱ የነበሩበትን የሚነኩ ታሪኮች በመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ ይገኛሉ።

በክርስቶስ እምነት ያላቸው እንደተሳለቋብቸው እና እንደተሰደዱ ታስታውሳላችሁ። የዚያን ቀን የተራቀቁ ሰዎች የሚያምኑትን የሞኝነት ድርጊቶችን እንደሚጠብቁ ከሰሷቸው። በእርግጥም፣ የማያምኑት በሚያሳልቁበት ጉዳይ ድምጻቸው ከፍ ብሎ፣ በምድሩ ላይ “ታላቅ ረብሻ አደረጉ” (3 Nephi 1፥7)። አዳኝ እንደሚወለድ በሚያምኑትም ላይ አሾፉባቸው።

ንዴታቸው እና ቁጣታቸው ታላቅ ሆኖ በአዳኝ የሚያምኑትን ለመጨረሻ ጊዜ ጸጥ ለማድረግ ፍላጎታቸው ታላቅ ሆነ። መፅሐፈ ሞርሞን አስደናቂውን የታሪክ ፍጻሜ መዝግቧል።6

በዚህ ዘመን ይኖሩ የነበሩት ታማኞች ሌሎች በሚስቁባቸው፣ በሚያሳልቁባቸው፣ እና በሚያስፈራሯቸው ጊዜም ቢሆን ክርስቶስን የሚፈልጉትን ይወክላሉ። ሌሎች እነርሱን እንዳልተነጠሩ፣ እንዳልተራቀቁ፣ ወይም ሞኞች ሊያስመስሏቸው በሚጥሩበት ጊዜም እንኳን ክርስቶስን ይፈልጋሉ።

ነገር ግን የሌሎች ንቀት እውነተኛ ታማኞች ክርስቶስን ከመፈለግ አላደናቀፋቸውም።

ክርስቶስን እንሻለን

በአመቱ በሙሉ፣ እና ምናልባትም በዚህ በገና ዘመን፣ “ክርስቶስን እንዴት እፈልጋለሁ?” የሚለውን ጥያቄ እንደገና በዓል ላይ መጠየቃችን ጥቅም ይሰጠናል።

በህይወቱ አስቸጋሪ ጊዜ፣ ንጉስ ዳዊት እንዲህ ጻፈ፣ “አምላኬ፥ አምላኬ፥ ወደ አንተ እገሠግሣለሁ፤ ነፍሴ አንተን ተጠማች፥ ሥጋዬ አንተን እንዴት ናፈቀች።”7

በዚህ እግዚአብሔርን በመፈለግ ጸባዩ ምክንያት ይሆናል ዳዊት እንደ እግዚአብሔር ልብ የሆነ ሰው ተብሎ የሚታወቅበት።8

በዚህ የገና ዘመን እና በአምቱ በሙሉ፣ በልባችን እና በነፍሳችን ውስጥ አዳኛችንን፣ የሰላም ልዑልን፣ የእስራኤል ቅዱሱን እንፈልግ። ይህም ፍላጎት፣ በታላቅ ሁኔታ፣ እንደ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባላት ማን እንደሆንን ብቻ ሳይሆን እንደ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርቶች ማን እንደሆንን የሚያሳይ ነው።

አትም