2018 (እ.አ.አ)
እስራኤልን በመሰብሰብ የእህቶች ተሳታፊነት
ህዳር 2018 (እ.አ.አ)


ministering

የቀዳሚ አመራር መልእክት፣ ህዳር 2018 (እ.አ.አ)

እስራኤልን በመሰብሰብ የእህቶች ተሳታፊነት

የተበተኑትን እስራኤላዊያን እንዲሰበሰቡ በመርዳት ወደፊቱ እንድታቀኑ ነቢያዊ ልመናዬን ለእናንት ለቤተክርስቲያኗ ሴቶች አቀርባለሁ።

ውድ እና ተወዳጅ እህቶቼ ከናንተ ጋር በመሆኔ ደስ ይላል። ምናልባት በቅርብ ያጋጠመኝ ተሞክሮ ለእናንተ ያለኝን ስሜት እና እናንት ስለተባረካችሁበት መለኮታዊ ችሎታችሁ ቅንጭብ እይታ ልስጣችሁ

አንድ ቀን በደቡብ አሜሪካ ውስጥ ለተሰብሳቢዎች ንግግር ሳቀርብ፣ ስለርዕሱ ጓጉቼ ነበር ፣ እናም በአስፈላጊ ጊዜም፣ እንዲህ አልኩኝ፣ “እንደ 10 ልጆች እናት፣ እንዲህ ልነግራችሁ እችላለሁ …።” እና ከዚያም መልእክቴን ለመፈጸም ቀጠልኩኝ።

እናት የሚለውንውን ቃል እንዳልኩኝ አልተረዳሁም ነበር። ተርጓሚዬ፣ በስህተት የተናገርኩኝ መስሎት፣ የእናት ቃልን ወደ አባት ቀይሮ ነበር፣ ስለዚህ ተሰብሳቢዎች ራሴን እንደ እናት እንደጠቆምኩኝ አላወቁም ነበር። ነገር ግን ባለቤቴ ዌንዲ ይህን ሰምታ ነበር፣ እናም በስህተቴ ተደስታ ነበር።

በዚያ ጊዜ፣ ልክ እንደ እናት፣ በአለም ለውጥ ለማምጣት በልቤ ያለው የጉጉት ፍላጎት ከልቤ ተፈንቅሎ ወጣ። በአመታት ውስጥ፣ ዶክተር ለምን ለመሆን እንደመረጥኩኝ ስጠየቅ፣ መልሴ ሁሌም አንድ ነበር፥ “ምክንያቱም እናት ለመሆን ለመምረጥ ስላልቻልኩኝ።”

እባካችሁ በማንኛው ጊዜ እናት የሚለውን ቃል ስጠቀም፣ የምናገረው ልጆች ለወለዱት ወይም በጉዲፈቻ ስለሚያሳድጉት ብቻ አይደለም። ስለሰማይ ወላጆቻችን ጎልማሳ ሴት ልጆች በሙሉ ነው የምናገረው። እያንዳንዷ ሴት በዘለአለማዊ መለኮታዊ ተፈጥሮዋ እናት ናት።

ስለዚህ በዚህ ምሽት፣ እንደ 10 ልጆች አባትዘጠኝ ሴቶች እና አንድ ወንድ ልጆች—እና እንደ ቤተክርስቲያኗ ፕሬዘደንት፣ ስለእናንተ፣ ማን ስለመሆናችሁና ለምታደርጉት መልካም ነገሮች ሁሉ፣ ምን ያህል ጥልቅ ስሜት እንዳለኝ እንዲሰማችሁ እጸልያለሁ። ጻድቅ ሴት ለማድረግ የምትችለውን ማንም ለማድረግ አይችልም። ማንም የእናትን ተፅዕኖ አመሳስሎ ሊገለብጥ አይችልም።

ወንዶች የሰማይ አባትን እና አዳኝን ፍቅር ለማስተላለፍ ይችላሉ እናም በብዛት ያደርጉታል። ነገር ግን ሴቶች ለዚህ ልዩ ስጦታ—መለኮታዊ በረከት አላቸው። ሰው ምን እንደሚያስፈልገው—እናም መቼ እንደሚያስፈልጋቸው ለመሰማት ልዩ ችሎታ አላችሁ። እርዳታ በሚያስፈልጋቸው በዚያው ጊዜ ሰውን ለመድረስ፣ ለማፅናናት፣ ለማስተማር፣ እና ለማጠናከር ትችላላችሁ።

ሴቶች ወንዶች ነገሮችን ለመመልከት ከሚችሉት በተለየ ሁኔታ ያያሉ፣ እናም አስተያየታችሁ እንዴት ነው የሚያስፈልገን። ፍጥረታችሁ ስለሌሎች ፍላጎቶች በመጀመሪያ እንድታስቡ፣ ምንም የሚደረገው በሌሎች ላይ ምን ውጤት እንደሚኖረው እንድታስቡ ይመራችኋል።

ፕሬዘደንት አይሪንግ እንደጠቆሙት፣ ግርማዊዋ እናት ሔዋን ነበረች—ስለሰማይ አባታችን እቅድ ወደፊት በመመልከት— “ውድቀት” የምንለውን የጀመረችው። የእርሷ ጥበባውዊ እና ብርቱ ምርጫ እና የአዳም ደጋፊ ውሳኔ የእግዚአብሔርን የደስታ እቅድ ወደፊት ገፉ። እነርሱም ለእያንዳንዳችን ወደ ምድር ለመምጣት፣ ሰውነትን ለመቀበል፣ እናም አሁን፣ ልክ በቅድመ ምድር እንዳደረግነው፣ ለኢየሱስ ለመቆም እንድንመርጥ አስቻሉልን።

ውድ እህቶቼ፣ እናንተ ልዩ መንፈሳዊ ስጦታ እና የተፈጥሮ ዝንባሌ አላችሁ። በዚህ ምሽት፣ በልቤ ሙሉ ተስፋ፣ የመንፈሳዊ ስጦታችሁን ለመረዳት እንድትጸልዩ—ከዚሀ በፊት አድርጋችሁ ከምታውቁት በላይ እንድትኮተኩቱ፣ እንድትጠቀሙበት፣ እና እንድታስፋፉ አበረታታችኋለሁ። ይህን ስታደርጉ አለምን ትቀይራላችሁ።

እንደ ሴቶች፣ ሌሎችን ታነሳሳላችሁ እናም ለመከተል ብቁ የሆነ መሰረትም ትመሰርታላችሁ። ባለፈው አጠቃላይ ጉባኤ ስላስተዋወቅናቸው ሁለት ነገሮች መነሻ መሰረትን ልንገራችሁ። እናንተ፣ ውድ እህቶች፣ ለእያንዳንዱ ቁልፎች ነበራችሁ።

መጀመሪያ፣ አገልግሎት። ያም ታላቅ የአገልግሎት መሰረት የአዳኛችን፣ የኢየሱስ ክርስቶስ ነው። በአጠቃላይም፣ ሴቶች ከወንዶች በላይ በእነዚህ መሰረቶች አሁንም፣ እና ሁልጊዜም፣ የቀረቡ ነበሩ። በእውነት ስታገለግሉ፣ አንድን ሰው የአዳኝን ፍቅር እንዲለማመዱ ያላችሁን ስሜት ትከተላላችሁ። ለማገልገል ያለው ዝንባሌ በጻድቅ ሴቶች ውስጥ በፍጥረት የሚገኝ ነው። በየቀኑ፣ “ማንን እንድረዳ ትፈልጋለህ?” በማለት የሚጸልዩ ሴቶችን አውቃለሁ።

ከሚያዝያ 2018 (እ.አ.አ) ስለከፍተኛ እና ቅዱስ ሌሎችን ስለመንከባከብ መንገድ ከነበረው ማስታወቂያ በፊት፣ የአንዳንድ ወንዶች ልምምድ የቤት ለቤት ትምህርት ምድባቸውን “ተፈጽሟል” በማለት እና ወደሚቀጥለው ስራ መሄድ ነበር።

ነገር ግን እናንተ የምትጎበኟት ሴት እርዳታ እንደሚያስፈልጋት ሲሰማችሁ፣ ወዲያው እና ከዚያም ወሩን በሙሉ እርዳታ ትሰጣላችሁ። በዚህም፣ የእናንት ጉብኝት እንዴት አስተምዕሮ ከፍ ወዳለው አገልግሎት እንድንቀይር ያነሳሳን።

ሁለተኛ፣ ባለፈው አጠቃላይ ጉባኤ ውስጥ፣ የመልከ ጼዴቅ ክህነት ቡድኖችን እንደገና አደራጀን። የቤተክርስቲያኗ ወንዶች በሀላፊነቶቻቸው እንዴት ውጤታማ እንዲሆኑ ለመርዳት እንደምንችል ለማወቅ ስንታገል፣ የሴቶች መረዳጃ ማህበርን ምሳሌ በጥንቃቄ አሰብንበት።

በሴቶች መረዳጃ ማህበር ውስጥ፣ በተለያዩ እድሜ እና የህይወት ጉዳይ ላይ ያሉ ሴቶች አብረው ይሰበሰባሉ። በእያንዳንዱ የህይወት አስርተ አመቶች ልዩ ፈተናዎችን ያመጣሉ፣ እና ግን በሳምንት ወደሳምንት፣ አብራችሁ በመቀላቀል፣ አብራችሁ በማደግ እና ወንጌልን በማስተማር፣ እናም በአለም ላይ እውነተኛ ለውጥ በማምጣት ትገኛላችሁ።

አሁን፣ የእናንተን ምሳሌ በመከተል፣ የመልከ ጼዴቅ ክህነት ተሸካሚዎች የሽማግሌዎች ሸንጎ አባላት ናቸው። እነዚህ ወንዶች፣ ከእድሜያቸው እኩል የሆነ የክህነት እና የቤተክርስቲያን አጋጣሚዎች ኖሯቸው፣ በእድሜ ከ18 እስከ 98 (ምናልባት በላይ) ናቸው። እነዚህ ወንድሞች ጠንካራ የወንድምነት ግንኙነትን አብረው በመማር፣ እና ሌሎችን በፍጹም ውጤታማነት በመባረክ ለመፍጠር ይችላሉ።

ባለፈው ሰኔ፣ እህት ኔልሰን እና እኔ የቤተክርስቲያኗ ወጣቶችን እንዳነጋገርን ታስታውሳላችሁ። እስራኤልን በሁለቱም መጋረጃዎች በኩል በመሰብሰብ ለመርዳት በጌታ ወጣቶች ሰራዊት ውስጥ እንዲመለመሉ ጋበዝናቸው። ይህም ስብሰባ “በአለም ውስጥ ዛሬ ከሚገኙት ታላቁ ፈተና፣ ታላቁ ምክንያት፣ እናም ታላቁ ስራ ነው”!1

ይህም መርህ ሴቶችን በጣም የሚያስፈልገው ነው፣ ምክንያቱም ሴቶች ወደፊትን ይቀርጻሉና። የተበተኑትን እስራኤላዊያን እንዲሰበሰቡ በመርዳት ወደፊቱ እንድታቀኑ በዚህ ምሽት ነብያዊ ልመናዬን ለእናንት ለቤተክርስቲያኗ ሴቶች አቀርባለሁ።

የት መጀመር ትችላላችሁ?

አራት ግብዣዎችን አቀርብላችኋለሁ፥

መጀመሪያ፣ ለአእምሮ መጥፎ እና ንጹህ ያልሆኑ አስተሳሰቦችን ከሚያመጡ ከማኅበራዊ ሚዲያ እና ከማንኛውም መገናኛ ብዙሃን መንገዶች ለ10 ቀን ጾም እድትሳተፉ እጋብዛችኋለሁ። በዚህ ጾም የትኛውን ተፅዕኖ እንደምታስወግዱ ለማወቅ ጸልዩ። የእናንተ የ10 ቀን ጾም ውጤት ሊያስገርማችሁ ይችላል። መንፈሳችሁን የሚጎዳውን የዓለም አመለካከት ከጣላችሁ በኋላ ምን ታስተውላላችሁ? ጊዜያችሁንና ጉልበታችሁን ለማሳለፍ የምትፈልጉበት ቦታ አሁን ለውጥ ይኖራችኋል? ቅድሚያ የምትሰጧቸው ነገሮች ትንሽም እንኳ ቢሆን ተለውጠዋልን? እያንዳንዱን መነሳሻችሁን እንድትመዘግቡ እና እንድትከተሉ እገፋፋችኋለሁ።

ሁለተኛ፣ መፅሀፈ ሞርሞንን በአሁን እና በአመት መጨረሻ መካከል እንድታነብቡ እጋብዛችኋለሁ። በህይወታችሁ ለመቆጣጠር በምታደርጉት ነገሮች ላይ ሁሉ ተጨማሪ ይህም የሚቻል ባይመስላችሁም፣ ይህን ግብዣ በልብ ሙሉ እቅድ ከተቀበላችሁ፣ ጌታ ይህን ለማከናወን ይረዳችኋል። እናም፣ በጸሎት ስታጠኑ፣ ሰማያት ለእናንተ ይከፈታሉ። ጌታ በተጨማሪ መነሳሻ እና ራዕይ ይባርካችኋል።

ስታነቡም፣ ስለ አዳኝ የሚናገረውን ወይም የሚያመለክተውን እያንዳንዱ ጥቅስ በቀለም እንድታስመለክቱ አበረታታችኋለሁ። ከዚያም፣ ስለክርስቶስ በመናገር፣ በክርስቶስ በመደሰት፣ እና ስለ ክርስቶስ ለቤተሰቦቻችሁና ለወዳጆቻችሁ ለመስበክ በሀሳብ ተዘጋጁ።2 እናንተ እና እነርሱም ወደ አዳኝ በዚህ ድርጊት ትቀርባላችሁ። እናም ለውጦች፣ እንዲሁም ታዕምራቶች፣ መከሰት ይጀምራሉ።

በዚህ ጠዋት ስለአዲሱ የቤተክርስቲያን ሰዓቶች እና በቤት ላይ ያተኮረ፣ በቤተክርስቲያን ሰለተደገፈ ስርዓተ-ትምህርት ማስተዋወቂያ ነበር። እናንተ፣ ውድ እህቶቼ፣ ለዚህ አዲስ፣ የተመጣጠነ የወንጌል ማስተማሪያ ጥረት ውጤታማነት እናንተ ዋና ቁልፍ ናችሁ። እባካችሁ ከቅዱሳት መጻህፍት የምትማሩትን ለምትወዷቸው አስተምሩ። ለእነሱ መፈወስ እና ኃጢያት ሲሰሩ የሚያነፃ ሀይል ወዳለው አዳኝ እንዲዞሩ አስተምሯቸው። እናም የእርሱን የሚያጠናክር ሀይል በየቀኑ ወደ ህይወታቸው እንዴት እንደሚስቡ አስተምሯቸው።

ሶስተኛ፣ ሁልጊዜም ወደ ቤተመቅደስ የመሄድ ንድፍን መስርቱ። ይህም በህይወታችሁ ተጨማሪ መስዋዕትን ይጠይቅ ይሆናል። በቤተመቅደስ ውስጥ በተደጋጋሚ መሄድ በቤተመቅደስ ውስጥ የተባረካችሁበትን የክህነት ሀይሉን እንዴት ለመጠቀም እንደምትችሉ ጌታ ያስተምራችኋል። በቤተመቅደስ ቅርብ ለሆናችሁ፣ ስለቤተመቅደስ በቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ እና በህያው ነቢያት ቃላት ውስጥ በጸሎት እንድታጠኑ እጋብዛችኋለሁ። ከዚህ በፊት ከነበራችሁ በላይ ለማወቅ፣ በተጨማሪ ለመረዳት፣ ስለቤተክርስቲያን ተጨማሪ ስሜት እንዲኖራችሁ ፈልጉ።

ባለፈው ሰኔ በነበረን አለም አቀፋዊ የወጣቶች ስብሰባ፣ ወላጆቹ ስማርት ስልኩን ወደሚታጠፍ ስልክ ሲለውጡለት ህይወቱ እንዴት እንደተለወጠ ተናግሬ ነበር። የዚህም ወጣት እናት ፍርሀት የሌላት የእምነት ሴት ነበረች። ከሚሲሆናዊ አገልግሎተ ወደ ሚያሰናክሉት ምርጫዎች ሲሄድ ተመልከተች። ልጇን እንዴት ልትረዳው እንደምትችል ልመናዋን ወደ ቤተመቅደስ ወሰደች። ከዚያም የነበራትን ስሜት በሙሉ ተከተለች።

እንዲህም አለች፥ “በልዩ ሰዓት ወሳኝ ነገሮችን በልጄ ስልክ ላይ እንድከታተል የመንፈስ መመሪያ ተሰማኝ።” እነዚህን ስማርት ስልኮች እንዴት እንደሚሰሩ አላውቅም ነበር፣ ግን መንፈስ በማልጠቀምበት በማህበራዊ ሚድያ ውስጥ በሙሉ በመመልከት መመሪያ ሰጠኝ። መንፈስ ልጆቻቸውን ለመጠበቅ መመሪያ የሚጠይቁን ወላጆችን እንደሚረዳ አውቃለሁ። [በመጀመሪያ] ወንድ ልጄ በእኔ ተናድዶ ነበር። … ነገር ግን ከሶስት ቀናት በኋላ፣ አመሰገነኝ! ለውጡ ይሰማው ነበር።”

የልጇ ፀባይ እና አስተያየት በጣም ተቀየረ። በቤት ውስት ተጨማሪ እርዳታ መስጠት ጀመረ፣ ተጨማሪ ፈገግታ አሳየ፣ እናም በቤተክርስቲያንም ተጨማሪ ትኩረት ይሰጥ ነበር። ለጊዜውም በቤተመቅደስ ጥምቀት ውስጥ ማገልገልን እና ለወንጌል ስብከት አገልግሎቱ መዘጋጀትን ይወድ ነበር።

በአራተኛው የምጋብዛችሁ፣ በእድሜ ለምትገኙት፣በሴቶች መረዳጃ ማህበር በሙሉነት እንድትሳተፉ ነው። የአሁን የሴቶች መረዳጃ ማህበር አላማ መረጃን እንድታጠኑ አበረታታችኋለሁ። ይህም የሚያነሳሳ ነው። ይህም የራሳችሁን የአላማ መረጃ እንድትሰሩ መመሪያችሁ ሊሆን ይችላል። ከ20 አመት በፊት በሴቶች መረዳጃ ማህበር አዋጅ ውስጥ ያለውን እውነት እንድትደሰቱበት እለምናችኋለሁ።3 የዚህ አዋጅ ግልባጭ በቀዳሚ አመራር ቢሮ ግድግዳ ላይ በፈሬም ተደርጎ ተሰቅሏል። ይህን ሳነብ ሁልጊዜም እደሰታለሁ። ጌታ በዚህ ጊዜ የተበተኑ እስራኤልን ለመሰብሰብ ድርሻችሁን ስትወጡ ጌታ እናንተ ማን እንደሆናችሁ እና እንድትሆኑ የሚፈልገውን ይገልጻል።

ውድ እህቶቼ፣ እንፈልጋችኋለን! እኛም “የእናንተ ጥንካሬ፣ የእናንተ ለውጥ፣ የእናንተ አቋም፣ የእናንተ የመምራት አቅም፣ የእናንተ ጥበብ፣ እና የእናንተ ድምጽ ያስፈልገናል።”4 እስራኤልን ካለእናንተ ለመሰብሰብ አንችልም።

አፈቅራችኋለሁ እናም አመሰግናችኋለሁ እና በዚህ አስፈላጊ እና አስቸኳይ ስራ ስትረዱ አለምን ከኋላችሁ የመተው አቅም እንዲኖራችሁ እባርካችኋለሁ። አብረንም የሰማይ አባት አለምን ለውድ ልጁ ዳግም ምፅዓት ለማዘጋጀት እንድናደርግ የሚፈልገንን ሁሉ ለማድረግ እንችላለን።

ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ይህች የእርሱ ቤተክርስቲያን ናት። ይህንን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም እመሰክራለሁ፣ አሜን።