2021 (እ.አ.አ)
በሕይወቴ ውስጥ የጌታን ድምፅ እየሰማሁ እንደሆነ እንዴት ማወቅ እችላለሁ?
የካቲት 2021 (እ.አ.አ)


“በሕይወቴ ውስጥ የጌታን ድምፅ እየሰማሁ እንደሆነ እንዴት ማወቅ እችላለሁ?” ለወጣቶች ጥንካሬ፣ የካቲት 2021 (እ.አ.አ)፣ 29።

ወርሀዊ ለወጣቶች ጥንካሬ መልዕክት፣ የካቲት 2021 (እ.አ.አ)

በሕይወቴ ውስጥ የጌታን ድምፅ እየሰማሁ እንደሆነ እንዴት ማወቅ እችላለሁ?

ወጣት ልጅ ቅዱሳት መጻህፍትን ሲያነብ

ፕሬዘዳንት ራስል ኤም. ኔልሰን ኢየሱስ ክርስቶስን እንዴት እንደምንሰማው እና “በተሻለና በተደጋጋሚ እሱን ለመስማት እርምጃዎችን እንወስድ” ዘንድ “በጥልቀትና አብዝተን እንድናስብ” ጋብዘውናል። (“‘How Do You #HearHim?’ A Special Invitation,” Feb. 26, 2020, blog.ChurchofJesusChrist.org).

በቅዱሳት መጻሕፍት እና በነቢያት ቃላት አማካኘነት እርሱን መስማት እንችላለን። ቁልፉ ግን እነዚያን ቃላት መስማት ወይም ማንበብ ብቻ አይደለም። በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በኩል ጌታ እንዲህ አብራርቶታል፦

“ለእናንተ እነዚህን [ቃላቶች] የሚናገራችሁ ድምፄ ነው፤ ለእናንተም የተሰጧችሁ በመንፈሴ ነው …፤

“ስለዚህ፣ ድምፄን እንደሰማችሁ … መመስከር ትችላላችሁ” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 18፥35–36)።

በተጨማሪም፣ እርሱን ለመስማት መፈለግ በችኮላ የምናደርገው ነገር አይደለም። ፕሬዘዳንት ኔልሰን እንዳሉት፣ “ንቁ እና ወጥ የሆነ ጥረት ይጠይቃል” (“እርሱን ስሙት፣” የሚያዝያ 2020 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ [ኢንዛይን ወይም ሊያሆና፣ ግንቦት 2020 (እ.አ.አ)፣ 89])።

ስታጠኑ፣ ስትጸልዩ፣ ስታመልኩ፣ ስታገለግሉ እና የጌታን ትእዛዛት ስታከብሩ፣ በመንፈሱ ይባርካችኋል እናም በኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ በኩልም ይለውጣችኋል። ያኔ ድምፁን እንደሰማችሁ ማወቅ ትችላላችሁ።