2021 (እ.አ.አ)
እግዚአብሔር እንድንጠመቅ ነግሮናል
የካቲት 2021 (እ.አ.አ)


“እግዚአብሔር እንድንጠመቅ ነግሮናል፣” ሊያሆና፣ የካቲት 2021 (እ.አ.አ)

ወርሀዊ የሊያሆና መልዕክት፣ የካቲት 2021 (እ.አ.አ)

እግዚአብሔር እንድንጠመቅ ነግሮናል

ኢየሱስ ክርስቶስ ከእግዚአብሔር ስልጣን ባለው ሰው መጠመቅ እንዳለብን ምሳሌ ሰጥቶናል።

ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ የግል ህይወት ብዙ ዝርዝሮች ባይኖሩንም፣ እርሱ 30 ዓመት ገደማ በሆነው ጊዜ እንደተጠመቀ እናውቃለን (ሉቃስ 3፥23ን ይመልከቱ)። ስለጥምቀት እርሱ ከተወልን ምሳሌ የምንማራቸው አንዳንድ ነግሮች እዚህ ቀርበዋል።

ለእያንዳንዱ ሰው

በበጎ እና በስህተት መካከል ያለውን ልዩነት ለመለየት በቂ ዕድሜ ላይ ከደረስን፤ የሰማይ አባት እንድንጠመቅ ይፈልጋል (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 18፥42ን ይመልከቱ)። ኢየሱስ ፍጹም ነበር፣ ሆኖም የእግዚአብሔርን ትእዛዛት ለመከተል መጠመቅን መረጠ (ማቴዎስ 3፥13–172 ኔፊ 31፥7ን ይመልከቱ)። የሞቱት እንኳን ጥምቀትን መቀበል ይችላሉ። በቤተመቅደሶች ውስጥ ለእነርሱ በመጠመቅ ይህን እናቀርብላቸዋለን። (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች፣ 128፥15-18ን ይመልከቱ።)

ምስል
ጥምቀት

በባለስልጣን ይከናወናል

ኢየሱስ በማንም ተራ ሰው አልተጠመቀም። ከእግዚአብሔር ዘንድ የክህነት ስልጣን ወደነበረው የአጎቱ ልጅ ወደ ዮሐንስ ሄደ። ኢየሱስ ከሞተና ደቀ መዛሙርቱ ከተገደሉ በኋላ፣ ያ የክህነት ስልጣን ከምድር ላይ ጠፍቶ ነበር። ከዚያም፣ በ1829 (እ.አ.አ) መጥምቁ ዮሐንስ ለጆሴፍ ስሚዝ ተገልጦ በእግዚአብሔር ስም እንዲያጠምቅ ስልጣን ሰጠው። በዚያ ዳግም መመለስ ምክንያት፣ እኛም ዛሬ በተመሳሳይ ስልጣን መጠመቅ እንችላልን።

ምስል
የአሮናዊ ክህነት ዳግም መመለስ

የሁለትዮሽ ተስፋ

ጥምቀት በእኛ እና በእግዚአብሔር መካከል የሁለትዮሽ ተስፋ፣ ወይም ቃል ኪዳንን፣ ያካትታል። የሚከተሉትን ለማድረግ ቃል እንገባለን፦

  1. በላያችን ላይ የክርስቶስን ስም ለመውሰድ።

  2. ሁሌም እርሱን ለማስታወስ።

  3. ትእዛዛቱን ለመጠበቅ።

በምላሹም፣ እግዚአብሔር መንፈሱ ሁልጊዜ ከእኛ ጋር እንደሚሆን ቃል ገብቷል። የቅዱስ ቁርባን ጸሎት ቃላቶች ስለዚህ ቃል ኪዳን በየሳምንቱ ያስታውሱናል። (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 20፥77፣79ን ይመልከቱ።)

ምስል
ቤተሰብ በቅዱስ ቁርባን ስብሰባ ውስጥ

መንፈስ ቅዱስን መቀበል የጥምቀት አስፈላጊው ክፍል ነው

ኢየሱስ ከተጠመቀ በኋላ መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል ወረደ (2 ኔፊ 31፥8ን ይመልከቱ)። ዛሬ ሰዎች ከተጠመቁ በኋላ ይረጋገጣሉ። ይህም ማለት በመንፈስ ቅዱስ ስጦታ በኩል መንፈጻዊ መፅዳትን ለመቀበል የሚጋበዙበትን ልዩ በረከት ይቀበላሉ ማለት ነው (2 ኔፊ 31፣17ን ይመልከቱ)። መንፈስ ቅዱስ ስለ አደጋ ሊያስጠነቅቀን፣ ሊያፅናናን፣ ጥሩ ውሳኔዎችን ለማድረግ እንድንችል ሊመራን እና የእግዚአብሔር ፍቅር እንዲሰማን ሊረዳን ይችላል (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 39፥ 6ን ይመልከቱ)።

ምስል
አንዲት ሴት ስትረጋገጥ

ሁል ጊዜም ንሰሀ መግባት እንችላለን

እግዚአብሔር ስህተትን እንደምንሰራ ያውቅ ነበር። ምንም እንኳን የተቻለንን ጥረት ሁሉ ብናደርግም፣ ኃጢያት እንሠራለን እናም የጥምቀታችንን ቃል ኪዳን ለመፈፀም ሳንችል እንቀራለን። ስለዚህ እርሱም ለእያንዳንዳችን ንስሐ የመግባት ዕድል ይሰጠናል። (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 18፥13ን ይመልከቱ።) ይቅርታ ለመጠየቅ እና ማንኛውንም ስህተቶች ለማረም በየቀኑ የተቻለንን ሁሉ ማድረግ እንችላለን። መጸለይ እና እግዚአብሔርን ይቅርታ መጠየቅ እንችላለን። ከዚያም፣ ቅዱስ ቁርባንን በትሁት ልብ በምንወስድበት ጊዜ፣ መንፈስ ቅዱስ ከእኛ ጋር ሊሆን ይችላል (3 ኔፊ 18፥11ን ይመልከቱ)።

ምስል
አንዲት ሴት በአልጋ አጠገብ ስትጸልይ

ቅዱሳት መጻህፍት ስለጥምቀት ምን ይላሉ?

ወላጆች ልጆቻቸው ለጥምቀት እንዲዘጋጁ መርዳት አለባቸው (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 68፥25ን ይመልከቱ)።

ከስምንት ዓመት በታች የሆኑ መጠመቅ አያስፈልጋቸውም (ሞሮኒ 8ን ይመልከቱ)።

ስንጠመቅ “ከሚያዝኑት ጋር ለማዘን፤ መፅናናትን ለሚፈልጉም [ለማፅናናት፣] እናም በሁሉም ጊዜ በሁሉም ነገርና፣ በምትኖሩበት ቦታዎች ሁሉ … የእግዚአብሔር ምስክር በመሆን [ለመቆም]” ቃል ገብተናል (ሞዛያ 18፥9)።

አትም