2021 (እ.አ.አ)
የኢየሱስ ክርስቶስን ቤተክርስቲያን ማቋቋም
መጋቢት 2021 (እ.አ.አ)


“የኢየሱስ ክርስቶስን ቤተክርስቲያን ማቋቋም፣” ጓደኛ፣ መጋቢት 2021 (እ.አ.አ)

ወርኃዊ የ ጓደኛ መልእክት፣ መጋቢት 2021 (እ.አ.አ)

የኢየሱስ ክርስቶስን ቤተክርስቲያን ማቋቋም

ምስል
ጆሴፍ ስሚዝ እና ኦሊቨር ካውድሪ ቤተክርስቲያንን ሲያደራጁ

ሥዕል በአፕርይል ስቶት

ሚያዚያ 6 ቀን 1830 (እ.አ.አ) በአንድ የእንጨት ቤት ውስጥ ልዩ ስብሰባ ተደርጎ ነበር። ጆሴፍ ስሚዝ የኢየሱስ ክርስቶስን ቤተክርስቲያን ዳግመኛ በምድር ላይ አቋቋማት።

ምስል
በቤተክርስቲያኗ መቋቋም ወቅት የነበረው የቅዱስ ቁርባን ሰርአት

ጆሴፍ ስሚዝ እና ኦሊቨር ካውድሪ ቅዱስ ቁርባኑን ባርከው አስተላለፉ።

ምስል
ሰዎች በወንዝ ውስጥ ሲጠመቁ

ስብሰባው ካበቃ በኋላ፣ በርካታ ሰዎች ተጠመቁ።

ምስል
ኤማ ስሚዝ ሰዎችን በመዝሙር እየመራች

ከጥቂት ወራት በኋላ፣ ለቤተክርስቲያኗ የመዝሙር መጽሐፍ እንድታዘጋጅ እግዚአብሔር ኤማ ስሚዝን ጠራት። በዚህ መንገድ ሰዎች በቤተክርስቲያን ጉባዔዎች ወቅት መዘመር ይችላሉ።

ምስል
የህጻናት ስብሰባ

እኔ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባል ነኝ። መዝሙር መዘመር እና በየሳምንቱ ቅዱስ ቁርባንን መቀበል እችላለሁ።

የሚቀባ ገፅ

ወደ ቤተክርስቲያን መሄድ እወዳለሁ

ምስል
የሚቀባ ገፅ

ቤተክርስቲያን መሄድ ለምን ትወዳላችሁ?

አትም