2021 (እ.አ.አ)
ኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ቁርባንን እንድንቀበል ጋብዞናል
መጋቢት 2021 (እ.አ.አ)


“ኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ቁርባንን እንድንቀበል ጋብዞናል፣” ሊያሆና፣ መጋቢት 2021 (እ.አ.አ)

ወርኃዊ የ ሊያሆና መልዕክት፣ መጋቢት 2021 (እ.አ.አ)

ኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ቁርባንን እንድንቀበል ጋብዞናል

በየሳምንቱ አዳኛችንን ስናስታውሰው እንነጻለን እንዲሁም እንፈወሳለን

ምስል
የመጨረሻው እራት

የመጨረሻው እራት፣ በካርል ሄንሪክ ብሎች

ከመሞቱ በፊት፣ ኢየሱስ ክርስቶስ የመጨረሻው እራት በመባል የሚታወቀውን የመጨረሻውን ምግብ በልቷል። በዚህ ምግብ መጨረሻ ላይ፣ ለደቀ መዛሙርቱ ስለ ቅዱስ ቁርባን አስተማራቸው። ዳቦውን ቆረሰና ባረከው። “ይህንን ለመታሰቢያ አድርጉት፣” አላቸው (ሉቃስ 22፥19)። በመቀጠልም፣ የወይን ጠጅ ጽዋውን ባረከ እና ሰጣቸው።

ምስል
ቤተሰብ ቅዱስ ቁርባንን ሲቀበል

የሳምንታዊው አምልኮ ሥነ ሥርዓት አንድ አካል

የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን በምድር ላይ ዳግም ስትመለስ ቅዱስ ቁርባን የሳምንታዊው አምልኮ ሥነ ሥርዓት አንድ አካል ሆነ። በቤተክርስቲያን ሥነ ሥርዓት ወቅት፣ ቅዱስ ቁርባኑ የክህነት ስልጣን ባላቸው ሰዎች ይባረክና ይተላለፋል። ከቅዱሳን መጽሐፍት የተወሰዱ ቃላትን በመጠቀም ይጸልያሉ ( ሞሮኒ 45ን ይመልከቱ)። ከዚህ በመቀጠል ኢየሱስን እና ለእኛ የከፈለውን መሥዋዕትነት ለማስታወስ እርሱ እንድናደርገው ባዘዘን መሠረት በጉባዔው ላይ የተገኘ ሁሉም ሰው ዳቦውን ይበላል እንዲሁም ውሃውን ይጠጣል።

ምስል
ወጣት ሴት ስትጸልይ

በአንጄላ ሱይተር የተነሣ ፎቶ

ለመካፈል መዘጋጀት

ቅዱስ ቁርባኑን ለመቀበል ለመዘጋጀት፣ ስለ ሕይወታችን እና ምርጫዎቻችን በታማኝነት ማሰብ ይኖርብናል። እግዚያብሄር ይቅር እንዲለን መጠየቅን ጨምሮ ባለፈው ሳምንት ስለ ሠራናቸው ስሕተቶች እና ኃጢያቶች መጸጸት ይኖርብናል። ቅዱስ ቁርባንን ለመቀበል ፍጹም ሰው መሆን የለብንም ሆኖም ግን ልባችን ትሁት መሆን አለበት።

ምስል
የጌተሰማኔው ጸሎት

የጌተሰማኔው ጸሎት፣ በዴል ፓርሰን

ከዳቦ እና ከውሃም በላይ

ቅዱስ ቁርባንን መቀበል የተቀደሰ፣ የብፅዕና ጊዜ ነው። ዳቦውን እና ውሃውን ስንቀበል የምንጸልየው የቅዱስ ቁርባን ጸሎት ኢየሱስ ክርስቶስ ለእኛ የሰጠንን ሥጋውን እና ደሙን እንድናስታውስ ያደርገናል። እርሱን ለመከተል እና ክርስቲያናዊ ሕይወት ለመኖር ቃል እንገባለን። የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት ለማክበር ጥረት ማድረጋችንን ለመቀጠል ቃል እንገባለን። በምላሹም፣ መንፈስ ቅዱስ ያጽናናል፣ ይመራናል እንዲሁም ይፈውሰናል።

ምስል
ጥምቀት

ቃል ኪዳኖችን ማደስ

የተጠመቅን ሰዎች ቅዱስ ቁርባንን በንጹሕ ልብ ስንቀበል፣ በጥምቀት ወቅት የገባነውን ቃል ኪዳን እናድሰዋለን። ይህ መንፈስ ቅዱስን መቀበልን እና ልክ እንደገና የተጠመቅን ያክል ከኃጢያታችን መጽዳትን ያካትታል። ይህ ኢየሱስ ለእያንዳንዳችን የሰጠን ተስፋ እና ምህረት ነው። ንስሐ ገብቶ ይቅርታን ለማግኘት ምንጊዜም አይረፍድም።

ምስል
ኢየሱስ ክርስቶስ ለኔፋውያን ቅዱስ ቁርባንን ሲያስተዋውቅ

ሁልጊዜ እኔን ታስታውሱኛላችሁ፣ በጋሪ ኤል ካፕ፣ ሊቀዳ አይችልም

ቅዱሳን መጽሐፍት ስለ ቅዱስ ቁርባን ምን ይላሉ?

ቅዱስ ቁርባንን ከመቀበላችን በፊት በታማኝነት ወደ ውስጣችን በማየት ራሳችንን በመንፈሳዊ መንገድ መመርመር፣ አለብን ( 1ኛ ቆሮንቶስ 11፥28ይመልከቱ)።

ከሙታን ከተነሳ በኋላ ኢየሱስ እንዴት ቅዱስ ቁርባንን መውሰድ እንዳለባቸው በአሜሪካዎች ውስጥ ላሉት ተከታዮቹ አሳያቸው ( 3 ኔፊ 18ይመልከቱ)።

በአሁን ዘመን ያሉ ነቢያት ለቅዱስ ቁርባን ዳቦ እና ውሃ እንድንጠቀም ነግረውናል፣ ሆኖም የምንበላው እና የምንጠጣው ያን ያክል ቁም ነገር የለውም ( ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 27፥2ይመልከቱ)። አለርጂ ያለባቸው ሰዎች ዳቦን የሚመስል ንጥረ ነገር መጠቀም ይኖርባቸዋል።

የመጨረሻው እራት፣ በካርል ሄንሪክ ብሎች፤ ወጣት ሴት ስትጸልይ በአንጄላ ሱይተር የተነሣ ፎቶ፣ የጌተሰማኔው ጸሎት፣ በዴል ፓርሰን፣ ሁልጊዜ እኔን ታስታውሱኛላችሁ፣ በጋሪ ኤል ካፕ፣ ሊቀዳ አይችልም

አትም