2021 (እ.አ.አ)
የቤተሰብ ታሪክ ቅድመ አያቶቻችንን ይረዳል
ታህሳስ 2021 (እ.አ.አ)


“የቤተሰብ ታሪክ ቅድመ አያቶቻችንን ይረዳል፣” ሊያሆና፣ ታህሳስ 2021 (እ.አ.አ)

ወርሀዊ የሊያሆና መልዕክት፣ ታህሳስ 2021 (እ.አ.አ)

የቤተሰብ ታሪክ ቅድመ አያቶቻችንን ይረዳል

የቤተሰብ ታሪክ ስራ ስለቤተሰብ አባሎቻችን ማወቅ እና መማር ነው። እንዲሁም ለእነርሱ የቤተመቅደስን ስራ ለመስራት ስለ ቅድመ አያቶቻችን መረጃ እንሰበስባለን።

ምስል
alt ጽሑፍ

ቤተሰቦች በሰማይ አባት የደስታ እቅድ ውስጥ ማዕከላዊ ናቸው። እርሱም ቤተሰቦች ለዘለአለም የሚቀጥሉበትን መንገድ አዘጋጅቷል። የቤተሰባችን ታሪክ እና የቤተመቅደስ ስራ ስንሰራ፣ የእኛን ቤተሰብ አባላት፣ በህይወት ያሉ እና የሞቱትን፣ ለማቀራረብ እንረዳለን። (“የመቅደስ ስራ” ማለት፣ ከትዳር ጓደኛችን ጋር መታተም አይነት የሆነ የራሳችን የቤተመቅደስ ስነስርዓቶችን መቀበል እና እንዲሁም በቤተመቅደስ ውስጥ ለቅድመ አያቶቻችን ስርአቶችን ማድረግ ነው።)

የቤተሰብ ታሪክ እና የቤተመቅደስ ስራ

በምድር ላይ የኖረ ወይም የሚኖር ማንኛውም ሰው የወንጌል ስርአቶች ያስፈልገዋል። ቅድመ አያቶቻችን ያን እድል ካላገኙ፣ በቤተመቅደስ ውስጥ ስነስርዓቶችን ልናደርግላቸው እንችላለን። ከእነዚህ ስነስርዓቶች አንዱ ከቤተሰብ አባላት ጋር መታተም ነው። “መታተም” ማለት ጻድቅ ከሆንን ከቤተሰቦቻችን ጋር ለዘለአለም መኖር እንችላለን ማለት ነው። ለቤተሰቦቻችን መታተም የምንችለው በቤተመቅደስ ውስጥ ብቻ ነው።

የቤተሰብ ታሪክ ሥራ በረከቶች

ምስል
ቤተሰብ

የቤተሰብ ታሪክ በህይወት ካሉ የቤተሰባችን አባላት ጋር ያለንን ግንኙነት ለማጠናከር ይረዳናል። እርስ በርሳችን ታሪኮችን፣ ፎቶግራፎችን እና ሌሎች ትውስታዎችን ስንካፈል፣ የቤተሰብ ትስስርን እንፈጥራለን። እርስ በርሳችን ያለንን ፍቅርም እናጠናክራለን። እንዲሁም በቤተሰባችን ታሪክ ላይ መስራት ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሚያቀርበን ነቢያት ቃል ገብተዋል።

ቅድመ አያቶቻችንን ማግኘት

ምስል
በቻይንኛ የተጻፉ መዝገቦች

የሰማይ አባት ከአሁኑ ቤተሰቦቻችን እና ከቅድመ አያቶቻችን ጋር እንድንታተም ይፈልጋል። ከቅድመ አያቶቻችን ጋር ከመታተማችን በፊት፣ ስለእነርሱ መረጃ መፈለግ እና ከዚያም ማስቀመጥ አለብን። ነገር ግን የቤተሰብ ታሪክ ስሞችን፣ ቀኖችን እና ቦታዎችን ከመመርመር በላይ ነው። ስለ ቅድመ አያቶቻችን ስንማር፣ ከእነርሱ ጋር የበለጠ እንደተገናኘን ይሰማናል።

አትም