2021 (እ.አ.አ)
ስለዚህ ተወልጃለሁ
ታህሳስ 2021 (እ.አ.አ)


የአካባቢ አመራር መልዕክት

ስለዚህ ተወልጃለሁ

ሌሎችን የማገልገል ተነሳሽነታችንን የምናገኘው እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ እና በቤዛው አማካኝነት ህያውነትን እና ዘላለማዊ ሕይወትን ለእኛ ለልጆቹ ለማምጣት ያለውን ዓላማ በመረዳት ነው።.

በምድራዊ አገልግሎቱ ብዙ ክስተቶች ውስጥ ክርስቶስ ለምን በምድር ላይ እንዳለ መግለፅ አስፈላጊ ሆኖ አገኘ።

እርሱን የመፈተን እና ተልዕኮውን የማስተጓጎል ሙከራ አለመሳካትን ተከትሎ ሰይጣን ከአጠገቡ ከተለየ በኋላ፣ ኢየሱስ ወደ ናዝሬት ምኩራብ ሄደ። ቆመ እና አላማውን የሚያሳካ ጥቅስን ከኢሳይያስ መጽሐፍ ውስጥ በመምረጥ ለተሰበሰቡት ሰዎች እንዲህ አስተዋወቀ፦

“የጌታ መንፈስ በእኔ ላይ ነው፣ ለድሆች ወንጌልን እሰብክ ዘንድ ቀብቶኛልና፣ ለታሰሩትም መፈታትን ለዕውሮችም ማየትን እሰብክ ዘንድ፣ የተጠቁትንም ነፃ አወጣ ዘንድ የተወደደችውንም የጌታን ዓመት እሰብክ ዘንድ ልኮኛል… እርሱም ዛሬ ይህ መጽሐፍ በጆሮአችሁ ተፈፀመ ይላቸው ጀመር” (ሉቃስ 4፥18-19፣ 21 ይመልከቱ)።

በሌላ ጊዜ ሴት ልጇን ጋኔን ክፉኛ ስለያዛት አንዲት ከነዓናዊ ሴት ለልጇ ምህረት እንዲያሳይ ያቀረበችውን ልመና ቸል ስለማለቱ አስመልክቶ ለደቀመዛሙርቱ ሲመልስ እንዲህ አስተማረ፦

“ከእስራኤል ቤት ለጠፉት በጎች በቀር አልተላክሁም አለ” (ማቴዎስ 15፥24 ይመልከቱ)። የምድራዊ አገልግሎቱን አላማ ለመናገር እና የእርሱ ታዳሚዎች ማን እንደሆኑ ለመለየት የሴቲቷን ልጅ በመፈወስ የተጠናቀቀውን ይህን ምሳሌ ተጠቀመ። የእስራኤል ቤት በቤተሰብ ትውልዶች አባል የሆኑ ብቻ አይደሉም። የከነናዊ ሴቷ እንዳሳየችው በእርሱ እምነት ስላላቸው አባል የሆኑትንም ሁሉ ያካትታል።

እንደገና በሌላ ጊዜ ስለ ምድራዊ ሕይወቱ አላማ ኒቆዲሞስን ለማነፅ ጥረት አደረገ።

“ሙሴ በምድረ በዳ እባብን እንደሰቀለ እንዲሁ፦

“በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ የሰው ልጅ ይሰቀል ይገባዋል።

“በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለምን እንዲሁ ወዶአልና።

“ዓለም በልጁ እንዲድን ነው እንጂ በዓለም እንዲፈርድ እግዚአብሔር ወደ ዓለም አልላከውምና።

“በእርሱ በሚያምን አይፈረድበትም፣ በማያምን ግን በአንዱ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ስላላመነ አሁን ተፈርዶበታል።

“ብርሃንም ወደ ዓለም ስለመጣ ሰዎችም ስራቸው ክፉ ነበርና ከብርሃን ይልቅ ጨለማን ስለ ወደዱ ፍርድ ይህ ነው።

“ክፉ የሚያደርግ ሁሉ ብርሃንን ይጠላልና ስራውም እንዳይገለጥ ወደ ብርሃን አይመጣም።

“እውነት የሚያደርግ ግን ስራው በእግዚአብሔር ተደርጎ እንደሆነ ይገለጥ ዘንድ ወደ ብርሃን ይመጣል” (ዮሐንስ 3፥14–21 ይመልከቱ)።

በምድር ቆይታው የመጨረሻ ቀናት የአይሁዶች ነጉሥ ስለመሆኑ አስመልክቶ ለጴንጤናዊው ጲላጦስ ጥያቄ ምላሽ ሲሰጥ፣ በድጋሚ የመወለዱን አላማ አወጀ፦

“ኢየሱስም መልሶ መንግስቴ ከዚህ ዓለም አይደለችም፤ መንግስቴ ከዚህ ዓለም ብትሆን ወደ አይሁድ እንዳልሰጥ ሎሌዎቼ ይዋጉልኝ ነበር፤ አሁን ግን መንግስቴ ከዚህ አይደለችም አለው።

“ጲላጦስም እንግዲያ ንጉሥ ነህን? አለው። ኢየሱስም መልሶ እኔ ንጉሥ እንደሆንሁ አንተ ትላለህ። እኔ ለእውነት ልመሰክር ስለዚህ ተወልጃለሁ ስለዚህም ወደ ዓለም መጥቻለሁ፤ ከእውነት የሆነ ሁሉ ድምፄን ይሰማል አለው” (የሐንስ 18፥36-37) ይመልቱ።

በድንግል መፀነስ ተዐምራት በመታጀብ የኢየሱስ ክርስቶስን ወደ ምድር መምጣት ሁላችንም ከእርሱ ጋር በምንካፈለው በሰው ልጅ ውልደት ልምምድ አማካኝነት ማክበር ለእያንዳንዳችን ያለውን የእርሱን ምድራዊ ሕይወት ጥቅም ትኩረት እንድንሰጥ ሊያደርግ ይገባል። ከላይ የተጠቀሱት ጥቅሶች ለየግል ውስጣዊ ምርመራ ይጋብዙናል፦

በምን ዓይነት መንገድ ነው የክርስቶስ ውልደት ለእኛ ያረጋገጠው ፈውስ የሚያስፈልገን እናም በእርሱ ላይ ባለን የማይወላውል እምነት ቆራጥነት አማካኝነት በማንኛውም ሰዓት ማግኘት የምንችለው?

ልክ እንደ ከነዓናዊቷ ሴት የእስራኤል ቤት ለመሆን ብቁ እንሆን ዘንድ በምን ዓይነት መንገድ ነው እንቅስቃሴዎቻችን በእርሱ ላይ ያለንን እምነት እንዲያሳዩ የምናደርገው?

በዚህ ዓመት ውስጥ ያደረግናቸውን ውሳኔዎች እና የወሰድናቸውን ተግባሮች ስናስብ ሁሌም በእውነት ተራምደናል እናም ያንን በማድረጋችን በኩራት በበለጠ ብርሃን እና ጥበብ ተባርከናል ማለት እንችላለን? ካልቻልን፣ ካሁን ጀምሮ ይህን ለማድረግ ቃል ለመግባት ፍቃደኞች ነን?

የእርሱን ድምፅ መስማት መቀጠል የምንችለው እንዴት ነው?

እነዚህ ጥያቄዎች የገናን በዓል በዓመቱ መጨረሻ ወር ላይ ዝም ብለን የምናከብረው ክስተት እና የሚቀጥለውን ታህሳስ በመጠባበቅ ወደ ሌሎች እንቅስቃሴዎች እንዳናመራ እንደሚረዱን ተስፋ እናደርጋለን። የገና በዓል እንደ ክርስቶስ ደቀመዛሙርት በእርግጥ ማን እንደሆንን ለመገምገም ሊረዳን ይገባል። የእርሱ ውልደት በግል እና በቤተሰብ ሕይወታችን ውስጥ ታላቅ ተፅዕኖ እና በረከት እንዲኖረው ምን ማድረግ እንደምንችል የበለጠ ለመረዳት ለመሻት ይህን እድል መጠቀም ይኖርብናል።

ለብዙ ዓመታት ቤተሰባችን የገናን በዓል በጋራ ለማክበር ጥረት ያደርጋሉ። በእያንዳንዱ ዓመት በታህሳስ 25 እና 31 (እ.አ.አ) መካከል፣ በአንድ ቦታ የምንሰበሰብበትን እና በጋራ ሰዓት የምናሳልፍበትን ቀን እንመርጣለን። በዛ ዓመት ውስጥ ለእያንዳንዱ የተከሰተውን ክስተት ዝርዝር እናካፍላለን። ብዙ ልጆች ሲወለዱ እና ሲያድጉ፣ ለእያንዳንዱ ክስተት ደስታን የጨመሩ የሚያስደስቱ ጨዋታዎችን አክለናል። ምንም እንኳን ሁላችንም እራሳችንን የክርስቶስ ደቀመዛሙርት አድርገን ብንወስድም፣ በሐይማኖት እምነት እና ተግባር ልዩነት ምክንያት፣ ብዙውን ጊዜ እያንዳንዱ ቤተሰብ ወደ ትልቁ የቤተሰብ ስብሰባ ከመምጣታቸው በፊት የራሳቸውን የገና በዓል በቤታቸው ያከብራሉ። የቅርብ የሆነ እና እያደገ የመጣው ልምድ አንዳንድ ጊዜ የሆነ ሰው ለልጆች ስጦታዎችን ያመጣል፣ ያም ልጆች ስለክስተቱ ያላቸውን ጉጉት ይጨምራል። እነዚህ መልካም ጊዜዎች ናቸው።

መልካም የቤተሰብ የገና በዓል ትውስታዎችን ለማጠናከር ያደረግናቸውን ነገሮች ሳሰላስል፣ የክርስቶስ ውልደት ያመጣውን የእድል ሙሉነት ግንዛቤ በውስጤ የበለጠ ለማድረግ ታላቅ ፍላጎትን አነሳስቷል።

አዎ፣ እያንዳንዱ የቤተሰባችን አባል የአዳኙን የበለጠ የመፈወስ ኃይል ይፈልጋል። የእስራኤል ቤት አባሎች ለመሆን ለመብቃት እያንዳንዳችን የበለጠ መስራት እንችላለን። በኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል በቀረበው እውነታ እና ጥበብ ውስጥ የበለጠ በፅናት ልንራመድ ይገባል፣ ብዙ ጊዜ የእርሱን ድምፅ ለመስማት ስንሞክር እንኳን። ስለሆነም፣ በዚህ ዓመት የቤተሰብ ስብሰባችን እንዴት ይህን ማድረግ እንደምንችል የበለጠ ለመስራት የገናን በዓል የማክበር ዕድልን እጓጓለሁ።

ተመሳሳይ ነገርን እንድታደርጉ እጋብዛለሁ። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።

ጆሴፍ ደብሊው ሲታቲ እንደ አጠቃላይ ሰባዎች ባለስልጣን የተሾሙት በሚያዚያ 2009 (እ.አ.አ) ነበር። ከግላዲስ ናንጎኒ ጋር ትዳራቸውን መስርተዋል፤ የአምስት ልጆች ወላጆች ናቸው።

አትም