2021 (እ.አ.አ)
የሱዳን ልዑካን ቡድን የሶልት ሌክ ቤተክርስቲያን ቦታዎችን ጎበኙ
ታህሳስ 2021 (እ.አ.አ)


በድረ ገፅ ላይ ብቻ

የሱዳን ልዑካን ቡድን የሶልት ሌክ ቤተክርስቲያን ቦታዎችን ጎበኙ

“ስለ[ዩታ] ያገኘነው ግንዛቤ ችግሮችን እንዴት ማሸነፍ እንደሚችል ያስተማረን ማህበረሰብ መሆኑን ነው። ሌላኛው ያገኘነው ግንዛቤ ይህ ቤተክርስቲያን ከማህበረሰቡ ጋር በመሆን የበጎ አድራጎት መርሆዎችን ለማጠናከር መስራት መቻሉን ነው።” የሱዳን የቡራኬ እና የሐይማኖት ጉዳይ ሚኒስቴር የሆኑት ናስርልዲን ሞፋራህ በቅርቡ በሶልት ሌክ ሲቲ ውስጥ የቤተክርቲያኗን ዋና መስሪያ ቤት በጎበኙበት ወቅት ይህንን ሃሳብ ሰጥተዋል። የሱዳን መንግስት መሪዎች ልዑካን ቡድንም ከአቶ ሞፋራህ ጋር ነበሩ። አንድ ላይ በመሆንም ከኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን የበላይ መሪዎች ጋር ተገናኝተዋል።

በጉብኝቱ ወቅት ስድስት አባላት ያሉት የሱዳን ልዑካን ቡድን የቤተመቅደስ አደባባይን፣ የደህንነት አደባባይን፣ የበጎ አድራጎት ማዕከልን እና የኤጲስ ቆጶስ ግምጃ ቤት ማዕከልን ጎብኝተዋል። ከቤተክርስቲያኗ ቀዳሚ አመራር፣ ከማዕከላዊ ምስራቅ ደቡብ አፍሪካ አካባቢ አመራር እና ከአጠቃላይ የሴቶች መረዳጃ አመራር ጋርም ተገናኝተዋል። በተጨማሪም በሶልት ሌክ ሸለቆ አካባቢ የሚገኝን መስጊድ ጎብኝተዋል። ፎቶዎችን ለመመልከት እና ስለ ክስተቱ የበለጠ ለማንበብ፣ የማዕከላዊ አፍሪካ ፌስቡክ ገፃችንን ይጎብኙ፦ https://www.facebook.com/churchofjesuschristafricacentral/

አትም