2021 (እ.አ.አ)
በታህሳስ 2000(እ.አ.አ)፦መጽሐፈ ሞርሞን በአማርኛ፣ በኢሲሆሳ ቋንቋ ወጣ።
ታህሳስ 2021 (እ.አ.አ)


ወሩ በቤተክርስቲያኗ ታሪክ ውስጥ

በታህሳስ 2000(እ.አ.አ)፦መጽሐፈ ሞርሞን በአማርኛ፣ በኢሲሆሳ ቋንቋ ወጣ።

በታህሳስ 2000(እ.አ.አ.) የአማርኛ (በኢትዮጲያ እና በኤርትራ ውስጥ የሚነገር ቋንቋ) እና የኢሲሆሳ (በደቡብ አፍሪካ ውስጥ የሚነገር ቋንቋ) የመጽሐፈ ሞርሞን ትርጉሞች ህትመት ለመጀመሪያ ጊዜ ወጡ።

ገመቹ ዋሪዮ ጎጃ፣ የኢትዮጲያ አዲስ አበባ ፕሬዚዳንት በጥር 2001(እ.አ.አ) ሲናገር “ዛሬ መጽሐፈ ሞርሞንን በአማርኛ የተቀበልኩኝ የመጀመሪያው ኢትዮጲያዊ አባል ሆንኩኝ እናም በጣም በጣም ደስተኛ ነኝ” ብሏል። “የመጀመሪያዎቹን ቅጂዎች መጽሐፉን በመተርጎም አብረውኝ ለሰሩት አባላት ሳከፋፍል ሁሉም በደስታ ጮኹ እንዲሁም በደስታ ወደላይ ዘለሉ። የራሴን ቅጂ ወደቤት ወሰድኩኝ እናም ቤተሰቤ በጉጉት መጽሐፉን ከበውት አንዳቸው ለሌላው በአማርኛ አነበቡ። አስደናቂ ነበር።”

በተመሳሳይ ዓመት ቀደም ብሎ መጽሐፈ ሞርሞን ወደ ስዋህሊ ተተረጎመ ይህም በምስራቅ አፍሪካ ያሉ የቤተክርስቲያኗ አባላት በራሳቸው ቋንቋ እንዲያነቡት ፈቀደ። በታንዛንያ የቻንጎምቤ ቅርንጫፍ ፕሬዝዳንት የሆነው ዊሊያም ጊዴሜ እንዲህ አለ “ከአሁን በኋላ መጽሐፈ ሞርሞንን ለመላው ቤተሰቤ በፍፁም መረዳት ማንበብ እችላለሁ። በጣም አመስጋኝ ነኝ።”

በታህሳስ 2000(እ.አ.አ) ውስጥ ተተርጉመው ያለቁ ቋንቋዎች አጠቃላይ ቁጥር 100 ደረሰ። ስልሳ አንዱ የመጽሐፈ ሞርሞን ሙሉ ትርጉሞች ናቸው፤ 39ኙ ደግሞ የተወሰኑ ምዕራፎች ትርጉሞች ናቸው። በአፍሪካ ውስጥ ብዙ የቤተክርስቲያኗ አባላት አሁን መጽሐፈ ሞርሞንን በራሳቸው ቋንቋዎች በማንበብ ይደሰታሉ።

የመጽሐፈ ሞርሞን ወደ ብዙ ቋንቋዎች መተርጎም ከዚህ ቀደም መጽሐፉ ስለቤተክርስቲያኗ ለሚማሩ ሰዎች ባልነበረበት አካባቢዎች ሚስዮናዊ ስኬትን ለማሳደግም ተስፋ ይሰጣል። በኢትዮጲያ ውስጥ እያገለገለ ያለ አንድ ሚስዮናዊ ለፕሬዚዳንት ገመቹ እንዲህ ብሎ ነገረው፣ “አሁን በስራ የበለጠ ልንጠመድ ነው።” —ጁሊ ብረፍ፣ የአፍሪካ ማዕከላዊ አካባቢ የቤተክርስቲያን ታሪክ ሚስዮናዊ

አትም