2022 (እ.አ.አ)
በቤተክርስቲያን ጥሪዎች ውስጥ ማገልገል
መጋቢት 2022 (እ.አ.አ)


“በቤተክርስቲያን ጥሪዎች ውስጥ ማገልገል፣” ሊያሆና፣ መጋቢት 2022 (እ.አ.አ)

ወርኃዊ የ ሊያሆና መልዕክት፣ መጋቢት 2022 (እ.አ.አ)

በቤተክርስቲያን ጥሪዎች ውስጥ ማገልገል

የቤተክርስቲያን መሪዎች አባሎችን “ጥሪዎች” ተብሎ በሚታወቀው በተለየ ሃላፊነት ውስጥ እንዲያገለግሉ ይጠይቃሉ። ጥሪዎች ለአባሎች ሌሎችን እንዲያገለግሉ እና ወደ እግዚአብሔር እንዲቀርቡ እድልን ይሰጣሉ።

ምስል
አንድ ሰው በዊልቸር ተቀምጦ የቤተክርስቲያን ትምህርት ሲያስተምር

ፎቶ በዴቪድ ቦወን ኒውተን

በጥሪዎቻችን ውስጥ ስናገለግል፣ የእግዚአብሔር ስራ እንዲሳካ እናግዛለን። ሌሎችን ስለ ሰማይ አባት እና ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ እናስተምራለን እናም የምናስተምራቸውን ወደ እነርሱ እንዲቀርቡ እንረዳለን። በታማኝነት ስናገለግል በረከቶችን እንቀበላለን።

ጥሪዎችን መቀበል

ምስል
ወጣት ወንድ ከቤተክርስቲያን ታዳሚዎች ፊት ቆሞ

በቤተክርስቲያን ውስጥ የሚያገለግሉ ሰዎች ከእግዚአብሔር የተጠሩ ናቸው። የቤተክርስቲያን መሪዎች በእያንዳንዱ ጥሪ ውስጥ ማን እንዲያገለግል ለመጠየቅ እንዲያውቁ ለመነሳሳት ይጸልያሉ። አንድ መሪ ከዛ አንድን አባል እንዲያገለግል ይጠይቃል እናም የጥሪውን ሃላፊነት ይገልፃል። የዋርድ ወይም የቅርንጫፍ አባሎች የድጋፍ ድምፃቸውን በሚሰጡበት በቤተክርስቲያን ስብሰባ ውስጥ አባሎች ድጋፍ ያገኛሉ። ይህ ማለት የሚጠራውን ሰው ለመደገፍ ፍቃደኞች ናቸው ማለት ነው። አባሉ ከዛ የክህነት ስልጣን ባለው ሰው በረከት ይሰጠዋል። ይህ ተለይቶ መሾም ተብሎ ይጠራል። አባሉ/ሏ በጥሪው/ዋ ውስጥ እንዲተገብር/ትተገብር እና ሌሎችን ለመባረክ እንዲረዳው/ት ስልጣን ይሰጠዋል/ታል።

ኤጲስ ቆጶሶች

ኤጲስ ቆጶስ የዋርድ መሪ ነው። (በቅርንጫፍ ውስጥ የቅርንጫፍ ፕሬዝዳንት ከኤጲስ ቆጶስ ጋር ተመሳሳይ ነው።) የካስማ ፕሬዝዳንት ብቁ የክህነት ስልጣን ተሸካሚን እንደ ኤጲስ ቆጶስ ሆኖ እንዲጠራ ሃሳብ ያቀርባል። የቀዳሚ አመራር ጥሪውን ያፀድቃሉ። ኤጲስ ቆጶሱ ከዛ ድጋፍ ያገኛል እናም ለማገልገል ተለይቶ ይሾማል። ከዛ የክህነት ቁልፍን ይቀበላል ይህም ማለት ዋርዱን የመምራት ስልጣን አለው ማለት ነው። እንደ ኤጲስ ቆጶስ፣ የዋርዱን አባሎች በሙሉ ያገለግላል እንዲሁም ይመራል።

አመራሮች

የክህነት ምልዓተ ጉባኤዎች እና የሴቶች መረዳጃዎች፣ ወጣት ሴቶች፣ ህፃናት እና የሰንበት ክፍል አወቃቀሮች በአመራሮች ነው የሚመሩት ብዙውን ጊዜ በአንድ ፕሬዝዳንት እና በሁለት አማካሪዎች። የሽማግሌ ምልዓተ ጉባኤዎች አመራሮች በካስማ ፕሬዝዳንቱ ነው የሚጠሩት እና ተለይተው የሚሾሙት። የኤጲስ ቆጶስ አመራር አባሎችን በዋርዱ በሌላ አመራሮች ውስጥ እንዲያገለግሉ ይጠይቃሉ እናም ለይተው ይሾሟቸዋል። ሁሉም መሪዎች አባሎችን በየምልዓተ ጉባኤያቸው ወይም አወቃቀራቸው ውስጥ ያገለግላሉ። የአባሎችን ፍላጎቶች ያገለግላሉ እንዲሁም የእግዚአብሔርን ፍቅር እንዲሰማቸው ያግዛሉ።

ምስል
አንዲት ሴት ህፃን ለያዘች እናት ምግብን ስታመጣ

ሌሎች ጥሪዎች

ሌሎች የቤተክርስቲያን ጥሪዎች ማስተማርን፣ በመዝሙር መርዳትን፣ መዝገብ መያዝን፣ ለወጣቶች ወይም ለህፃናት እንቅስቃሴዎችን ማቀድን እና በሌላ መንገዶች ማገልገልን ያካትታሉ። በቤተክርስቲያን ውስጥ እያንዳንዱ ጥሪ አስፈላጊ ነው እናም አባሎች ሌሎችን እና እግዚአብሔርን እንዲያገለግሉ እድል ይሰጣቸዋል። ሁላችንም ጥሪያችንን ለማከናወን ስንሰራ ሌሎችን እናጠነክራለን እናም ቤተክርስቲያኗ እንድታድግ እናግዛለን።

አትም