2022 (እ.አ.አ)
የሚስዮን አገልግሎታችሁ እና የተቀበረው ውርስ ምሳሌ
መጋቢት 2022 (እ.አ.አ)


የአካባቢ አመራር መልዕክት

የሚስዮን አገልግሎታችሁ እና የተቀበረው ውርስ ምሳሌ

በምሳሌው ውስጥ ያሉት የባለጸጋው ልጆች ስለሕይወት እውነት በራሳቸው ምስክርነት ላይ መታመን የሚገባቸው ጊዜ እንደሚመጣ አወቁ።

በአስራዎቹ እድሜ ውስጥ እያለሁ ለጋ አእምሮዬን የሚማርከኝ የነበረው አንድ ትልቅ የፍራፍሬ እርሻ ስለነበረው አንድ ባለጸጋ የሚናገር ታሪክ ነበር። አንድ ችግር ብቻ ነበረበት። ልጆቹ ያደጉት የፍራፍሬ እርሻው ሀብታም ካደረገው በኋላ ነበር። ብዙ አገልጋዮች ነበሩት፤ ስለዚህም ልጆቹ ምንም ከባድ ስራ መስራት አይጠበቅባቸውም ነበር። ልጆቹ የፍራፍሬ እርሻውን ይፈልጉት እንዳልነበረ አስተዋለ። በፍራፍሬ እርሻው ውስጥ መስራት የአገልጋዮቹ ስራ እንደሆነ አሰበው ነበር። ለእነሱ በጣም ከባድ እና በጣም አሰልቺ ነበር። ለዚህ ጽሁፍ ዓላማ ታሪኩን የተቀበረው ርስት ምሳሌ ብዬ እጠራዋለሁ። ባለጸጋው፣ ልጆቹ በዚህ ዝንባሌያቸው ከቀጠሉ እርሱ ከሞተ በኋላ ሊያጋጥሟቸው ስለሚችሉት ችግሮች አሳስቦት ነበር።

ስለዚህ አንድ ቀን ሰበሰባቸውና ለውርሳቸው ያካበተውን ሃብት ድርሻ ለእያንዳንዳቸው ይሰጥ ዘንድ ኑዛዜ እንደጻፈ ነገራቸው። ኑዛዜውን አሽጎት የነበረ ሲሆን መክፈት የሚችሉትም እሱ ከሞተ በኋላ ብቻ ነበር። ስለዚህ እርሱ ካረፈ በኋላ ስለሚሆነው ነገር ልጆቹ በጣም ጓጉ። እያንዳንዳቸው የየራሳቸውን ውርስ ድርሻ ለመውሰድ እና በተሟላ ደስታ እንዲሁም ምቾት የተሞላ ኑሮ በመኖር ለመቀጠል በጉጉት ይጠባበቁ ነበር።

በመጨረሻም በኑዛዜው ውስጥ ያለው የሚታወቅበት ቀን መጣ። በኑዛዜውም ውስጥ ርስታቸውን በፍራፍሬ እርሻው የተለያዩ ቦታዎች በድብቅ እንደቀበረ ነገራቸው። በእያንዳንዱ ልጅ ድርሻ ላይ ስሙ ተጽፎበት ነበር። ነገር ግን የቀበረበትን ሚስጥራዊ ቦታ ማወቅ የእነርሱ ድርሻ ነበር። ያንን ማድረግ የሚቻልበት ብቸኛው መንገድ የፍራፍሬ እርሻውን መቆፈር ነበር። አንድ ጥንቃቄ ብቻ ማድረግ ያስፈልጋቸው ነበር። የፍራፍሬ ዛፎቹን እንዳይጎዱ መጠንቀቅ ነበረባቸው!

ስለዚህ ቁፋሮው ተጀመረ። ሙሉውን የፍራፍሬ እርሻ ቆፈሩ ሆኖም አንድም ሃብት አላገኙም ነበር። አባታቸውን ሁልጊዜ ቃሉን የሚጠብቅ ሃቀኛ ሰው እንደነበረ ስለሚያውቁ የፍራፍሬ እርሻውን ለሁለተኛ ጊዜ ቆፈሩ። በዚህ ጊዜ በፍራፍሬ እርሻው ውስጥ ያለው አፈር ሙሉ በሙሉ መቆፈሩን አረጋግጠዋል፣ ነገር ግን አሁንም ምንም አይነት ውድ ሀብት አላወጡም ነበር። አሁን ለሁለተኛ ጊዜ በትልቁ ሜዳ ላይ ያለውን አፈር ቆፍረው ሲጨርሱ በፍራፍሬ እርሻው ውስጥ ያሉት የዛፎች ቅርንጫፎች ሁሉ እየተወደቁ መሆናቸውን እንዲሁም ብዙ ጥሩና የበሰለ ፍሬ ያፈሩ መሆናቸውን አስተዋሉ። ስለዚህም ቁፋሯቸውን አቆሙና እያንዳንዳቸው በፍራፍሬ እርሻው የነበሩትን ፍሬዎች እንደአቅማቸው ለቀሙና ሸጡ። ያኔ ነው የአባታቸው ኑዛዜ እንቆቅልሽ የተገለጠላቸው። የተደበቀው ሀብት ያለው ጥሩ ፍሬ እንዲያፈራ የአትክልት ቦታውን መቆፈር እና መንከባከቡ ላይ ነበር። ጥሩ እንክብካቤ እስከተደረገለላቸው ጊዜ ድረስ ዛፎቹ ብዙ ጥሩ ፍሬ ማፍራታቸውን ይቀጥላሉ። የመንከባከቡን ከባድ ስራ ከሰሩ በርግጥ ገንዘብ በዛፎች ላይ ይበቅላል የሚለውን ጠቃሚ መመሪያ አባታቸው በሞተ ጊዜ አስተምሯቸዋል። ከዚያን ጊዜ ጀምሮም ጠንክረው ለመሥራት ወሰኑ እንዲሁም አባታቸው የተወላቸውን ርስት ጠበቁ።

የተደበቀው ሃብት ምሳሌ ከሚስዮናዊ ስራ ጋር ይመሳሰላል። እንደወጣት እጩ ሚስዮናዊ፣ በወጣትነታችሁ አብዛኛውን ጊዜያችሁን በትምህርት ቤት አሳልፋችሁ ሊሆን ይችላል፤ እናም ከዚያም ውስጥ አብዛኛውን ጊዜ በወላጆቻችሁ ወይም በአዋቂ አሳዳጊዎቻችሁ ሥር ነበራችሁ። የቤተክርስቲያኗ አባላት ከሆኑ፣ ከወንጌል ጋር አስተዋውቀዋችሁ ይሆናል፣ እንዲሁም የእነርሱ ምስክርነት በምስክርነታችሁ ላይ ተጽዕኖ አድርጎ ሊሆን እንደሚችል ነው። የግል የአምልኮ ልማዶቻችሁ እነርሱ በቤት ውስጥ የመሠረቱትን ልማዶች የተከተሉ ሊሆኑ ይችላሉ—የቤተሰብ ጸሎት፣ የቤተሰብ ንባብ ወይንም የቅዱሳን ጽሁፎች ጥናት፣ የቤተሰብ የቤት ምሽት፣ በቤተክርስቲያን መሳተፍ እንዲሁም በአቅራቢያችሁ የሚገኝ ከሆነ በቤተመቅደስ መሳተፍ። ክፍያችሁን ከፍለዋል፣ ዩኒፎርማችሁን እና ልብሳችሁን ገዝተዋል እንዲሁም ለትምህርት ቤታችሁ እና ለሌሎች የግል ፍላጎቶቻቸሁ የሚያስፈልጓችሁን ሌሎች ወጪዎች አሟልተዋል። የትምህርት ቤት ሕይወታችሁ የታቀደ ነበር—የትምህርት እና የተግባራት የጊዜ ሰሌዳዎች ይሰጧችሁ ነበር እነሱንም ትከተሉ ነበር። ስለእነዚህ ነገሮች በግላችሁ ብዙ መጨነቅ አያስፈልጋችሁም ነበር። ስለዚህ ሕይወት በዚህ መንገድ ትቀጥላለች ብሎ መጠበቅ እንግዳ ነገር አይደለም።

ሆኖም ልክ የባለጸጋው ልጆች እንደተረዱት በህይወት አውነቶች የራሳችሁ ምስክርነት ላይ መተማመን የሚገባችሁ ጊዜ ይመጣል።ይህ የሚመጣው የግል ጥረት በማድረግ ብቻ ነው። ይህን ካላደረጋችሁ፣ በአዋቂነት ህይወታችሁ ውስጥ ላሉት የተለመዱ ችግሮች የሚያስፈልጉ መፍትሄዎችም በሌሎች ሊቀርቡ እንደሚገባቸው በማመን ልትቀጥሉ ትችላላችሁ። እንደአዋቂነታችሁ የሚያጋጥሟችሁን የህይወት ችግሮች በመፍታት ረገድ የራሳችሁን ሃላፊነት ሳትገነዘቡ ልትቀሩ ትችላላችሁ። በዚህ ዝንባሌ፣ ለራሳችሁ ማድረግ ያለባችሁን ነገር ባለማድረጋችሁ በተለምዶ ሌሎችን ወደመውቀስ ልትሄዱ ትችላላችሁ።አስቀድሞ ከባድ እና አሰልቺ የመሰላቸውን የፍራፍሬ እርሻ በመቆፈር ጥረት ሲያደርጉ የባለጸጋው ልጆች በፍራፍሬ እርሻው ውስጥ የተቀበረውን እውነተኛ ሀብት ያገኙት በራሳቸው ጥረት እንደሆነ ተገነዘቡ—ሲኮተኩቱት እና የአፈሩን ንጥረ ነገር ለሥሩ ሲያቀርቡለት የጎመራ ፍሬ።

በዚህ ምሳሌ መሰረት ህይወታችሁን ለዘለዓለም የሚባርከውን ምርጫ ይኸውም በሚስዮን ለማገልገል በደንብ ለመዘጋጀት የሚረዷችሁን የሚከተሉትን ሶስት ነገሮች እጠቁማለሁ።

  1. የመጀመሪያው እርምጃ በአንድያ ልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ የሃጥያት ክፍያ በተገኘው በአብ የደስታ እቅድ ላይ የማይናወጥ እምነት በማግኘት ይጀምራል። ደስተኛ እና ውጤታማ እንድትሆኑ ይፈልጋል። ይህንን ግብ ማሳካት ትችሉ ዘንድ መንገዶችን እና እድሎችን አቅርበውላችኋል። በሚስዮን ማገልገል ከእነዚህ እድሎች አንዱ ነው። ስለደስታ እቅድ የበለጠ መማር እና ለሌሎች ማካፈል ታላቅ ደስታን ያመጣል።

አልማ እንዳስተማረው፣ “አዕምሮአችሁን[እንድታነቁት]፣ እናም [እንድታነሳሱት]፣ በቃሌም እስከምትለማመዱ እንኳን፣ እናም” የእናንተን ግላዊ ዘላለማዊ ደስታ በሚፈልጉ እና በሰማይ አባት ልጆች ሁሉ ላይ “ቅንጣት ያህል እምነትን [እንድትለማመዱ]”1 ያስፈልጋል።

  1. ይህ ለራሳችሁ እና ለሌሎች ይህንን በረከት ወደመፈለግ ወደ ሁለተኛው ደረጃ ይመራችኋል። “ከማመን በላይ የበለጠ ለመፈለግ ባትችሉም፣ ለቃላቴ በውስጣችሁ ትንሽ ቦታ ለመስጠት” እስከምትችሉ ድረስ ይህ ፍላጎት በእናንተ እንዲሰራ አድርጉ2። ሚስዮን ገና እያገለገላችሁ ካልሆነ፣ ልክ በአባታቸው የተገባውን ቃል እንደታመኑት እንደባለጸጋው ልጆች ለሚስዮን አገልግሎት እራሳችሁን በትጋት ለማዘጋጀት እድሎችን በንቃት መፈለግ ትጀምራላችሁ። የሚስዮናዊ ዝግጅት ትምህርትን ትቀላቀላላችሁ፤ በዚያም Missionary Preparation Lessons, Africa Central Area የተባለውን የማሰልጠኛ መጽሃፍ አንድ ቅጂ በሽማግሌዎች ቡድን ወይም በኤጲስ ቆጶሳችሁ አማካኝነት ታገኛላችሁ። በዚህ በራሪ ወረቀት ውስጥ ያሉት ትምህርቶች የተማራችኋቸውን እያንዳንዱን መርሆች እንድትሞክሯው በውጤቱም ስለመርሁ እውነትነት እና ሃይል የግል ምስክርነት እንድታዳብሩ ለመርዳት ተዘጋጅተዋል። እያንዳንዳቸው አስራ ሁለቱ ትምህርቶች እናንተን ወደሚከተሉት ለመምራት መረጃዎችን ያቀርባሉ 1) እንድታሰላስሉ 2) እንደታጠኑ እና እንድትወያዩ እንዲሁም 3) በሳምንት አንድ ትምህርት በመሸፈን በአስራ ሁለት ሳምንታት ጊዜ ውስጥ በእያንዳንዱ መርህ ላይ የራሳችሁን ምስክርነት እንድታገኙ እንድትዘጋጁ ይጋብዟችኋል። አሁን ሚስዮን እያገለገላችሁ ከሆነ፣ ይህንን በራሪ ወረቀት ከሚስዮን ፕሬዘዳንቱ አግኙ እና በግል ጥናታችሁ እንዲሁም በየዕለቱ በስራችሁ ስለእያንዳንዱ መርህ ያላችሁን ግንዛቤ ለማደስ ተጠቀሙበት።

  2. በሚስዮናውያን የዝግጅት ትምህርቶች በትጋት መስራት ልክ የባለጸጋው ልጆች ለመጀመሪያ ጊዜ ሜዳውን እንደቆፈሩት ማለት ነው። በአባታቸው ተማምነው ነበረ ነገር ግን በመጀመሪያ ቁፋሯቸው ምንም እንኳ በዚያ ደረጃ ላይ በፍራፍሬ እርሻው የነበሩት ዛፎች በተሻለ ሁኔታ መለወጥ እንደጀመሩ አይተው የነበረ ሊሆን ቢችልም ተስፋ ያደረጉትን ሃብት አላስገኘም። ስለዚህ ሦስተኛው እርምጃ የባለጸጋው ልጆች ከመጀመሪያው ቁፋሮ በኋላ ያደረጉትን ማድረግ ነው—የሙሉ ጊዜ ሚስዮናዊ ሆናችሁ ወደሚሲዮኑ መስክ ስትገቡ የተማራችኋቸውን መርሆች በሥራ ላይ በማዋል ረገድ የበለጠ ጠንቃቃ እና ትጉ ሁኑ።

ይህን ካደረጋችሁ፣ የአብ የደስታ እቅድ ተስፋ ምስክርነታችሁ ያብባል እንዲሁም የሚስዮን አገልግሎታችሁ ለእናንተ “ወደ ዘለዓለማዊው ህይወት የሚያድግ ዛፍ ይሆናል”3. የራሳችሁን ህይወት፣ በሚስዮናዊነት የምታገለግሏቸውን ሰዎች ህይወት እና የወደፊት ቤተሰባችሁን ለመባረክ በሰማያዊ አባት እጅ መሳሪያዎች ትሆናላችሁ። እነዚህን መርሆዎች በመላው የወደፊት ህይወታችሁ የራሳችሁ ስታደርጉ፣ ብዙ ጊዜ “መልካም፥ አንተ በጎ ታማኝም ባሪያ፥ በጥቂቱ ታምነሃል፥ በብዙ እሾምሃለሁ፥ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ“ የሚለውን ምስክርነት በልባችሁ የምትቀበሉባቸው ብዙ አጋጣሚዎች ይኖራሉ።”4.

ጆሴፍ ደብልዩ ሲታቲ እንደአጠቃላይ ሰባ ድጋፍ ያገኙት በየካቲት 2009(እ.አ.አ)ነው። ከግላዲስ ናንጎኒ ጋር ትዳር መስርተው የአምስት ልጆች ወላጆች ሆነዋል።

ማስታወሻዎች

  1. አልማ 32፥27 ይመልከቱ።

  2. አልማ 32፥27 ይመልከቱ።

  3. አልማ 32፥41 ይመልከቱ።

  4. ማቴዎስ 25፥21።

አትም