2022 (እ.አ.አ)
ለሚስዮን መዘጋጀት
መጋቢት 2022 (እ.አ.አ)


የአካባቢ መሪ መልዕክት

ለሚስዮን መዘጋጀት

ሚስዮኔን እንዳገለግል በተጠራሁባት አገር ወደ አጎራባች የኮንጎ ዲሞክራታዊ ሪፐብክ ለመድረስ 360 ኪ.ሜ. ተራመድኩኝ።

በነሐሴ 20 ቀን 1994 (እ.አ.አ) በብራዛቪል አውራጃ በማከሌከሌ ቅርንጫፍ ውስጥ ጥምቀቴን ተከትሎ፣ እራሴን የሚከተሉትን ጥያቄዎች ጠየቅኩኝ፦

እራሴን እንዴት ላዘጋጅ?

በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 11፥21 ውስጥ እንዲህ እናነባለን፦ “ቃሌን ለማወጅ አትፈልግ፣ ነገር ግን አስቀድመህ ቃሌን ለማግኘት ፈልግ፣ እናም ከእዚያ አንደበትህ ይፈታል፤ ከዚያም ፈቃድህ ከሆነ አዎን ሰዎችን ለማሳመን የእግዚአብሔር ኃይል የሆነውን ቃሌን እና መንፈሴን ትቀበላለህ።”

ይህ መጽሐፈ ሞርሞንን ማጥናት በምችልበት የሐይማኖት ኢንስቲትውት ውስጥ እንድመዘገብ አነሳሳኝ። ይህ ሕይወቴን አበራው፣ ስለተመለሰው ወንጌል ምስክርነትን እንዳገኝ፣ ወደ ክርስቶስ እንድመጣ ፈቀደልኝ እና የሙሉ ጊዜ የወንጌል ሚስዮንን እንዳገለግል እንድወስን አነሳሳኝ። በኔፊ በታየው መታዘዝ በመነካት በ1ኛ ኔፊ 3፥7 ውስጥ እንዳደረገው ለማድረግ ወሰንኩኝ፦ “እሄዳለሁ ጌታ ያዘዘኝንም ነገሮች አደርጋለሁ ምክንያቱም ጌታ ያዘዛቸውን ትዕዛዛት የሚሟሉበትን መንገድ ካላዘጋጀ በቀር ለሰው ልጆች ትዕዛዛትን እንደማይሰጥ አውቃለሁና።”

በአረሬ በኮንጎ ብራዛቪል ውስጥ በታህሳስ 18 ቀን 1998 (እ.አ.አ) የእርስ በእርስ ጦርነት ከመከፈቱ ከሳምንት በፊት የሚስዮን ጥሪዬን ተቀበልኩኝ። 28 ዓመቴ ነበር። በአገልጋዩ በፕሬዝደንት ጎርደን ቢ. ሂንክሊ (1910–2008) አማካኝነት የተሰጠውን የጌታን ጥሪ መመለስ ነበረብኝ። ሚስዮኔን እንዳገለግል በተጠራሁባት አገር ወደ አጎራባች የኮንጎ ዲሞክራታዊ ሪፐብክ ለመድረስ 360 ኪ.ሜ. ተራመድኩኝ።

ባልንጀሮቻችንን ስናገለግል ተግዳሮቶች ወደ እድሎች ሊቀየሩ ይችላሉ። መጽሐፈ ሞርሞንን ሳነብ እና በቅዱሳት መጻሕፍት ላይ ሳሰላስል ጌታ ኔፊን ሁል ጊዜ እንደረዳው ተገነዘብኩኝ። ያ እኔም በሙሉ ጊዜ ሚስዮን እርሱን ለማገልገል ጽድቅ ውሳኔዎችን ካደረኩኝ ጌታ እኔንም እንደሚረዳኝ ተስፋን ሰጠኝ። በዚህ ልምድ ውስጥ፣ ምንም እንኳን መሰናክሎች ቢኖሩም ነብያችን ከነበሩት ፕሬዝደንት ጎርደን ቢ. ሂንክሊ የደረሰኝን የሚስዮን ጥሪ ደብዳቤዬን በመከተል ወደ ፊት በነፃነት ተጓዝኩኝ። በሚስዮን ላይ በመላው ጉዞዬ ውስጥ የጌታ መንፈስን መገኘት ተሰማኝ።

አንድ ሚስዮን በጌታ እጆች ውስጥ እንደ መሳሪያ እንደሆነ እና የአንድ ሚስዮን አላማ “ሌሎችን የተመለሰውን ወንጌል በእምነት በኢየሱስ ክርስቶስ እና በሃጢያት ክፍያው፣ በንስሃ፣ በጥምቀት፣ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታን በመቀበል እና እስከመጨረሻው እንዲፀኑ በመርዳት ወደ ክርስቶስ እንዲመጡ መጋበዝ” እንደሆነ ማወቅ አስፈላጊ ነው።”1 በሚከተለው ጥያቄ ላይ ማሰላሰል ይኖርብናል፦ይህንን ዓላማ ለማሳካት ከፈለግን እራሳችንን ለማዘጋጀት ምን እናድርግ?

ሁላችንም—ወላጆች፣ ወጣቶች እና ልጆች—እንደሚስዮኖች ለማገልገል ለመዘጋጀት እንችላለን እንዲሁም ይኖርብናል—እንደ ዋርድ ወይም ቅርንጫፍ ሚስዮኖች ለማገልገልም በወጣት እድሜ ለማገልገል ወይም እንደ የአዛውንት ሚስዮኖች ለመጠራት አቅዱ። የሙሉ ጊዜ ሚስዮንን ለማገልገል ብቁ ወጣት ወንዶች ማሰብ ይኖርባቸዋ ሴቶች ደግሞ እንዲያስቡ ይበረታታሉ። ከኤጲስ ቆጶሳችሁ ወይም ከቅርንጫፍ ፕሬዝደንታችሁ ጋር ተነጋገሩ። በዚህ ስራ ውስጥ ለሙሉ ጊዜ ሚስዮን እና የወላጆች ሃላፊነት የዝግጅት ሂደት ማገዝ ይችላል።

በማቴዎስ 28፥19–20 ውስጥ ጌታ እንዲህ አለ፦ “እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እሰከ ዓለም ፍፃሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።”

ይህ እርሱን የሚከተሉት ሰዎች ሁሉ በሚስዮን ስራ ላይ እንዲሰማሩ ሃላነት እንዳለባቸው ይነግረና። በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 88፥81 ውስጥ በዚህ ዘመን መጀመሪያ ላይ ጌታ ይህን አዋጅ እንዲህ በድጋሚ ተናገረ “የተጠነቀቀው ሰው ባልንጀራውን ማስጠንቀቁ አስፈላጊ ነው።”

እህት ኢፒፈኒ ክሪስትል ማቢአላ የተወለደችው በፖት ኑአ፣ የኮንጎ ሪፐብሊክ ውስጥ ነበር። እሷ እና ባለቤቷ የሶስት ልጆች ወላጆች ናቸው። እንደ አካባቢ ድርጅት አማካሪ የተጠራችው በሐምሌ 2021 (እ.አ.አ) ነበር።

ማስታወሻዎች

  1. ወንጌሌን ስበኩ፦ A Guide to Missionary Service [2004] (እ.አ.አ)፣ ገ. 1]።

አትም