2022 (እ.አ.አ)
ቅድመ አያቶቻችሁ የተቀደሱ ስርዓቶችን እንዲቀበሉ እርዷቸው
መጋቢት 2022 (እ.አ.አ)


የቃል ኪዳን መንገዴ

ቅድመ አያቶቻችሁ የተቀደሱ ስርዓቶችን እንዲቀበሉ እርዷቸው

የቤተሰብ ታሪክ ለሁሉም የቤተሰብ አባላት በረከቶችን ያስገኛል።

የሰማይ አባታችን ሁሉንም ልጆቹን ይወዳል እናም የሞቱ የቤተሰብ አባላቶቻችን የወንጌልን በረከቶች እንዲቀበሉ መንገድ አዘጋጅቷል። ብዙ አጥቢያዎች እና ቅርንጫፎች የቤተሰብ ስም እና መረጃ እንዴት እንደሚሰበሰብ የሚያስተምሩ የቤተሰብ ታሪክ ትምህርት ክፍሎች አሏቸው።

በሶዌቶ ካስማ ከሚገኘው የዶብሰንቪል አጥቢያ የመጣችው እህት ዶሊ ኛንዴኒ የቤተሰብ ታሪክን ትወዳለች እናም እንዴት እንደጀመረች ታብራራለች፦ “በቤተክርስቲያን የቤተሰብ ታሪክ ትምህርት ክፍል ተሳተፍኩኝ እና ስለዘር ሃረግ ሰንጠረዥ አሞላል እና ስለቤተሰቤ ሌሎች አስፈላጊ ገጽታዎች ይበልጥ ተማርኩኝ።”

“በጾም እና በጸሎት አማካኝነት መንፈስ ቅዱስ ለቅድመ አያቶቼ ያስፈልጉ የነበሩትን እንደስሞች እና ቀናት ያሉትን ሌሎች ነገሮች ወደማወቅ መራኝ። በተጨማሪም የቤተሰብ ስብሰባ ተጨማሪ መረጃዎችን እንዳገኝ ረዳኝ።”

“በሚልክያ 4 ቁጥር 5 እና 6 ተጨማሪ ግንዛቤ አገኘሁ። ነብዩ ኤሊያስ አስፈሪው የጌታ ቀን ከመምጣቱ በፊት የልጆችን ልብ ወደ አባቶች እንዲሁም የአባቶችን ልብ ወደ ልጆች ስለመመለስ አስተማረ። ያም ከቅድመ አያቶቻችን ጋር ስላለን ትስስር እና ፍቅር ግንዛቤ ሰጠኝ። በመንፈስ ከእኛ ጋር ናቸው።”

የቤተሰባችሁን ስሞች ማሰባሰብ ለመጀመር የሚረዷችሁ ብዙ መረጃዎች በቤተክርስቲያን ይገኛሉ። የ‘My Family’ ትንሽ መጽሃፍ እና FamilySearch.org የመጀመሪያ ሁለት መንገዶች ናቸው። የቤተሰባችሁን ስሞች ስትሞሉ አንድ ጓደኛ ወይም የቤተሰብ አባል እንዲረዳችሁ አድርጉ። ከዚያም ከቤተሰብ እና ከጓደኞች ጋር በቤተመቅደስ ለመሳተፍ እና ለሞቱ የቤተሰባችሁ አባላት ለመጠመቅ ቀን መቁረጥ ትችላላችሁ።

ፕሬዝዳንት ርስል ኤም. ኔልሰን “ቤተመቅደስ እና የቤተሰብ ታሪክ ስራ ከመጋረጃው ሌላኛው በኩል ያሉትን እንዲሁም ህያዋንን በእኩል ደረጃ የመባረክ ሃይል አላቸው። በሚሳተፉት ላይም የማንጻት ሃይል አላቸው። ቃል በቃል በዘላለማዊ ህይወት ከፍ ከፍ እንዲሉ እየረዱ ነው።”1

የትኞቹን የቤተሰብ ቅድመ አያቶች ወደ ቤተመቅደስ እንደምትወስዱ በጸሎት ስታስቡ በምታገለግሏቸው ሰዓት መንፈሱ ይኖራችኋል።

“በቤተመቅደስ አስፈላጊ የሆኑትን ስርዓቶች እያከናወንኩኝ እያለሁ፣ ከቅድመ አያቶቼ ጋር በመንፈስ አንድ ስንሆን የሰማይ አባት ከአጠገቤ መኖሩ፣ ደስታው እና ፍቅሩ ተሰማኝ” ስትል እህት ዶሊ ትናገራለች። አብዝተን እንባረካለን፤ እኛ ያለ እነርሱ እንዲሁም እነርሱ ያለ እኛ ምንም ስለሆንን ከመንፈስ እስር ቤት ሲለቀቁ ያ ደስታ ይኖራቸዋል።”

“ጌታ እስራኤልን የመሰብሰቡን ስራ እያፋጠነ እንደሆነ ነብያችን ነግሮናል። ያ መሰብሰብ ዛሬ በምድር ላይ እየተደረጉ ካሉት እጅግ አስፈላጊው ነገር ነው . . . ብትመርጡ፣ ብትፈልጉ፣ የዚህ ትልቅ አካል መሆን ትችላላችሁ። የአንድ ትልቅ ነገር ታላቅ ነገር፣ ግርማ ሞገስ ያለው ነገር ትልቅ አካል መሆን ትችላላችሁ።”2

የፕሬዝዳንት ኔልሰንን ምክር እንከተል እና የቤተሰብ ታሪክን በመስራት የአንድ ትልቅ፣ ታላቅ፣ ግርማ ሞገስ ያለው ነገር አካል እንሁን።

ማስታወሻዎች

  1. ረስል ኤም ኔልሰን፣ “Generations Linked in Love,” General Conference, የካቲት 2010 (እ.አ.አ)።

  2. ፕሬዝዳንት ኔልሰን፣ “Hope of Israel”, Worldwide Youth Devotional, ሰኔ 2018 (እ.አ.አ)።

አትም