2022 (እ.አ.አ)
መጋቢት ቀን 1842 (እ.አ.አ): ፍቅር ለዘወትር አይወድቅም
መጋቢት 2022 (እ.አ.አ)


ወሩ በቤተክርስቲያኗ ታሪክ ውስጥ

መጋቢት ቀን 1842 (እ.አ.አ): ፍቅር ለዘወትር አይወድቅም

ከ180 አመት በፊት የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን የሴቶች መረዳጃ ማህበር መጋቢት 17 ቀን 1942 (እ.አ.አ) ተደራጀ። የተመሰረተው ሴቶች ሀብታቸውን በአንድ ቋት በማሰባሰብ እና ጥረቶቻቸውን በማቀናጀት በማህበረሰባቸው ውስጥ ላሉ ሰዎች አገልግሎት ለማቅረብ ነበር። ለዚህ ነው የሴቶች መረዳጃ ማህበር የተባለው—ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ድጋፍ ለመስጠት ነበር የተዘጋጀው። የቀድሞው የሴቶች መረዳጃ ማህበር የሴቶች የህክምና ስልጠናን፣ የሆስፒታሎች ግንባታን፣ የጉዲፈቻ አገልግሎቶችን ለማቋቋም፣ የሴቶችን የመምረጥ ነጻነት ለማረጋገጥ እና ሌሎች ነገሮችንም በገንዘብ ለመደገፍ ረድቷል።

ዛሬ የሴቶች መረዳጃ ማህበር የአገልግሎት ፕሮጀክቶችን ያዘጋጃል፣ ከሌሎች ሴቶች ጋር ይገናኛል እንዲሁም የህይወት ክህሎቶችን እና ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲሁም ስለ ወንጌሉ ጥልቅ ግንዛቤ እንዲያዳብሩ ይረዳቸዋል። መሪ ቃሉም “ፍቅር ለዘወትር አይወድቅም” የሚል ነው። የሴቶች መረዳጃ ማህበር እህቶች የኢየሱስን ምሳሌ ለመከተል ይፈልጋሉ፤ እንዲሁም ለጓደኞች፣ ለጎረቤቶች እና ለማያውቋቸው ሰዎች ፍቅርን ይሰጣሉ። የሴቶች መረዳጃ ማህበር በአለም ትልቁ፣ አንጋፋው እና እጅግ የተለያዩ አባላትን ያቀፈ አለም ዓቀፍ ድርጅት ነው። በናቩ ኢሊኖይ የቀይ ጡብ መሸጫ መደብር ውስጥ በትንሹ የጀመረው ስብስብ አሁን በ220 አገሮች ውስጥ ከ7.5 ሚሊዮን በላይ ሴቶችን ያካትታል።

ነብዩ ጆሴፍ ስሚዝ የሴቶች መረዳጃ ማህበርን ሲያቋቁም በክህነቱ ስር እና በክህነቱ መልክ እንደተደራጀ ተናግሯል።ኤሊዛ አር. ስኖው የሴቶች መረዳጃ ማህበር ሁለተኛ አጠቃላይ ፕሬዚዳንት፣ “ሁሉንም ስልጣኑን እና ሃላፊነቱን ከዚያ ምንጭ ያገኛል”።1 ብላለች። የሴቶች መረዳጃ ማህበር አጠቃላይ ፕሬዝዳንት ጂን ቢ. ቢንጋም፣ “ሰዎች የሴቶች መረዳጃ ማህበር በእውነት አለምን ለመለወጥ የሚያስችል ጉልበት ያለው ድርጅት እንደሆነ እንዲያውቁ እፈልጋለሁ . . . ። ዛሬ የሴቶች መረዳጃ ማህበሩ በእግዚብሄር እና በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ እምነታቸውን አድርገው ያልተለመዱ ነገሮችን በሚሰሩ የተለመዱ ሴቶች የተሞላ ነው” ስትል ገልጻለች።2

በ2021 (እ.አ.አ)፣ በአፍሪካ ማዕከላዊ አካባቢ ያሉ ሰባት ሴቶች አዲስ በተፈጠረው የቤተክርስቲያኗ አለም ዓቀፍ የአካባቢ ድርጅት አማካሪ መደብ ላይ እንዲያገለግሉ ተጠርተዋል። ወደዚህ አዲስ መደብ የተጠሩ ሴቶች በቦታው ላለው የሴቶች መረዳጃ ማህበር፣ ለመጀመሪያ ክፍል እና ለወጣት ሴቶች መሪዎች ስልጠና እና ምክር ይሰጣሉ፣ በየአካባቢያቸው ከቤተክሰስቲያኗ ወንዶች እና ሴቶች ጋር ስብሰባዎችን ይሳተፋሉ፣ እንዲሁም የክህነት ግባቸውን ያሳኩ ዘንድ በአካባቢው አመራሮች መመሪያ ያገለግላሉ።

ማስታወሻዎች

  1. Eliza R. Snow, “Female Relief Society,” Deseret Evening News, April 18, 1868, 2.

  2. Jean B. Bingham, “Episode 22: ‘Charity Never Faileth’ Even in a Pandemic President Bingham Celebrates 179 Years of Relief Society,” [Church News Podcast, March 16, 2021], www.TheChurchNews.com/podcast.

አትም