2022 (እ.አ.አ)
የክህነት ስርዓቶች እና በረከቶች
መጋቢት 2022 (እ.አ.አ)


የመመሪያ መጽሃፍ ጎላ ጎላ ያሉ ነጥቦች

የክህነት ስርዓቶች እና በረከቶች

ጌታ “አስፈላጊ ነገሮችን ሁሉ አዘጋጁ”ብሏል (ት እና ቃ 88፥119)። በቅርቡ “አስፈላጊ ነገሮች ሁሉ ምንድን ናቸው” ብለን ራሳችንን ጠይቀናል? በእርግጥ በየቀኑ፣ በየሳምንቱ፣ በየወሩ ወይም በየአመቱ የምናዘጋጃቸው እና በስርዓቱ ምናስቀምጣቸው ብዙ ስጋዊ ነገሮች አሉ። ነገር ግን ልንዘጋጅባቸው የሚገቡን መንፈሳዊ ነገሮችስ ምንድን ናቸው?

በዚህ አመት እነዚህን ለማሰብ እና ለማሰላሰል የተወሰነ ጊዜ እንመድብ፦ ወደመዳን እና ወደዘላለም ህይወት በሚወስደው የቃል ኪዳን መንገድ የት ላይ ነን? ሁሉንም የማዳን ስርዓቶች ተቀብለናል? ካልሆነስ ቀጥሎ ምን ማድረግ ይኖርብናል?

የአጠቃላይ መመሪያዎች መጽሃፍ፣ የክህነት ስርዓቶችን እና በረከቶችን በተመለከተ ክህነት ለደህንነት እና ለዘላለማዊ ህይወት አስፈላጊ የሆኑትን የወንጌል ስርዓቶች የማስተዳደር ስልጣንን እንደሚጨምር ያስተምራል።1 የክህነት ተሸካሚዎች እነዚህን ስርዓቶች እና በረከቶች ሲያከናውኑ አዳኙ ሌሎችን የባረከበትን የእርሱን ምሳሌ ይከተላሉ። የክህነት ስርዓቶች እና በረከቶች የአምላክን ሃይል እንድንጠቀም ያስችሉናል (ት እና ቃ 84፥20ይመልከቱ)። በሰማይ አባት እና በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ባለ እምነት እና በመንፈስ ቅዱስ መመሪያ መሰረት መከናወን ይኖርባቸዋል።

እነዚህን የማዳን ስርዓቶች ስንቀበል ከእግዚአብሄር ጋር ቅዱስ ቃል ኪዳን እንገባለን። እያንዳንዳቸውም እንድን ዘንድ እንዲሁም የዘላለም ሀይወትን እንድናገኝ አስፈላጊ ናቸው። እነርሱም ጥምቀት፣ ማረጋገጫ እና የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ፣ የመልከ ጼዴቅ ክህነትን መቀበል እና መሾም (ለወንዶች)፣ የቤተመቅደስ ቡራኬን መቀበል እንዲሁም በቤተመቅደስ መታተም ናቸው። አነዚህ ስርዓቶች በእድገታችን ላይ የመጀመሪያ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ናቸው። እነዚህን ቅዱስ ቃል ኪዳኖች በማክበር ወደ ዘለአለማዊ ህይወት በሚወስደው የቃል ኪዳን መንገድ ላይ አስፈላጊ እርምጃዎችን እንወስዳለን።

የሰማይ አባታችን ኃይሉን፣ ፈውሱን፣ መፅናናቱን እና መመሪያውን እንድንቀበል የሚያስችሉንን ሌሎች ስርዓቶች እና በረከቶች ሰጥቶናል። እነዚህም ለልጆች ስም መስጠትን እና መባረክን፣ ቅዱስ ቁርባንን፣ የአሮናዊ ክህነትን መቀበልን፣ የፓትርያርክ በረከቶችን፣ በጥሪዎች ለማገልገል መለየትን፣ ዘይትን መቀደስን፣ ለታመሙ መስጠትን፣ የመጽናኛ እና የምክር በረከቶችን (የአባቶችበረከቶችን ይጨምራል)፣ ቤቶችን እና መቃብሮች መቀደስን ያካትታሉ።

ዛሬ በአለም ውስጥ አስቸጋሪ ጊዜያት እያጋጠሙን ሊሆን ይችላል፣ ነገር ግን ዘላለማዊ ጠቀሜታ ባላቸው ነገሮች ላይ ካተኮርን እና ሁሉም መንፈሳዊ ነገሮች መዘጋጀታቸውን እና በስርዓት መቀመጣቸውን ካረጋገጥን በየእለቱ ወደፊት ስንሄጓዝ ሰላም ሊኖረን ይችላል። በመንገዱ ላይም ሌሎችን መርዳት እንችላለን። “ፍጹም[በ]ሆነ የተስፋ ብርሃን” መጠባበቅም እንችላለን (2 ኔፊ 31፥20 ይመልከቱ)።

ማስታወሻዎች

  1. General Handbook: Serving in The Church of Jesus Christ of Latter-day Saints, 3.0–3.4.

አትም