2022 (እ.አ.አ)
“የሚስዮን አገልግሎቴ ይሆናል ብዬ እንደጠበኩት አልነበረም—እናም ይህንን ነበር የተማርኩት።”
መጋቢት 2022 (እ.አ.አ)


የአባል ድምፆች

“የሚስዮን አገልግሎቴ ይሆናል ብዬ እንደጠበኩት አልነበረም—እናም ይህንን ነበር የተማርኩት።”

ክርስቲያና ኦጉነቦቴ የሚስዮን አገልግሎቷን በወረርሽኙ ወቅት ጨረሰች። በብዙ ያልተጠበቁ ክስተቶች መካከል እንዴት እንደተማረች እና እንዳደገች አካፈለች።

በሉሳካ ዛምቢያ ሚስዮኗ በአራት ወር ላይ እህት ክርስቲያና ኦጉነቦቴ ወደ ቤት መሄድ እንዳለባት ተነገራት። የወረርሽኙ መጀመሪያ በዓለም ዙሪያ ያሉ ብዙ ሚስዮኖች ወደ አገራቸው መመለስ አለባቸው ማለት ነበር። ስለዚህ እህት ኦጉነቦቴ ወደ ተወለደችበት ዩናይትድ ኪንግደም ተመለሰች። መለወጡ መቀየሩን ቀጠለ፦ በስኮትላንድ/አየርላንድ ሚስዮን ተመደበች እና ከዛም በጥቅምት 2020 (እ.አ.አ) ወደ ዛምቢያ በድጋሚ ተጠራች። በወረርሽኙ ጊዜ ሚስዮን በማገልገሏ ስለተማረችው ስለ የሕይወት ትምህርት ስትጠየቅ፣ በገዛ ቃላቷ የሚከተሉትን አካፈለች፦

“ብዙ የመማር እና የሕይወት ትምህርቶች ነበሩ። አንደኛው ትልቁ ነገር እንደ ሚስዮን ለማገልገል ስንጠራ የጥሪያችንን ሁኔታዎች መምረጥ አንችልም። ባለን ነገር ሁሉ የትም ይሁን ምንም አይነት ቋንቋም ይሁን በሚስዮን መኖሪያ ቤት ውስጥም ይሁን በውጪ በመንገድ ላይ፣ ጌታን ለማገልገል እንመርጣለን። እነዛን ሁኔታዎች መምረጥ አንችልም።

“ነገር ግን እንዴት ምላሽ እንደምንችል መምረጥ እንችላለን። በደስታ እና በሙሉ ልባችን ለማገልገል መምረጥ ወይም አሉታዊውን ነገር ማየት ከፈለግን እና ማድረግ የማንችለው ነገር እንዲጫነን መምረጥ እንችላለን። ያ ነበር እኔ መማር የቻልት ነገር እና የሚስዮን ልምድ አንዱ ታላቅ ደስታ እንደሆነ ማስታወስ ችያለው። የጌታን ስራ ከማከናወን የበለጠ ደስታን የሚያመጣ ስራ የለም።

“በዛምቢያ ውስጥ መኖር የሕይወቴ የማይታመን ጊዜ ነበር። በስኮትላንድ የነበረኝ ጊዜ ሚስዮኔን ካሰብኩት በላይ ታላቅ አደረገው። በወላጆቼ ቤት ውስጥ ሚስዮን መሆን መቻል እና በቀን ተቀን ሕይወታቸው ውስጥ ሚስዮን ለመሆን መጣር ለእኔ እና ለሌሎች እንደ እኔ ተመሳሳይ ነገርን ላደረጉ ሚስዮኖች የሚያስገርም ሁኔታ ነበር። ለምን ሚስዮኖች መሆን እንደምንፈል ለመረዳት የሚያስፈልገን ስልጠና ነበር ብዬ አስባለው።

“ምንም እንኳን ከአንድ አህጉር ወደ ሌላው ብሄድም እና ጊዜን በቤቴ ውስጥ ከወላጆቼ ጋር ባሳልፍም፣ በእውን የሰማይ አባት በሕይወታችን ዝርዝር ውስጥ እንዳለ እንዳውቅ ልምድ የማግኘት አካል እንደሆነ አውቃለው። እያንዳንዳችንን እርሱ ያውቀናል እና በእርሱ ዕቅድ መሰረት ነገሮችን እንድናደርግ ይፈልጋል።

“ሁሉም ነገር አበባ በአበባ እንደማይሆን በማወቅ የተሻለ የዘላለም እይታ አለኝ። ነገር ግን ያን የዘላለም እይታ መኖር ማለት የሚያጋጥመንን ተግዳሮቶች እና ፈተናዎች ፅናቱን ለማግኘት ጌታ ጥንካሬ የሚሰጠን መንገድ ነው።”

አትም