2022 (እ.አ.አ)
ቅዱስ ቁርባን፦ አዳኝን የምናስታውስበት መንገድ
ሚያዝያ 2022 (እ.አ.አ)


“ቅዱስ ቁርባን፦ አዳኝን የምናስታውስበት መንገድ፣” ሊያሆና፣ ሚያዝያ 2022።

ወርሀዊ የሊያሆና መልዕክት፣ ሚያዝያ 2022 (እ.አ.አ)

ቅዱስ ቁርባን፦ አዳኝን የምናስታውስበት መንገድ

placeholder altText

የመጨረሻው እራት፣ በሳይመን ዱዊ

ከመሰቀሉ በፊት በነበረው ምሽት፣ ኢየሱስ ክርስቶስ በመጨረሻው እራት ከሐዋርያቱ ጋር ተገናኘ። በዚያም ቅዱስ ቁርባንን ለመጀመሪያ ጊዜ ሰጣቸው። እርሱን የሚያስታውሱበት መንገድ እንደሆነ ገለጸ። ቅዱስ ቁርባኑ የክርስቶስን የኃጢያት ክፍያ ለማስታወስ ዳቦ እና ውሃ የምንካፈልበት ስነስርዓት ነው። ዳቦው የክርስቶስን ሰውነት፣ እና ውሀው የእርሱን ደም ይወክላሉ።

በእያንዳንዱ እሁድ በቅዱስ ቁርባን ስብሰባ ላይ ቅዱስ ቁርባንን እንወስዳለን። የክህነት ተሸካሚዎች ዳቦውን በትናንሽ ቁርጥራጮች ሲቆርሱ መዝሙር እንዘምራለን።

ዳቦውን የቆረሱት የክህነት ተሸካሚዎች ልዩ ጸሎት ያደርጋሉ። እነዚህ ጸሎቶች በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 20፥77፣ 79 ውስጥ ይገኛሉ። ጸሎቶቹ ለሰማይ አባት የገባነውን ቃል ኪዳን እና እሱ የገባልንን ቃል ኪዳን ያስታውሰናል።

ሌሎች የክህነት ተሸካሚዎች ቅዱስ ቁርባንን ለአጥቢያው ወይም ለቅርንጫፍ አባላት ያስተላልፋሉ። ቅዱስ ቁርባንን ስንወስድ፣ አዳኝን እና ለእኛ ያደረገውን መስዋዕትነት እናስታውሳለን። ከሰማይ አባት ጋር የገባናቸውን ቃል ኪዳኖች (ተስፋዎች) ለመጠበቅ በድጋሚ ቃል ገብተናል።

በቅዱስ ቁርባን ስብሰባ ወቅት ሴት ልጅ ዳቦ ስትቀበል

ቅዱስ ቁርባን በሚባረክበት እና በሚተላለፍበት ጌዜ በአምልኮ ጸጥታ እንቀመጣለን። ይህም ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ህይወት፣ ትምህርቶች እና የኃጢያት ክፍያ የምናስብበት ጊዜ ነው። የእሱን ምሳሌ መከተል የምንችለው እንዴት እንደሆነ ማሰብም እንችላለን።